tg-me.com/yenetube/54908
Last Update:
ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ተጨማሪ ሁለት አባላቱ መታሰራቸውን አስታወቀ!
-ክልሉ በበኩሉ በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ ሰው የለም ሲል አስተባብሏል
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሰው የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) ሁለት ተጨማሪ አባላቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታወቀ፤ በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ኧርገታ ወርቁ የተባሉ በቡለን ወረዳ የፓርቲው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና አቶ ታምራት ጉዴሶ የተባሉ የፓርቲው አባል መሆናቸው ተገልጿል።
"በዚህ ወንጀል ተብሎ የተጠረጠሩበት የደረሳቸው የወንጀል ክስ የለም" ያሉት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አንድ የፓርቲው አመራር አክለውም የፓርቲው አባል በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ለእስር ተዳርገዋል ሲሉ ገልጸዋል። በክልሉ በተለይም በቡለን ወረዳ በፓርቲያችን አባላቶች ላይ እስር እና ወከባ ቀጥሏል ያሉት አመራሩ "ይህም ለቀጣዩ አገር አቀፍ ምርጫ በቂ ዝግጅት እንዳናደርግ የታለመ ነው" ሲሉ አመልክተዋል።
ጉዳዩን በተመለከተ የጠየቅናቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ቢንያም መንገሻ "በክልሉ እስከአሁን በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራር የለም" ሲሉ አስተባብለዋል።
“ማንኛውም ግለሰብ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣን ይሁን አልያም የተፎካካሪ ፓርቲ አመራር፣ የወንጀል ድርጊቶች ላይ ተሳታፊ ሆኖ የተገኘ ግለሰብ ላይ የክልሉ መንግስት ህግ የማስከበር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተዋል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
BY YeneTube

Share with your friend now:
tg-me.com/yenetube/54908