tg-me.com/tikvahethsport/60244
Last Update:
" ከሽንፈቶቻችን ብዙ ተምረናል " ቡካዮ ሳካ
የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዮ ሳካ ቡድናቸው ባለፉት ጨዋታዎች ካስተናገዳቸው ሽንፈቶች ብዙ መማሩን በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።
" ከገጠሙን ሽንፈቶች በብዙ ተምረናል " ያለው ሳካ " አሁን ወደ አሸናፊነታችን ልንመለስ የሚገባን ጊዜ ላይ ደርሰናል" በማለት የዛሬው የኢንተር ሚላን ጨዋታ ወሳኝ መሆኑን ገልጿል።
ተጨዋቹ አያይዞም ቡድናቸው ዛሬ ከምርጥ ቡድን ጋር እንደሚጫወት በመጥቀስ " ነገር ግን እኛ የትኛውም ቡድንን የማሸነፍ አቅም አለን" ብሏል።
ቡካዩ ሳካ አያይዞም በሰሞኑ ውጤት ምክንያ የአርሰናል ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች እንዲረጋጉ በሰጠው አስተያየት ጠይቋል።
መድፈኞቹ ዛሬ ምሽት 5:00 በሻምፒዮንስ ሊጉ ከኢንተር ሚላን ጋር ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
BY TIKVAH-SPORT

Share with your friend now:
tg-me.com/tikvahethsport/60244