Telegram Group & Telegram Channel
" ላለፉት አምስት አመታት ከሳሽ እንጂ አማራጭ ሃሳብ ይዞ የሚመጣ ግለሰብ፣ቡድን እና ፓርቲ አላየንም " - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)

ከትላንትና በስቲያ የተጀመረው የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን ዛሬ እሁድ ማጠቃለያውን ያገኝቷል።

ጠቅላላ ጉባኤው በፓርቲው ፕሬዜዳንት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የመክፈቻ ንግግር የተከፈተ ሲሆን በጉባኤው የሃገር ውስጥ እንዲሁም የውጭ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ተገኝተውበት ነበር።

" ከቃል እስከ ባህል " በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ የሚገኘው የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በርካታ ውሳኔዎች ይወሰኑበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን እስከሚቀጥለው ጉባኤ ድረስ ፓርቲውን የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች በጉባኤው ላይ እንደሚመረጡ ይጠበቃል።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ዘለግ ያለ ንግግር አሰምተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለግማሽ ሰዓት በሚጠጋ የመክፈቻ ንግግራቸው " ላለፉት አምስት አመታት ከሳሽ እንጂ አማራጭ ሃሳብ ይዞ የመጣ ግለሰብ፣ ቡድን እና ፓርቲ አላየንም " ሲሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የተቹ ሲሆን ሃገር በቀል እሳቤዎችን ይዞ ለሚመጣ ፓርቲ አብረን ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ እየታዩ ላሉ ግጭቶች እና አለመግባባቶችም " ትላንት ፖለቲካ ሲያንቦጫርቁ የነበሩ " ያሏቸውን አካላት ተጠያቂ አድርገዋል።

ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው በዝርዝር ምን አሉ ?

" የኢትዮጵያ የፓርቲ ፖለቲካ ታሪክ በጣም አጭር ነው 60 ዓመት ያልሞላው ታሪክ ነው ያለው።

ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 50 ዓመታት የነበረን የፓርቲ ፖለቲካ  ልምምድ የምንጠላውን አብዝተን መውቀስ ፣ልናፈርስ ልንንድ ያሰብነውን አብዝተን በብዙ ማስረጃ መክሰስ እንጂ ልንገነባ የምናስበውን ፣ልናመጣ የምንፈልገውን ለውጥ ማመላከት ላይ ውስንነት ነበረብን።

ብልጽግና ሊያፈርስ የሚፈልገው በርካታ ኋላ ቀር አሰራሮች እና ልምምዶች ኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ።

ብልጽግና ለኢትዮጵያ ፍቱን መድኃኒት መደመር ነው ብሎ ሃሳብ ይዞ ሲመጣ ላለፉት አምስት አመታት ከሳሽ እንጂ አማራጭ ሃሳብ ይዞ የሚመጣ ግለሰብ፣ ቡድን እና ፓርቲ አላየንም።

ሃሳብ የለሽ ፖለቲከኞች፣ ሃሳብ የለሽ ፓርቲዎች ለአጭር ጊዜ ድል የረጅም ጊዜ መከራን ያመጡብናል ።

ቶርቸር በኢትዮጵያ ይቁም ብለን ላለፉት ስድስት ዓመታት ብታምኑም ባታምኑም አንድ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ቶርች አይደረግም በዚህም እኛ እንኮራለን።

አባቶቻችን ፖለቲካን በቅጡ አልተለማመዱም ሃገርኛ ሃሳብ አላፈለቁም በተዋሱት ሃሳብ ሲጨቃጨቁ እና ሲጋደሉ የኖሩ ስለሆነ አሁንም ያን ማስቀጠል ይፈልጋሉ።

በኦሮሚያ ግጭት አለ ፣በአማራ ግጭት አለ፣በትግራይ ግጭት አለ በተለያየ ቦታ ግጭት አለ የዚህ ግጭት ጠንሳሽ ጨማቂዎች ትላንት ፖለቲካ ሲያንቦጫርቁ የነበሩ ሰዎች ናቸው " ብለዋል።

ዛሬ እሁድ በጠቅላላ ጉባኤ የመሳተፍ ዕድል የሚያገኙት 225 የብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት መሆናቸውን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ከጉባኤው ቀደም ብሎ በሰጡት መግለጫ ማሳወቃቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia

tg-me.com/tikvahethiopia/94183
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
tg-me.com/tikvahethiopia/94183

View MORE
Open in Telegram

TIKVAH ETHIOPIA Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

How Does Bitcoin Mining Work?

Bitcoin mining is the process of adding new transactions to the Bitcoin blockchain. It’s a tough job. People who choose to mine Bitcoin use a process called proof of work, deploying computers in a race to solve mathematical puzzles that verify transactions.To entice miners to keep racing to solve the puzzles and support the overall system, the Bitcoin code rewards miners with new Bitcoins. “This is how new coins are created” and new transactions are added to the blockchain, says Okoro.

How to Invest in Bitcoin?

Like a stock, you can buy and hold Bitcoin as an investment. You can even now do so in special retirement accounts called Bitcoin IRAs. No matter where you choose to hold your Bitcoin, people’s philosophies on how to invest it vary: Some buy and hold long term, some buy and aim to sell after a price rally, and others bet on its price decreasing. Bitcoin’s price over time has experienced big price swings, going as low as $5,165 and as high as $28,990 in 2020 alone. “I think in some places, people might be using Bitcoin to pay for things, but the truth is that it’s an asset that looks like it’s going to be increasing in value relatively quickly for some time,” Marquez says. “So why would you sell something that’s going to be worth so much more next year than it is today? The majority of people that hold it are long-term investors.”

TIKVAH ETHIOPIA from us

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM USA