Telegram Group & Telegram Channel
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የ11 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል !

ኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ከግብፅ ጉቦ ሲበሉ የነበሩት ሴናተር ቦብ ሜንዴዝ የ11 ዓመታት እስር ተፈረደባቸው።

" የግብጽን ጥቅም ለማስከበር ጉቦ ተቀብለዋል " የተባሉት አሜሪካዊው ሴናተር ቦብ ሜንዴዝ የ11 ዓመት እስር ተፈርዶባቸዋል።

ባለፉት 40 ዓመታት በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ የነበሩት ቦብ ሜነንዴዝ ለዓመታት የሀገሪቱ ውጭ ግንኙነት ስራዎች ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰው ነበሩ፡፡

ሜኔንዴዝ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው የአሜሪካ ህግ አውጪ ምክር ቤት ውስጥ ሰርተዋል።

በፈረንጆቹ 2020 ላይ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ በንቃት እንዲሳተፉ የተደረጉ ሲሆን ከፍተኛ ጫና ሲያደርጉ ነበር።

ፖለቲከኛው ይህን ያደረጉት ከግብጽ ባለስልጣናት ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ጉቦ ከተቀበሉ በኋላ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት በማድረግ ላይ የነበሩ ሲሆን የወቅቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህ ውይይት ወደ ዋሸንግተን እንዲመጣ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

በዋሸንግተን በተደረጉት ተከታታይ የሶስትዮሽ ድርድር ላይ ኢትዮጵያ በጫና ወደ ስምምነት እንድትመጣ ግፊት ሲደረግ እንደነበር እና ኢትዮጵያ ስምምነቱን " አልፈርምም " በሚል አቋም መጽናቷ የሚታወቅ ነው።

በወቅቱም የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ፖለቲከኛው ከግብጽ እና ኳታር ኩባንያዎች ጋር ያልተገባ ጥቅም ትስስር በመፍጠር 150 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ወርቅ እና ከ450 ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ ተከፍሏቸዋል።

የሀገሪቱ ፍትህ ተቋማት ባደረጉት ምርመራ ሜኔንዴዝ በጉቦ መቀበል፣ በፍትህ ማዛባት እና ሌሎችም ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸው በክርክር ላይ ቆይተዋል፡፡

የተመሰረተባቸውን ክስ አምነዋል የተባለ ሲሆን እድሜያቸውን፣ አስቀድሞ አስተዳድራዊ ቅጣቶች እንደተላለፈባቸው እና ሌሎች ምክንያቶችን ታሳቢ አድርጎ ቅጣቱን እንዲቀንስላቸው በጠበቃቸው በኩል ጠይቀዋል።

የሀገሪቱ አቃቢ ህግ በቦብ ሜኔንዴዝ ላይ የ15 ዓመት እስር እንዲተላለፍባቸው ፍርድ ቤቱን የጠየቁ ሲሆን ፍርድ ቤቱም በሴናተሩ ላይ በ11 ዓመት እስር እንዲቀጡ ወስኗል ተብሏል።

መረጃውን ሲኤንኤንን (CNN) ዋቢ በማድረግ ያስነበበው አል አይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia

tg-me.com/tikvahethiopia/94135
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
tg-me.com/tikvahethiopia/94135

View MORE
Open in Telegram

TIKVAH ETHIOPIA Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Mr. Durov launched Telegram in late 2013 with his brother, Nikolai, just months before he was pushed out of VK, the Russian social-media platform he founded. Mr. Durov pitched his new app—funded with the proceeds from the VK sale—less as a business than as a way for people to send messages while avoiding government surveillance and censorship.

Spiking bond yields driving sharp losses in tech stocks

A spike in interest rates since the start of the year has accelerated a rotation out of high-growth technology stocks and into value stocks poised to benefit from a reopening of the economy. The Nasdaq has fallen more than 10% over the past month as the Dow has soared to record highs, with a spike in the 10-year US Treasury yield acting as the main catalyst. It recently surged to a cycle high of more than 1.60% after starting the year below 1%. But according to Jim Paulsen, the Leuthold Group's chief investment strategist, rising interest rates do not represent a long-term threat to the stock market. Paulsen expects the 10-year yield to cross 2% by the end of the year. A spike in interest rates and its impact on the stock market depends on the economic backdrop, according to Paulsen. Rising interest rates amid a strengthening economy "may prove no challenge at all for stocks," Paulsen said.

TIKVAH ETHIOPIA from us

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM USA