#AddisAbaba
" ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም " -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ " በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየሰራው ነው " ሲል ገልጿል።
ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ የቁጥጥር ስራው ከዚህ ቀደምም የነበረ ቢሆንም በዘመቻ መልክ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ዘመቻ ሲባል ፦
- ወደ ቫት ስርዓት ውስጥ ያልገቡትን ማስገባት ፣
- ፈቃድ የሌላቸው ፈቃድ እንዲያወጡ ማድረግ፣
- ደረጃቸው ደረሰኝ መስጠት የሚገባቸው ሆኖ ሳለ የማይሰጡትን ደረሰኝ አስፈቅደው እና አሳትመው መጠቀም እንዲጀምሩ ማስቻልን ያካትታል።
የቁጥጥር ስራው በተለይም በገበያ ሞሎች ላይ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ታውቋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘም አንዳንድ ነጋዴዎች እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ " ንብረት ለመውረስ እና ሱቆችንም ለመዝጋት ነው " በሚል ሱቃቸውን ዘግተዋል ንብረትም ወደ ሌላ ቦታ አዙረዋል።
ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ በመርካቶ አካባቢ የሚሰሩ ነጋዴዎች " ከምንም በፊት ያሉትን ችግሮች ማወቅ ይገባል። ቸርቻሪውን ማነጋገር ያስፈልጋል። ችግሮቹን ለመቅረፍ መሰራት አለበት። " ብለዋል።
" ነጋዴው ከአስመጪ እቃ ሲገዛ አስመጪው ከዋጋው በታች ደርሰኝ ይሰጣል አልያም ጭራሽ ላይሰጥም ይችላል ፤ ምንም አይነት የግዢ ደረሰኝ ባላገኘበት ' ነጋዴው ሱቅ ውስጥ ያለዉን ንብረት እንወርሳለን ' ማለት ትክክል አይደለም " ሲሉ አክለዋል።
" መንግሥት ታች ያለው ነጋዴ ላይ ጣቱን ከመቀሰር አስመጪዎቹን ደረሰኝ እንዲሰጡ ማድረግ እና ቸርቻሪውን ማወያየት ያስፈልጋል " ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ አንዳንድ የራሳቸው የገቢዎች ሰዎች ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ቸርቻሪዎችን ማስጨነቅ እንደሚቀናቸው ቃላቸውን የሰጡ አንዳንድ ነጋዴዎች ጠቁመዋል።
ያለ ደረሰኝ ግብይት በሚፈጸምበት ወቅት የገንዘብ ድርድር ሁሉ እንደሚያደርጉና ያሉ ችግሮች ስር የሰደዱ እንደሆኑ ገልጸዋል።
" ከምንም በላይ ያለ ደረሰኝ ግብይት እንዳይኖር ከላይ ጀምሮ መስራት እንደሚገባ ነጋዴው በደረሰኝ ከገዛ በደረሠኝ እንደሚሸጥ ከላይ ግን እጃቸው የረዘመ ሰዎች ስላሉ መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ " አመልክተዋል።
ሁኔታዎችን በመጠቀም በህግ ሰበብ ከነጋዴው ገንዘብ የሚቀበሉና ሙስና የሚሰሩ ህገወጥ ተግባራትንም የሚያባብሱ በገቢዎች አካባቢ ያሉ ሰዎች እንዲታረሙ መሰራት እንዳለበት አክለዋል።
ዛሬ በመርካቶ " ያለ ደረሰኝ ለምን ሸጣችሁ " በሚል ንብረት ይዘው የሄዱም እንዳሉ በመጠቆም በዚህ ምክንያት ሱቆች ተዘግተው እንደነበር ጠቁመዋል።
ሌላ አንድ በቲክቫህ ኢትዮጵያ የሃሳብ መለዋወጫ መድረክ ሃሳባቸውን ያካፈሉ ዜጋ ፥ አስመጪዎች እና አምራቾች ለጅምላ ነጋዴ እና ቸርቻሪ ያለደረሰኝ ስለሚሸጡ ያለደረሰኝ የተገዙ እቃዎች እንደሚኖሩ ገልጸዋል።
" ነጋዴዎች እቃዎቻቸው ሳይወዱ ደረሰኝ ስለሌላቸው እንዳንወረስ ብለው ወደ ሌላ ቦታ ያሸሻሉ ሱቅም ለመዝጋት ይገደዳሉ " ብለዋል።
" ዋናው ስራ መጀመር ያለበት ከአስመጪዎች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች መሆን አለበት ፤ እነሱን በሚገባ ከተቆጣጠሩ እና እርምጃ ከወሰዱ በኋላ በተዋረድ ጅምላ ነጋዴዎች እና ቸርቻሪዎችን መቆጣጠር ይገባል " ብለዋል።
" የችግሩ ምንጭ ከሆኑት አስመጭዎች እና አምራች ኢንዱስትሪዎች ጠበቅ ያለ እርምጃ መወሰድ አለበት " ሲሉ ሃሳባቸውን አካፍለዋል።
" በዛሬው ዕለት በመርካቶ አካባቢ ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው " የሚል ውዥንብሮች በመፈጠራቸው አንዳንድ ነጋዴዎችን ግርታ ውስጥ መክተቱ ተናግሯል።
ስለ ጉዳዩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽን አነጋግሯል።
ዳይሬክተሩ ምን መለሱ ?
➡️ " ጠዋት ሱቆች ሁሉ ተዘግተዋል " ተብሎ ተወርቶ በአካል ዞሬ አይቻለሁ የተወሰኑ ሱቆች የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተዘጉ የሚመስሉ አሉ ነገር ግን መደበኛ ሥራ ቀጥሏል።
➡️ " በዚህ ደረጃ ተዘግቷል ለማለት እይቻልም ተዘጋ የሚባለው ምን ያህል ሱቅ ሲዘጋ ነው ? አንድ ቤት ሁለት ቤት ተዘግቶ ይሆናል ነገር ግን አብዛኛው እየሰራ ነው።
➡️ ህገ ወጥነትን ማስቀጠል የሚፈልግ አካል አለ። ሆን ብሎ ' የሆነ ነገር ተሰርቷል፣ ሊሰራ ነው ' የሚል ውዥንብር መፍጠር የሚፈልግ አካል እንዳለ ነው የተረዳሁት።
➡️ ቁጥጥር ሊደረግ ነው በተለይ አስመጪ እና አከፋፋይ ላይ ሲባል ቸርቻሪ ላይ ስጋት የሚፈጥሩ አሉ፣ በትላንትናው ዕለትም የሚሸሹ ነጋዴዎች ገጥመውናል ያለፍቃድ ይነግዱ የነበሩ ናቸው ብንጠየቅ መልስ የለንም በሚል ስጋት ነው። ሱቃቸውን ቢዘጉም እነሱ ናቸው የሚሆኑት።
➡️ ተዘግቷል የሚለውንም እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል በእርግጥ የተዘጋ ነው ወይስ ነጋዴው በsocial ችግር ሱቃቸውን ዘግተው ስለሌሉ ነው የሚል ጥርጣሬ የሚያጭር ስለሆነ የተዘጉ አይደሉም ወደሚል ድምዳሜ ነው የደረስነው።
➡️ ይርጋ ሃይሌ የገበያ ሞል ላይ ከ15 ቀን በፊት ኮንትሮባንድ ስለነበረ ጎምሩኮች በርብረዋል ደረሰኝ የሌለውን ወርሰዋል ደረሰኝ ያለውን ጥለው ወጥተዋል።
➡️ የገበያ ሞሉ ላይ እቃዎችን መለየት አስቸጋሪ ስለነበር እና ሰዎቹም ተባባሪ ስላልነበሩ ለጊዜው ታሽጎ ነበር። በአሁኑ ሰዓት ሀሉም ተከፍተዋል። የቀረ ካለ በንግድ ቢሮ በኩል ፈቃድ ያልነበረው በመሆኑ በተወሰደ እርምጃ ነው።
➡️ ታሽገው የነበሩ አብዛኛው ሱቆች ተከፍተዋል። እስካሁን ያልተከፈተ ካለ ፈቃድ ስላላወጣ ነው የሚሆነው በተረፈ እቃ የሚወረሰው ኮንትሮባንድ ሲሆን ብቻ ነው።
➡️ ሁሉም ሰው ደረሰኝ ስለማይሰጥ የሚመለከተው ብቻ ነው ደረሰኝ እንዲሰጡ የሚጠበቀው መስጠት የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች ደረሰኝ እየሰጡ ግብይታቸውን ይቀጥሉ።
➡️ " እቃችሁ እየተወረሰ ነው፣ ሊወረስብን ነው" የሚሉ አካላት እቃቸው ምን ስለሆነ ነው የሚወረሰው ? እንደዚህ የሚሉ አካላት ኮንትሮባንድ ስለሆነ ይመስላል።
➡️ ያለደረሰኝ አትግዙ ፣የሚሸጥላችሁን ጠቀሙ እኛ ደግሞ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽምን አካል እንቆጣጠራለን ብለናል የምንከታተላቸውም ለዛ ነው።
➡️ እቃ ለመውረስ የህግ መሰረት ያስፈልጋክ። እቃ የሚወረሰው የታክስ እዳ ማካካሻነት ከተያዘ ብቻ ነው።
➡️ ግብይት ላይ ያለ እቃን የታክስ ማካካሻ ብለን የምንወርስበት ምክንያት የለንም። ክፍተት ያለበትን ነጋዴ ለማወናበድ የሚሮጥ ሌላ ጥላ የሚፈልግ አካል የሚያወራው ወሬ ነው።
➡️ " ያለደረሰኝ አትሽጡ " አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም። ይህም ለነጋዴዎች በደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia

tg-me.com/tikvahethiopia/92064
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
tg-me.com/tikvahethiopia/92064