Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/tikvahethiopia/-91985-91986-91987-91988-91989-91990-91991-): Failed to open stream: No space left on device in /var/www/tg-me/post.php on line 50
TIKVAH-ETHIOPIA | Telegram Webview: tikvahethiopia/91991 -
Telegram Group & Telegram Channel
#ሞዛምቢክ

• 49 ዓመታት ስልጣን ላይ የቆየ ገዢ ፓርቲ ዕጩ ምርጫ ማሸነፉ ተቃውሞና አመጽ ቀስቅሷል።

በአፍሪካዊቷ ሀገር ሞዛምቢክ ባለፈው ወር ላይ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ተደርጎ ነበር።

ለረጅም አመታት ስልጣን ላይ የቆየው ገዢ ፓርቲ ዕጩ ዳንኤል ቻፖ " ምርጫውን አሸነፉ " መባሉ ከፍተኛ ተቃውሞ እና አመጽ ቀስቅሶ ሰዎች ተገድለዋል።

የአደባባይ ተቃውሞዎችም እየተደረጉ ነው።

አወዛጋቢ ነው በተባለው ምርጫ አሸንፏል የተባለውን " ፍሬሊሞ " የተሰኘውን ገዢ ፓርቲ ለመቃወም ዛሬ ማፑቶ ላይ ሰልፍ የወጡ ብዙሃኑ ወጣቶችን የፀጥታ ኃይሎች የአስለቃሽ ጭስ እየተኮሱ ሲያሳድዱ ውለዋል።

ምርጫውን " አሸንፏል " የተባለው ፓርቲ 49 ዓመታት ስልጣን ላይ የቆየ ሲሆን የምርጫ ውጤቱ የ49 ዓመታት ስልጣኑን ለማራዘም ያስችለዋል ተብሏል።

ይሄ ገዢ ፓርቲ እ.ኤ.አ ከ1975 ጀምሮ በስልጣን ላይ ይገኛል።

የፍሬሊሞ ፓርቲ ዕጩ ምርጫ ማሸነፉ ይፋ ከተደረገ በኃላ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ 18 ሰዎች በፖሊስ መገደላቸውን የሰብዓዊ መብት ተቋማት ገልጸዋል።

ምርጫው ከፍተኛ ፉክክር የተደረገበት ነበር የተባለ ሲሆን ብዙሃኑ ወጣቶች ዋነኛውን ተቀናቃኝ የ ' ፖዴሞስ ' መሪ ቬንሢዮ ሞንዳኔ ደግፈው ድምጽ መስጥታቸው ተነግሯል።

እሳቸውም ምርጫው የተጭበረበረ እንደሆነ ገልጸው ተቃውሞዎችን አበረታተዋል።

ምርጫው መጭበርበሩን ብቻ ሳይሆን እሳቸው እንዳሸነፉ የገለጹት ሞንዳኔ ፥ የግድያ ሙከራ ጭምር ተደርጎባቸው እንዳመለጡ ገልጸዋል።

ጠበቃቸው መገደላቸውንም ጠቁመዋል።

አሁን ላይም ሀገር ውስጥ እንደማይገኙ ተነግሯል።

ዛሬ በዋና ከተማይቱ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ የተቆጡ ሰልፈኞች " ስልጣን ለህዝብ " ፣ " ውድቀት ለፍሬሊሞ " እና " ፍሬሊሞ መውደቅ አለበት " ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ፖሊሶች አስለቃሽ ጭስ ተጠቅመው ሰልፉን በትነዋል።

አንድ እድሜያቸው 55 የሆነ የ6 ልጆች እናት " አሁን ካልተነሳን ምንም ለውጥ አይመጣም " ሲሉ ተናግረዋል።

" የፍሬሊሞ ጀርባ የሚታይበት ጊዜው አሁን ነው " ብለዋል።

ህዝባዊ ተቃውሞው ከተባባሰ በኋላ የሀገሪቱ ተሰናባች ፕሬዝዳንት ፊሊፔ ኑዩሲ ትንፍሽ አላሉም።

የመከላከያ ሚኒስትራቸው ግን ወጥተው ወታደሩን እንደሚያሰማሩ እና ስልጣን በኃይል ለማያዝ ሙከራ እንዳይደረግ አስጠንቅቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ማሰባሰቡን ይገልጻል።

@tikvahethiopia

tg-me.com/tikvahethiopia/91991
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
tg-me.com/tikvahethiopia/91991

View MORE
Open in Telegram

TIKVAH ETHIOPIA Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

What Is Bitcoin?

Bitcoin is a decentralized digital currency that you can buy, sell and exchange directly, without an intermediary like a bank. Bitcoin’s creator, Satoshi Nakamoto, originally described the need for “an electronic payment system based on cryptographic proof instead of trust.” Each and every Bitcoin transaction that’s ever been made exists on a public ledger accessible to everyone, making transactions hard to reverse and difficult to fake. That’s by design: Core to their decentralized nature, Bitcoins aren’t backed by the government or any issuing institution, and there’s nothing to guarantee their value besides the proof baked in the heart of the system. “The reason why it’s worth money is simply because we, as people, decided it has value—same as gold,” says Anton Mozgovoy, co-founder & CEO of digital financial service company Holyheld.

If riding a bucking bronco is your idea of fun, you’re going to love what the stock market has in store. Consider this past week’s ride a preview.The week’s action didn’t look like much, if you didn’t know better. The Dow Jones Industrial Average rose 213.12 points or 0.6%, while the S&P 500 advanced 0.5%, and the Nasdaq Composite ended little changed.

TIKVAH ETHIOPIA from us

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM USA