#ጥናት
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሥር የሚንቀሳቀሰው የጄኖሳይድ አጣሪ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው አዲስ ጥናት በክልሉ የሚገኙ የሥራ አጦች ቁጥር እጅግ አሻቅቧል።
የአጣሪ ኮሚሽኑ ሰነድ ምን ይላል ?
➡ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከጥቅል ክልላዊ ምርት አኳያ (GDP Per Capita) ከጦርነቱ በፊት ነበረ ከተባለበት 845 ዶላር ወደ 10.2 ዶላር አሽቆልቁሏል።
➡ የድህነት ምጣኔ ከ29.6 በመቶ ወደ 91.09 በመቶ አሻቅቧል።
➡ የምግብ ደኅንነት ዋስትናን ማስጠበቅ ምጣኔ ከ74.20 በመቶ ወደ 18.73 በመቶ ወርዷል።
➡ አጠቃላይ በየዓመቱ በአማካይ የሚሰበሰብ ሰብል በፊት ከነበረው 20,633,070 ኩንታል ወደ 5.2 ሚሊዮን ኩንታል ዝቅ ብሏል።
➡ የአትክልት ዋጋ ግሽበት ከ8.5 በመቶ ወደ 179.8 በመቶ ከፍ ብሏል።
➡ ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካቾች ሆነው ከቀረቡት መካከል አንዱ የሆነው የሥራ አጦች ምጣኔ ነው። ይህም ከጦርነቱ ጅማሮ በፊት ከነበረበት 17 በመቶ በአሁኑ ወቅት ከፍ ብሎ 74.1 በመቶ ላይ ደርሷል።
ኮሚሽኑ ያቀረበው የጥናት ውጤት የክልሉ ወጣቶች ማኅበር በተናጠል ባደረገው ጥናት ግኝት ላይም ተመላክቷል።
የማኅበሩ የጥናት ውጤት ምን ይላል ?
🔴 የሥራ አጥ ምጣኔው ባለፈው ዓመት ከነበረበት 81 በመቶ በዘንድሮው ዓመት ዝቅ ብሏል።
🔴ባለፈው ዓመት በክልሉ ከነበሩ 10 ወጣቶች ስምንቱ ሥራ አጥ ነበሩ።
🔴 በባለፈው ዓመት ጥናት በክልሉ ከነበሩ አጠቃላይ ወጣቶች 40 በመቶ ያህሉ ቀዬአቸውን ለቀው ሥራ ፍለጋ የመሰደድ ፍላጎት እንዳላቸው ተጠንቷል። ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 54 በመቶ ያህሉ ከ29 እስከ 35 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ምርታማ የሚባሉ ወጣቶች ናቸው።
🔴 በያዝነው ዓመት የሥራ አጥ ወጣቶች መጠን በስምንት በመቶ ቢቀንስም ወደ 12 በመቶ የሚጠጉ የክልሉ ወጣቶች የአካል ጉዳትና ጤና እክልን ጨምሮ በሌሎችም ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምክንያት ሥራ ለመፈለግም ሆነ ለመሥራት አልቻሉም።
🔴 ከሥራ አጥ ወጣቶች መካከል 23.4 በመቶው በየዕለቱ በሥራ ፍለጋ ላይ ቢሰማሩም በፋይናንስ እጥረት፣ በመሠረተ ልማት አለመሟላት፣ አስተዳደራዊና መዋቅራዊ መሰናክሎችን በመሳሰሉ ዋና ዋና ጉዳዩች ምክንያትነት ሥራ ማግኘት አልቻሉም።
🔴 ከአጠቃላይ የጥናቱ ተሳታፊዎች 52 በመቶው ሥራ የማግኘትም ሆነ የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅማቸው በኢኮኖሚያዊ መደላድሎች አለመሟላት እንደተደናቀፈባቸው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። ወደ 46 በመቶ የሚጠጉት ደግሞ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ የሥራ ፍለጋ ሁኔታቸው ላይ ችግር እየፈጠረ ስለመሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
🔴 ወጣቶች ሌሎች የሥራ ሁኔታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደሩ እንደሆነ ከገለጿቸው ጉዳዩች መካከል፣ የማኅበራዊ አገልግሎቶች አለመሟላት፣ የተለያዩ የጤና እክሎች፣ ማንነት፣ እንዲሁም ፆታና ዕድሜን መሠረት ያደረገ አድልኦና መገለል ተጠቃሽ ናቸው።
አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በኃላፊነት ላይ የሚገኙ አካል በ2016 ዓ.ም. ብቻ በክልሉ 49 ወረዳዎች በተደረገ ጥናት 27,000 ወጣቶች ሥራ ፍለጋ ወደ ውጭ አገሮች ለመሰደድ ቀዬአቸውን ለቀው መውጣታቸውን ቤተሰቦቻቸው መግለጻቸውን ተናግረዋል፡፡
ወጣቶች በብዛት እየተሰደዱ ካሉባቸው ሥፍራዎችም የኢሮብ ብሔረሰብ ወረዳዎችና የማዕከላዊ ትግራይ ዞን አካባቢዎች ይገኙበታል።
" በ2016 ዓ.ም. በኢሮብ ወረዳ ብቻ ከተሰበሰበ መረጃ 32 ወጣቶች ወደ ውጭ አገሮች በሕገወጥ መንገድ ሲሰደዱ በረሃ ላይ በተለያዩ መንገዶች ሕይወታቸው ማለፉን ቤተሰቦቻቸው ተረድተዋል " ብለዋል።
ከክልሉ በተገኘ መረጃ በጂቡቲና በሶማሊያ በኩል ወደ የመን በሕገወጥ መንገድ ለመሰደድ ዜጎች ከ300 እስከ 500 ሺሕ ብር እየከፈሉ ናቸው።
ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የመረጃ ምንጭ፣ " ወጣቱ ለስደት ወጥቶ ሕይወቱ ያለፈ ወንድሙን ለቅሶ አርባ ቀን እንኳን ሳያወጣ ነው ተነስቶ ለስደት እየወጣ ያለው " ብለዋል።
ሴቶች በደላሎቹ እጅግ ተፈላጊ መሆናቸውንና ሴቶችን ለሚያመጡ ወንዶች እስከ ነፃ ጉዞ ድረስ የሚደርስ ድርድር እንደሚያደርጉ ከስደተኞች መስማታቸውንም ተናግረዋል።
ወጣቶች በገፍ እየተሰደዱ ያለበትን ምክንያት በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ " የመጀመሪያው የደኅንነት ጉዳይ ነው፣ ደኅንነት እየተሰማቸው አይደለም፡፡ በተለይ በድንበር አካባቢ ያለው ወጣት በአንድ በኩል የኤርትራ ኃይል በየቀኑ ሰውን እያፈሰ ሲወስድ ይመለከታል፡፡ ሕዝቡ በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው። ሌላው የሚሰደደው የሥራ ዕድል ለመፍጠርም ሆነ ሥራ ለማግኘትም ያልቻለ ነው፡፡ በሌላ በኩል ጦርነት እንዳያገረሽ ሥጋት ያለበትም እንዲሁ እየተሰደደ ነው " ብለዋል።
(ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሪፖርተር ጋዜጣ ነው)
@tikvahethiopia

tg-me.com/tikvahethiopia/91971
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
tg-me.com/tikvahethiopia/91971