Telegram Group & Telegram Channel
አንድ እንጀራ 30 ብር በገባበት ወቅት 450 ብር ለምን ይጠቅማል ? ለቤት ኪራይ፣ ወይስ ለቀለብ ነው የሚሆነው? ” - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር።

የመምህራን የስልጠና ክፍያ እጅግ አነስተኛ መሆን ከኑሮ ውደነት ጋር ተያይዞ ፣ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሰጡት የነበረውን የሙያ ስልጠና አለመስጠታቸው የትምህርት ጥራት ቀውስ ውስጥ እንዲገባ እያደረገ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጠየቀ።

ከማኀበሩ የተሰነዘሩ ቅሬታዎች ምንድን ናቸው ?

“ ከትምህርት ሥርዓት አንጻር በአሁኑ ሰዓት የትምህርት ጥራት ችግር ብቻ ልንለው አንችልም። የትምህርት ቀውስ ነው። ቀውስ ውስጥ ገብተናል። ወደ መምህራን ችግሩን የመግፋት ነገር ይታያል። ይሄ ትክክል አይደለም። 

ሲጀመር የመምህርት ስልጠና ዋጋ አልተሰጠውም። ለምላሌ ፦ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት እጩ መምህራን ከተወሰኑ ኮሌጆች ውጪ 450 ብር ተሰጥቷቸው ውጪ ሆነው እንዲማሩ የሚደረጉት።

አንድ እንጀራ 30 ብር በገባበት ወቅት 450 ብር ለምን ይጠቅማል ? ለቤት ኪራይ ወይስ ለቀለብ ነው የሚሆነው ? ችግሩ እዚያ ጋ ነው የሚጀምረው። 

እጩ መምህራን ወደ ኮሌጅ ውስጥ ሲገቡ 450 ብር ይከፈላቸዋል። ፍላጎታቸውን ስለማይሟላ ትምህርት ላይ ትኩረት ሳያደርጉ ፍላጎታቸውን ለሟሟላት ይንቀሳቀሳሉ። ይሄ የመምህርነትን ሙያ ጥራቱን ቀንሶታል። ስለዚህ ጉዳዩ ሊታረብበት ይገባል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር ጥናት አጥንቷል። በዚያ መልኩ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል

በሌላ በኩል ፥ ወደ መምህርነት ሙያ ሴንተር ኦፍ ኤክሰለንሲ ተብለው እነዚህ የመቐለ ፣ ባሕር ዳር፣ የአዲስ አበባ፣ ጅማና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንን የሚያሰለጥኑ ነበሩ ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች። 

ነገር ግን ላለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ምንም አይነት ተማሪ ወደ መምህርነት ሙያ እንዲገባ እያሰለጠኑ አይደለም። 

ይሄ ደግሞ በቀጣይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶቻችንን በድጎማ መምህር ልናስይዝ አይደለም ወይ ! ይሄ ወዴት እየሄደ ነው ?

በተያያዘ፣ የመፅሐፍት ስርጭት ችግሮች አሉ። ችግር መኖር ብቻ ሳንሆን አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ በአንድ ላይ ኮምባይን የሆኑ ትምህርት ቤቶች አሉ። 

ለምላሌ ፦ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ባይሎጂ አንድ ላይ ናቸው። በአንድ መምህር ነው የሚሰጡት። ይህም መምህራን ኬሚስትሪውን ፓርት ያስተምሩና ፊዚክስና ባይሎጂው የተመረቁበት ስለማይሆን ለማስተማር እየተቸገሩ ነው። 

በሌሎች የትምህርት አይነቶችም ተመሳሳይ ችግር አለ። መምህር ያልተዘጋጀባቸው ሥርዓተ ትምህርቶች አሉ። የትምህርት ጥራቱን እየጎዳው ያለው አንዱ ችግር ይሄ ነው። አጠቃላይ ትምህርቱ ሴክተሩ በቂ ትኩረት አላገኘም። በቂ ፋይናንስ እየተመደበለት አይደለምና ሊመደብለት ይገባል።

መምህራንም የተለያዬ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሲፈጠሩ መብታቸውን ለማስከበር ወደ ሕግ ተቋማት ስለሚሄዱ የትምህርት ጊዜ ይዘጋል። ይሄ ደግሞ የትምህርት ጥራት ላይ ችግር አምጥቷል። ”

እነዚህ ቅሬታዎች የትምህርት ሚኒስቴር በተገኘበት መድረክ እንደቀረቡ ማኀበርሩ ገልጾልናል።

የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዲሰጡ ያሳሰበው ማኀበሩ፣ ትምህርት ሚኒስቴር በተነሱት ቅሬታዎች ዙሪያ መፍትሄ ለማምጣት አሳይመንት ይዞ እንደሄደ አመላክቷል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia

tg-me.com/tikvahethiopia/91560
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
tg-me.com/tikvahethiopia/91560

View MORE
Open in Telegram

TIKVAH ETHIOPIA Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

A Telegram spokesman declined to comment on the bond issue or the amount of the debt the company has due. The spokesman said Telegram’s equipment and bandwidth costs are growing because it has consistently posted more than 40% year-to-year growth in users.

For some time, Mr. Durov and a few dozen staffers had no fixed headquarters, but rather traveled the world, setting up shop in one city after another, he told the Journal in 2016. The company now has its operational base in Dubai, though it says it doesn’t keep servers there.Mr. Durov maintains a yearslong friendship from his VK days with actor and tech investor Jared Leto, with whom he shares an ascetic lifestyle that eschews meat and alcohol.

TIKVAH ETHIOPIA from us

Telegram TIKVAH-ETHIOPIA
FROM USA