TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ተፈታኞች ፈተናውን ያለምንም ጭንቀትና ስጋት በጥንቃቄ ስሩ " - ትምህርት ሚኒስቴር
ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ያለምንም ጭንቀትና ስጋት ተረጋግተው እንዲወስዱ መልዕክቱን አስተለልፏል።
ሚኒስቴሩ ዛሬ የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ለተፈታኞች መልዕክት አስተላልፏል።
በዚህ መልዕክቱ ፤ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና በተማሩት የትምህርት መስክ ከፍተኛ ግንዛቤ ያላቸውን ተመራቂዎች ለማፍራት እንዲቻል የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። ከእነዚህም መካከል አንዱ የመውጫ ፈተና መስጠት እንደሆነ አመልክቷል።
ከዚህ ዓመት ጀምሮ በየትኛውም የትምህርት መስክና ከየትኛውም የአገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ተከታትለው የሚወጡ ተማሪዎች በኦንላይን የመውጫ ፈተና እንዲወስዱ እየሰራ መሆኑና የመውጫ ፈተና የሚሰጥበት ቀንም በአገር አቀፍ ደረጃ ሰኔ 30 ቀን በጤናና ተጏዳኝ መስኮች መሰጠት መጀመሩን ገልጿል።
ሚኒስቴሩ ፤ ፈተናው በኦንላይን እንዲሰጥ ሲያደርግ በየደረጃው ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ የቆየ መሆኑንና አስፈታኝ ተቋማትም ያደረጉትን ዝግጅት መገምገሙን ጠቁሟል።
ባደረገው ክትትልና ግምገማም ሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተናውን ለመስጠት በሚያስችል ዝግጅትና ቁመና ላይ መሆናቸውን እንዳረጋገጠ ገልጿል።
በተጨማሪ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የፈተና አዘገጃጀቱን በበላይነት ሲመራና ሲከታተል መቆየቱን ጥያቄዎቹ በየዘርፉ መምህራን እንዲዘጋጁና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ የማድረግ ሥራ መስራቱን አስገንዝቧል።
ይህ የመውጫ ፈተና ሁሉንም የቅድመ ምረቃ ድግሪ የሚሸፍን ነው ያለው ሚኒስቴሩ ፤ በዲጂታል መሰጠቱ ልዩ ያደርገዋል ብሏል።
ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን ገልጾ ለተፈታኝ ተማሪዎችም ጥያቄዎቹ የተዘጋጁት በቆይታቸው ከተማሯቸው ርዕሰ ጉዳዮች መሆኑን ተገንዝበው ያለምንም ጭንቀትና ስጋት በጥንቃቄ እንዲሰሩ አሳስቧል።
@tikvahethiopia

tg-me.com/tikvahethiopia/79608
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
tg-me.com/tikvahethiopia/79608