#ትግራይ #መቐለ
" ስካይ ማይክሮፋይናንስ አ/ማ " የተሰኘ የቁጠባና የብድር የፋይናንስ ተቋም በይፋ ተመሰረተ።
የስካይ ማይክሮፋይናንስ ሰብሳቢ አቶ ግርማይ ካሕሳይ በይፋዊ የምስረታ ፕሮግራም ባሰሙት ንግግር ተቋሙ በመላ አገሪቱ መንቀሳቀስ የሚያስችለው ፍቃድ ከብሄራዊ ባንክ ማግኘቱንና ዘመኑ በሚጠይቀው ቴክኖሎጂ በመታገዝ የቁጠባ ፣ የገቢ ወጪ እንዲሁም ገንዘብ የመቀበል እና የማስተላለፍ የሃዋላ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል ።
የአንድ አክስዮን የሽያጭ ዋጋ አንድ ሺ ብር መሆኑና በግለሰብ 10,000 ፤ በተቋም 30,000 አክስዮኖች መግዛት እንደሚቻል ያብራሩት ሰብሳቢው ፤ ተቋሙ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት መደበኛ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ብለዋል።
የትግራይ ክልል የፋይናንስ ፎረም አስተባባሪና የፕሮግራሙ የክብር እንግዳ ዶ/ር መብራህቱ መለስ " የፋይናንስ እንቅስቃሴ በድህረ ግጭት ወቅት " በሚል ርእስ ባቀረቡት ፅሁፍ ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ የፋይናንስ ተቋማት ምስረታ በመላ አገሪቱ መስፋፋቱንና ፤ በትግራይ እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ 59 ቢሊዮን ብር የቆጠቡ ፤ ከ70 ሚሊዮን ብድር መስጠት የቻሉ 1074 ቅርንጫፍ ያላቸው 44 የፋይናንስ ተቋማት እንደነበሩ ገልፀው ፤ ተቋማቱ በተካሄደው ጦርነት ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርገዋል ብለዋል።
ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የፋይናንስ ዘርፉ በክልሉ መነቃቃት ማሳየት እንደጀመረ የዚሁ ማሳያ ስካይ ጨምሮ 45 የግል የፋይናንስ ተቋማት በምስረታ ላይ መሆናቸው ዶ/ር መብራህቱ አስታውቀዋል።
ባለፉት ሶስት የጦርነት አመታት የትግራይ የፋይናስ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዱንና ይህንን ለማዳንና ክልላዊና አገራዊ ፋይዳው እንዲጎለብት የፌደራል መንግስት የተለየ ትኩረት መስጠት ይገባዋል ብለዋል ዶ/ር መብራህቱ መለስ።
የምስረታ ፕሮግራሙ ተሳታፊ ወ/ሮ ለምለም ሃይሚካኤልና አቶ አስገዶም አሰፋ በሰጡት አስተያየት የተበታተነ ፋይናንስ በቁጠባ መልክ በማሰባሰብ መልሰው ለአገርና ህዝብ እድገት ብድር በመስጠት ኢኮኖሚው የሚደገፉ የግል የፋይናንስ ተቋማት የመንግስት ልዩ ትኩረትና ጥበቃ ይሻሉ ።
በስካይ ማይክሮፋይናንስ አ/ማ ይፋዊ የምስረታ ፕሮግራም ባለ አክስዮኖች የሃይማኖት መሪዎች : በፋይናንስ ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ ተቋማት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ለማወቅ ችለናል።
@tikvahethiopia

tg-me.com/tikvahethiopia/79590
Create:
Last Update:

BY TIKVAH-ETHIOPIA

Share with your friend now:
tg-me.com/tikvahethiopia/79590