tg-me.com/techzone_ethio/1504
Last Update:
✳️ Chrom Browser ተጠቃሚዎች በአስቸኳይ ⚠️ (Update) ⚠️ እንዲያደርጉ ጉግል አሳሰበ!
💠አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 26/2013፡- በጉግል ክሮም የመረጃ ማፈላለጊያዉ (Browser) ላይ ከፍተኛ የሚባል የደህንነት ክፍተት መከሰቱን ተከትሎ ተጠቃሚዎች ክሮምን (Chrome) በፍጥነት እንዲያዘምኑ ጉግል አሳሰበ፡፡
💠ከዚህ ቀደም ወቅታቸዉን ጠብቀዉ በሚለቀቁ የሶፍትዌር ዝመናዎች ያልተለዩ የዜሮ ደይ (zero-day) ተጋላጭነቶች እና የደህንነት ክፍተቶች መከሰታቸዉን ጉግል ኩባንያ ገልጿል፡፡ ይህን ተከትሎም ጉግል ድንገተኛ የሆነ እና ለክፍተቱ መድፈኛ የሚሆኑ ዝመናዎችን (Update) ለክሮም መረጃ ማፈላለጊያ ተጠቃሚዎች አቅርቧል፡፡
💠በጉግል የስጋት ትንተና ቡድን የተገኘዉ የጥቃት ተጋላጭነት (CVE-2020-16009) ዘግይቶ የተገኘ የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ሲሆን ጉግል ባለፈው ወር 'ለዜሮ-ደይ' ክፍተት የሚሆን መጠገኛ ያቀረበ ቢሆንም የዊንዶውስ ስርዓትን የሚጎዳ ተጨማሪ ክፍተት ተከስቷል፡፡
💠በክሮም የተገኘዉ (CVE-2020-16009) ተጋላጭነት የጃቫ ስክሪፕትን (JavaScript) ኮድ በሚያስተዳድረው የአሳሽ ክፍል ውስጥ ተደብቆ ተገኝቷል፡፡ ሆኖም ተጠቃሚዎች የክሮም የመረጃ ማፈላለጊያ ወደ version (86.0.4240.183) ወይም ከዚያ በኋላ ወደ ተለቀቁ የክሮም ስሪቶች እንዲያሳድጉ ጉግል አሳስቧል፡፡
💠Chrom ተጠቃሚዎች ብሮዉዘሩን ለማዘመን "Customize and control Google Chrome" የሚለዉን በመክፈት "Settings" መምረጥ ከዚም "about chrome"ን በመጫን እየተጠቀሙበት ያለዉ ከ 'Version 86.0.4240.183' በታች ከሆነ አሁኑኑ ክሮሙን Update ያርጉ፡፡
© መረጃው ከ Mame Tech የተወሰደ ነው።
▫️JOIN👉
@techzone_ethio
@techzone_ethio
BY ᴇᴛʜɪᴏ ᴛᴇᴄʜ ᴢᴏɴᴇ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283
Share with your friend now:
tg-me.com/techzone_ethio/1504