tg-me.com/ortodoxtewahedo/21777
Last Update:
#በውስጥ መስመር ለተጠየቀ ጥያቄ መልስ።
#እግዚኦ_መሐረነ_ክርስቶስ_ለምን _እንላለን ?.......
—————“ #ሚስጢሩ ”—————
✔ በቤተክርስቲያናችን ስርዓት ሁል ጊዜ ካህኑ እግዚአብሔር ከታሰራችሁበት ኃጥያት ማሰሪያይፍታቹ ሲሉ
❖ 12 ጊዜ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስና
❖ 12 ጊዜ ደግሞ በእንተ እግዝትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ያስብላሉ ።
✔ ካህናትና ምእመናን በጣቶቻችን እየቆጠርን ይህኑን 12 ጊዜ እንላለን ።
============
✔ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ማለት አቤቱ ክርስቶስ ማረን ሲሆን በእንተ እግዝእትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ ደግሞ ስለ እመቤታችን ማርያም ብለህ ክርስቶስ ሆይ ማረን ማለት ነው ።
=============
✔አስራ ሁሉት ጊዜ መሐረነ መባሉ ለቀኑ 12 ሰዓት በእንተ እግዝእትነ ማርያም ደግሞ ለሊቱን
12 ሰዓት ሲሆን በአጠቃላይ በየሰዓቱ ለሰራነው ኃጥያት በሃያ አራቱ 24ቱ ሰዓት ምሕረት እናገኝ ዘንድ ነው።
🌼ሌላው አስራ ሁለት ጊዜ የሆነበት ምክንያት፦
☞ 1ኛ በስመ ሥላሴ ነው በእያንዳንዱ ፊደል•••
• አ ብ ወ ል ድ መ ን ፈ ስ ቅ ዱ ስ
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪
☞2ኛ የድህነታችን ምክንያት በሆነች በእመቤታችን ስም ፊደል ነው ።
• ቅ ድ ስ ት ድ ን ግ ል ማ ር ያ ም
፩ ፪ ፫ ፬ ፭ ፮ ፯ ፰ ፱ ፲ ፲፩ ፲፪
—————“እግዚኦ”————-
✔አቆጣጠረም እግዚኦ መሐረነ ሲባል በአውራ ጣት እየቆጠሩ ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ፣ቀጥሎ በመሐል ጣት ወደ ላይ ከዚያም በቀለበት ጣት ወደ ታች ተደርጎ በማርያም ጣት / በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ነው ።
✔ከጠቋሚ ጣት ወደ ታች ~ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት መውረዱን በዚህ ምድር መመላለሱን ሕማሙንና ሞቱን እናስባለን ።
=====================
✔ መሐል ጣት ወደ ላይ ~ማረጉን ወደ ሰማይ መውጣቱን በቀለበት ጣት ወደ ታች ስንቆጥር ወደዚች አለም ለፍርድ መምጣቱን፤
• በትንሿ/ ጣት ወደ ላይ ስንወጣ ደግሞ በትንሳኤ ዘጉባኤ ይዞን ወደ ሰማይ እንደሚያወጣን እያሰብን ነው።
—————“ብእንተ”————-
✔ በእንተ እግዝትነ ማርያም ስንል አቆጣጠሩ
• ከትንሿ ጣት ወደ ታች ይጀመርና
• በጠቋሚ ጣት ወደ ላይ ይፈጸማል ይህም እመቤታችን ድንግል ማርያም ከትሕትና ወደ ልዕልና ከፍ ማለቷን
የሚያሳይ ምሥጢር ነው ።
• ብእንት ሲባል በትንሿ ጣት ወደ ታች የሚጀመር ራሷን ዝቅ አድርጋ የትህትናዋ ምሳሌ ስለሆነ ነው ከላይ ወደ ታች ሚጀመረው።
==============
✔“ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፥ ራሱንም የሚያዋርድ ሁሉ ከፍ ይላል” - የማት ወን23፣12
• የበእንት ፍጻሜ ወደላይ የሚያልቀው ሚስጢሩ እመቤታችን በመቃብር አልቆየችም ወደላይ አረገች ማለት ነው።
✔ “ አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት”- መዝ 132፡8
✔ ስንዱዋ እመቤት ቅድስት ቤተክርስቲያን ማንኛውም ነገር ያለ ትርጉም አታደርግም።
http://www.tg-me.com/us/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
BY ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
![](https://photo.tg-me.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/RV_vF79ZyGynO0xSTrBuQMZ5Rj1-tEZ9RIdcJGT3iXg0aO_rNjX3BtB1JB01O_JZrFyCTvAeQanrdc_d89k7XhPt7fyHzg7uUMZ5HJSjqZQc4dseNfi6enOzVKCEPV6BTApTePLJcxY27R9cSPiVFu_AjdxqP_RdXU020O8OzLGnhoTwkfzS5aSvtIciB6umf8iMisXXoPQ-ltbNmgznXVSkvtEic1slAGUpuQdPbr4DbgPVmCqWyCmBvk43Twy-vrt_mJuFPubWVohiKCwL8_zX24W9DFv91xkyXtv-gmP6_t6qaneK9mnBVf1DAo-dp90oxpsZqNetQwjQO91DWA.jpg)
Share with your friend now:
tg-me.com/ortodoxtewahedo/21777