tg-me.com/Islam_and_Science/6291
Last Update:
>>>>>>>>>>>>>> #ዉዱዕ<<<<<<<<<<<<
✍ አሚር ሰይድ
ሁላችንም ብንሆን በቀጥታ ከፈጣሪያችን ጋር ወደምንገናኝበት የሶላት አምልኮ ከመሄዳችን በፊት የተሟላ ዉዱእ ማድረግ ግዴታችን ነው፡፡ ይህን ጉዳይ ቸል ማለት ወይም እንደነገሩ መያዝ በዋነኛው የአምልኮ ተግባር (በሶላታችን) ላይ አፍራሽ ተፅእኖ ይኖረዋል፡፡
⚡️⚡️⚡️ አንድ ጊዜ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ የሱብሂን ሶላት እየሰገዱ ነበር፡፡ የሩምን ምዕራፍ እያነበቡ ሳሉ የተወሰነ ቦታ ላይ ተሳሳቱ፡፡ ሶላቱ እንደተጠናቀቀም ወደ ሰጋጆቹ ፊታቸውን አዙረው እንዲህ አሉ፡-
“አንዳንድ ሰዎች ዉዱእ ሳይኖራቸው ወደ መስጊድ ይመጣሉ፡፡ ይህም ሰይጣን በምናነበው የቁርአን አንቀፅ ላይ ተፅዕኖ እንዲያደርግ በር ይከፍታል፡፡ ወደ መስጊድ ስትመጡ የቻላችሁትን ያክል ተጠንቅቃችሁ ዉዱእ አድርጉ፡፡"አሉ
ስለዚህም አካልን መታጠብና የተሟላ ዉዱእ ማድረግ ሶላታችን ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ መውሰድ የሚገባን ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡
>>>>> በተጨማሪም አንድ ሰው የቻለውን ያክል ዉዱእ ያለው ቢሆን ይህ ታላቅ የሆነ ፀጋ ነው፡፡ የአላህ መልዕክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ሁሉንም ሥራቸውን ዉዱእ ያላቸው ሆነው መፈፀም ይመርጡና ይወዱም ነበር፡፡
⚡️⚡️⚡️ አቡ ጁሃይም (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ አንድ ጊዜ ከጀመል ግምብ በኩል ሲመጡ አንድ ሰው አገኛቸውና ሰላምታ አቀረበላቸው፡፡ እርሳቸው ግን ለሰላምታው አፀፋ አልመለሱለትም ነበር፡፡ ሰውየው ወዲያው ወደ ግምቡ በመሄድ በመዳፎቹ ግድግዳውን ከመታ በኋላ እጆቹንና ፊቱን በማበስ (ተየሙም በማድረግ) ተመልሶ መጣና ሰላምታ አቀረበላቸው፡፡ እሳቸውም ለሰላምታው አፀፋውን መለሱ፡፡ በዚህ ድርጊታቸው ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ
ያስተላለፉት መልዕክት አንድ ሰው ምን ጊዜም ቢሆን ዉዱእ ያለው ሆኖ መንቀሳቀስ እንዳለበት ነው: ይህም ማንም ቢሆን የሚሰራውን ስራ ...ያ ሥራ የግዴታ ባይሆ እንኳን ዉዱዕ ካደረገ በኋላ ቢጀምረው ትሩፋቱ የበለጠ እንደሚሆን ያሳያል፡፡
⚡️⚡️⚡️በአንዳንድ ዘገባዎች መሰረት የአላህ መልዕክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ትጥበት በወጀበባቸዉ ጊዜ በግድግዳ ላይ መዳፎቻቸውን በማኖር ተየሙም ያደርጋሉ፡፡ ይህንም ያደርጉ የነበረው ዋናውን ትጥበት ከመፈፀማችው በፊት ያለ ዉዱእ እንዳይሆኑ በመፍራት ነው::(ሀይሰሚ ዘግበዉታል)
💚 የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ይህን በመሰለ ሁኔታ ነበር ሕዝባቸዉን አካላዊና መንፈሳዊ ንፅህናውን እንዲጠብቅ ያስተምሩት የነበረው፡፡
✏️✏️ አንድ ዕለት የአላህ መልዕክተኛ ሀቢቡና
ሙሀመድﷺ💚 ከባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ወደ አንድ የመቃብር ስፍራ ሄዱ፡፡ ከዚያም እንዲህ በማለት ለሙታን ዱዓ አደረጉ፡-
"እናንተ በዚህ ቦታ የሰፈራችሁ ምእመናን ሆይ! የአላህ ሰላምታ በእናንተ ላይ ይሁን፡፡ በአላህ ፈቃድ እኛም አንድ ቀን እንቀላቀላችኋለን። ወንድሞቼን ለማየት እንዴት ፈልጌያለሁ! እንዴት ነው የናፈቁኝ!”
"እኛ የእርስዎ ወንድሞች አይደለንምን?" በማለት ባልደረቦቻቸውጠየቋቸው፡፡
... እርሳቸውም እንዲህ አሉ፡- “እናንተ ባልደረቦቼ ናችሁ፡፡ ወንድሞቼ እነዚያ ገና ወደዚህች ዓለም ያልመጡት ናቸው፡፡''
ባልደረቦቻቸው አሁንም ጠየቁ፡-
“የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ገና ወደዚህ ዓለም ያልመጡ የሆኑትን ሰዎች ከሕዝቦችዎ ውስጥ እንዴት ለይተው ያውቋቸዋል?'
....ነቢዩ ሙሀመድ ﷺሲመልሱ እንዲህ አሉ፡-
ግምባሩና እግሩ ንፁህ ነጭ የሆነ ፈረስ ያለው ሰው አስቡ፡፡ ይህ ሰው ይህን ፈረሱን ከመንጋ ሙሉ ጥቁር ፈረሶች መካከል ሊለየው አይችልምን?"
በሚገባ ይለየዋል እንጂ የአላህ መልዕክተኛ" በማለት ተከታዮቻቸው መለሱ፡፡ የአላህ ነቢይና የተባረኩት መልዕክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ አሉ:-
እነዚያ ወንድሞቼ ፊታቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸው በሚያደርጉት ዉዱእ ምክንያት እያበሩ ወደእኔ ይመጣሉ፡፡ እኔ ደግሞ በሀውዴ ላይሆኜ የሚፈልጉትን ነገር ልስጣቸው እጠብቃቸዋለሁ። ሆኖም ግን ተጠንቀቁ! ከመንጋው ውስጥ በጥባጭ የሆነ ግመል እየተደበደበ ራቅ ተደርጐ እንደሚባረረው ሁሉ የተወሰኑ ሰዎች ከሀውዴ ይባረራሉ፡፡
....እኔም እንዲህ እያልኩ እጠራቸዋለሁ፡- 'ኑ ወደዚህ! እነርሱ የእኔ ሕዝቦች ናቸው' በዚህ ጊዜ እንዲህ እባላለሁ- 'ከአንተ በኋላ ብዙ ነገሮችን ቀይረዋል፡፡ ያንተን ሱና ትተው የጥመትን መንገድ ተከትለዋል
.... እኔም ይህን እንደሰማሁ እንዲህ እላለሁ፡-
'ከእኔ አርቁልኝ! ከእኔ አርቁልኝ!' " ሙስሊም ዘግበዉታል
🔰ከዚህ በመጠኑ ዘለግ ያለ ሐዲስ ምን ተማርን? አዎን! እነዚያ ዉዱአቸውን አሳምረው የሚያደርጉ የአላህንና የመልዕክተኛዉን ﷺ ውዴታ የሚያገኙ ሲሆን እርሳቸውም ወንድሞቼ' በሚል የቀረቤታ አጠራር ጠርተዋቸዋል፡፡
ከእርሳቸው ሀውድ መራቅና መባረር ምንኛ እድለቢስነት ነው! ምንኛ አዋራጅ ሁኔታ ነው! እርሳቸውም ከእኔ አርቁልኝ' ብለው የመሰከሩበት ሰዉ ከዚያ ቡሀላ ምን እጣ ነዉ የሚገጥመዉ??አሏህ ይህን ከመሰለ ጥፋትና አደጋ ይሰዉረን!!!
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
BY ISLAMIC SCHOOL
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283
Share with your friend now:
tg-me.com/Islam_and_Science/6291