Telegram Group & Telegram Channel
ከአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም የተሰጠ      አስቸኳይ መግለጫ

ሕገ መንገስቱ ሕገ አራዊት ካልሆነ ሕግ ይከበር !
አንድ የሆነን ማሕበረሰብ ወይም አካል አንድ ሁኑ ማለት ይከብዳል፡፡ ምንአልባትም የተሻለ ሊሆን የሚችለው የበለጠ አንድ ሁኑ ማለት ሳይሻል አይቀርም፡፡ በመሰረቱ፣አንድ እንሁን ያልነው አንድ የመሆን ተፈጥሯዊ ማንነታችን ስለሚፈቅድ ነው፡፡

መገለጫችን ስለሆነና ስለምንችል እንዲሁም አንድ መሆን ማለት የግዴታ አንድ አይነት ማለትም አይደለም፡፡  ‹‹ አንድ እንሁን ›› ያልነው አንድ አለመሆናችን ያስከተለውን፤ያስከፈለንን እና የሚስከፍለንን ከባድ ዋጋ ጠንቅቀን ስለምናውቅ ነው ፡፡ የአማራ ፋኖ ፣ የአማራ ሕዝባዊ ማሕበራት ፎረም እንዲሁም መላው የአማራ ሕዝብ ፈጽሞ ከማይደራደርባቸው ቁልፍ አበይት ጉዳዮች አንዱ አምሓራዊ አንድነቱ ነው፡፡

ዛሬም እንደ ትናንቱ እኛ አምሓራዊያን ከኢትዮጵያዊነት ሊያወርዱን አማሓራዊነታችን በታትነው እንደ አናሳ ብሔረሰብ ሊሳንስኑን ለሚመጡ የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ጠላቶች ረመጥ እሳት ነን፡፡  የነጻነት ታጋይን ልታስር ትችላለህ እንጅ ነጻነትን አታስርም ፤ ታጋይን ልትገድል ትችላለህ እንጅ ዓላማን የሰነቀ ትግል ሕያው ሆኖ ስለሚቀጥል ትግል አይሞትም፡፡

ዛሬ ታላቁ የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያን ከፊት በማስቀደሙና ዲሞክራሲያዊ የአምሓራዊ ብሔርተኝነቱን በማስቀደሙ ብቻ ለዘርፈ ብዙ ስቃይና መከራ ተዳርጓል፡፡ ይህ ደግሞ ሊያበቃ ይገባል እያልን አሁናዊ የሀገሪቱን ሁኔታ በጥልቅ በመረዳት የሚከተለውን መግለጫ አውጥተናል፡፡ ሰጠናል፡፡

ከምክክር ኮሚሽን አንጻር የምናነሳቸው ጥያቄዎች፤-

1ኛ. የአምሓራ ሕዝብ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ በሆነበት ሰዐት እና የአምሓራ ሕዝብ በጦርነት ላይ በሚገኝበትና አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት በአልተደረገበት ሁኔታ
2ኛ. በሕዝብ ጥያቄ የተያዙ ምሁራንና አጀንዳ ቀረጻ ላይ የሚሣተፉ ፖለቲከኞች ፣ ጋዜጠኞችና ወጣቶች በታሰሩበት ሑኔታ እንዲሁም  በሲቪልና ወታደራዊ ተቋማት ያሉ ምሁር አምሓራዊያን በማንነታቸው ምክንያት እየተገፉና እየተሳደዱ በሚገኙበት ሁኔታ

3ኛ. በሃገረ መንግሥት ግንባታ የላቀ ሚና በሚጫወቱ የእምነት ተቋማት ላይ ለአብነትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እንደ አምሓራ ሕዝብ ስቃይና መከራ ስደት እየተቀበለችበት ባለችበት ሰዐት እና በሃገራዊ አጀንዳ ተሳታፊ እንዳትሆን በተደረጉበት ወቅት

4ኛ. አጀንዳ ቀረጻ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ ሁሉም የመገናኛ ዘዴዎች ዝግ በተደረጉበት ሁኔታ ከዚህ በተጨማሪም  መዋቅራዊ ተሳትፎ የሚደረግበት ምንም አይነት አደረጃጀት እና ተዋረድ በሌለበት ሁኔታ

5ኛ. ነጻ እና ገለልተኛ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶችን በአገለለ ሁኔታ እና አዲስ አበባ ጨምሮ ሁሉም ክልሎች የሚኖሩ የአምሓራ ተወላጆችን አካታች እና አሳታፊ ባላደረገ መልኩ የተካሄደው የምክክር ሒደት

6ኛ. ሁሉም የተቃዋሚ ፖርቲዎች በአልተሳተፉበትና ከምክክሩ በተገለሉበት ሁኔታ

7ኛ. የአማሓራ ሕዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዳይመለሱ ክተት አዋጅ በታወጀበት ሰዐት የትኛዋ ኢትዮጵያ ናት ስትመክር የነበረችው እያልን ጥያቄችን እያቀረብን ከሐገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ጋር የነበረን ሒደት እና ስለ ኮሚሽኑ አሰራርና ግልጸኝነት በቀጣይ ራሱን በቻለ መግለጫ ለመላው የአማራ ህዝብና ለኢትዮጵያዊያን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

            ስለሆነም 

አስቸካይ ጊዜ አዋጅ ከመጠናቀቁ አንጻር ያለን አቋም ፤-
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረውና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈጻሚነት ተጠናቋል፡፡

  በዚህ መሠረትም

1ኛ. በአዋጁ አተገባበር ዐውድ ውስጥ የቆዩ በመላው የሀገሪቱ ክፍሎች በማንነታቸው ብቻ የታፈኑ እና ለስቃይ የተዳረጉ የህሊና እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ

2ኛ. በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎችና በመላው አምሓራዊያን ላይ የተጣለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከአሁን በኃላ በሕገ መንግስቱ መሠረት ተቀባይነት ስለሌለው ለሕገ መንግስቱ ስርዓት መከበር ‹‹ ሕግ እያስከበር ›› ነው የሚሉ አካላት የሚፈጽሙት የኮማንድ ፖስት ተግባር ሁሉ ሕገ - አራዊት መሆኑን እንድታውቁት

3ኛ. በክልሉ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ፈርሶ የክልሉ ሕዝብ በነጻነት ከሰዐት እላፊ ገደብ ወጥቶ ሠላማዊ ኑሮውን የሚመራበት ምቹ ሁኔታዎች ለመፍጠር ሁሉም አካል የጋራ ተሳትፎና ርብርብ እንዲያደርግ

4ኛ. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ምክንያት በጦርነቱ የተጎዱ አምሓራዊያን ለማቋቋምና ለማገዝ ሁሉም በየአካባቢው የድርሻውን እንዲወጣ እንዲሁም አርምሞ ላይ የነበራችሁ በአምሓራዊያን ስም የተደራጃችሁ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች የተቋቋማችሁበትን ዓላማ ትልቁ ፍጡር ሰው ከሌለ እናተም የላችሁምና ሰውን ለማዳን በምናደርገው ርብርብ ከጎናችን እንድትቆሙ እየጠይቅን

5ኛ. ‹‹ አንድ ሁኑ ! ›› ወዳዳችሁም ጠላችሁም አምሓራዊያን አንድ ሁነናል ፡፡ ቃሉም በተግባር ተፈጽሟል ፡፡ ወንድም እህቶቻችን ፤ አባት እናቶቻችን የሆናችሁ አምሓራዊ በሁለት ጎራ ተከፍላችሁ የቤተሰብ ጦርነት የከፈታችሁ ወገኖች የጠላት መሳቂና መሳለቂያ ሳንሆን አንድ እንሁን፡፡ ጊዜው የአንድነት ሀይሎች የአሸናፊነት ዘመን እያልን

ለተከበርከው የትግራይ ህዝብ፤-  በተሳሳተ የ50 ዓመት የፖለቲካ ታሪክና ትርክ በመርዝ በተለወሰ ሴራ ከወንድም የትግራይ ሕዝብ ጋር ተዋጋን፡፡ የትግራይ ሕዝብና አምሓራዊያን ምን አተረፍን ? 1 ሚሊየን በላይ አምራች ክብር የሆነውን ሰው አጣን ፤ በመቶሽዎች አካላቸው ጉደለ ፤ በትሪሊየን የሚቆጠር ሀብት ወደመ ሕዝብ ተጎዳ የፖለቲካ ቁማርተኞች ግን እስከ ከራባታቸው በሐሴትና በደስታ አሉ፡፡

ስለዚህ የእኛን ደስታ የነጠቁ ቁማርተኞች ወደ ጎን በመተው ሕዝብ ለሕዝብ ወዳጅነታችን እናጠናክር ዘንድ በጋራ እንድንሰራ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የተከበርከው የኦሮሚያ ሕዝብ ፤- በኦሮማራ ሴራ ሳይገባን በቅንነት የኦሮሞ ደም የእኔም ደም ነው ብለን ጎንደር ላይ መስዋዕትነት ከፍለናል ፡፡ እናተም ጣና ኬኛ ብላችሁ በአምሓራዊያን መዲና ባህርዳር የጣና እንቦጭን አረም አርማችዋል ፡፡

የሚያምርብን ይህ ነው፡፡ እኛ አልተጣላንም ፡፡ አንጣላም ፡፡ የጋራ እንቦጭ አረም ለማረም ግን ዛሬም የኦሮሞና አምሓራዊነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆናችን በተግባር እንድናሳይ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ለተከበራችሁ ወንድም የሌሎች ክልል ህዝቦች፤- አምሓራ ከማስተዋል፣ ጥበብን ከእውቀት፣ፈሪያ እግዚአብሔርን ፣ከሀገር ፍቅር ጋር አስተባብሮ የረቀቀ ሕዝባዊነት መገለጫ ነው፡፡ አምሓራነት ከመለያየት አንድነትን፤ከባርነት ነጻነትን ፤ ከውርደት ሞትን ፤ከመግፋት መገፋትን የሚል የአስተዋይ ሕዝብ ስነልቦናዊ ውቅር አናጭ ማንነት በመሆኑ በልዩነት ውበትን በመፍጠር ለዘመናት ከብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተጋብቶ፣ተዋልዶና ተዋዶ ኑራል ፡፡

ዛሬም ለወደፊቱም ይኖራል፡፡ በመሆኑም አብሮነታችን የጋራ መገለጫችን ነውና አብሮነታችን በጽኑ መሰረት ላይ እንድናስቀጥል በአምሓራዊያን ስም እንጠይቃለን፡፡

ሕዝብን ማሸነፍ አይቻልም ! ሰኔ 1 /2016 ዓ.ም                            ባህርዳር

tg-me.com/Asrat_News/12873
Create:
Last Update:

BY አሥራት ሚዲያ Asrat Media ®🇪🇹

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/Asrat_News/12873

View MORE
Open in Telegram

አሥራት ሚዲያ Asrat Media ® Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Dump Scam in Leaked Telegram Chat

A leaked Telegram discussion by 50 so-called crypto influencers has exposed the extraordinary steps they take in order to profit on the back off unsuspecting defi investors. According to a leaked screenshot of the chat, an elaborate plan to defraud defi investors using the worthless “$Few” tokens had been hatched. $Few tokens would be airdropped to some of the influencers who in turn promoted these to unsuspecting followers on Twitter.

That growth environment will include rising inflation and interest rates. Those upward shifts naturally accompany healthy growth periods as the demand for resources, products and services rise. Importantly, the Federal Reserve has laid out the rationale for not interfering with that natural growth transition.It's not exactly a fad, but there is a widespread willingness to pay up for a growth story. Classic fundamental analysis takes a back seat. Even negative earnings are ignored. In fact, positive earnings seem to be a limiting measure, producing the question, "Is that all you've got?" The preference is a vision of untold riches when the exciting story plays out as expected.

አሥራት ሚዲያ Asrat Media ® from us

Telegram አሥራት ሚዲያ Asrat Media ®🇪🇹
FROM USA