Telegram Group Search
Forwarded from Girum Sebsibe
Forwarded from Girum Sebsibe
ከአ- ጥበባት በሙሉ ክብሩ ሥራ ጀምሯል። እንኳን ደስ አለን።
ከአ- ጥበባት በሙሉ ክብሩ ተከፍቷል። እንኳን ደስ አላችሁ። ቦታው ከሃያ ሁለት ወደ ኢድናሞል በሚወስደው መንገድ አደይ አበባ ሰቴዲዮም( ቦሌ) ፊት ለፊት ንግድ ባንክ የሚገኝበት ህነጻ።
Forwarded from Mezagebt Net
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Addmesh አድሜሽ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በቅድሚያ ከአ- ጥበባት በአሜሪካን ሀገር ምርቶቹን ለመሸጥ የሚያስችለውን ፍቃድ በማግኘቱ እንኳን ደስ አለን፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
በአድሜሽ ሥርዓት በኩል በያዝነው አውድ ወይም ዘጠና አንድ ቀን ውስጥ ከተሰሩት ታላላቅ ስራዎች መካከል ትልቁን ድርሻ የሚይዘው የከአ-ጥበባት መመስርት ነው፡፡ ከአ-ጥበባት በአዲስ አበባ በመጪው ጊዜያትም ይሁን አሁን በአለንበት ሁኔታ ለንግድ ሥራ አመቺ ከሚባሉት ስፍራዎች አንዱ በሆነው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወይም አዲሱ ስቴዲዮም ፊት ለፊት በ260 ካሬ ስፍራ ላይ የመሸጫና የማምረቻ ፍቃድ አወጥቶ ሥራ ጀምሯል፡፡
ከአ-ጥበባትን መክፈት ያስፈለገበት ዋና ጉዳይ በብዙዎች እንደተለመደው የንግድ አሰራር ሂደት ሱቅ ከፍቶ ገንዘብ የመሰብሰብ ዓለማ የያዘ አይደለም፡፡ ብዙዎቻችን እንደምናውቀውና እንደምንናገረው እኛ ኢትዮጵያዊያን የቀደምት ስልጣኔዎች ባለቤቶች ነን፡፡ ነገር ግን አሁን ስለእነዚህ ስልጣኔዎች ከመናገር ባለፈ ሰርተን ለማሳየት የሚያስችል አቅም ግን አልታደልንም፡፡ ግን ይህ ለምን ሊሆን ቻለ? ለእዚህ ጥያቄ መልስ የተለያዩ ምክንያቶችን ብንደረድር መልስ ሊሆነን አይችልም፡፡ ለእኛ አጥጋቢ መልስ ሊሆን የሚችለው በእውነት ይህንን ጥበባችንን ገልጠን ማምጣት ስንችል ብቻ ነው፡፡
አድሜሽ ሥርዓተ መዋቅር በእዚህ በኩል ያለውን ሂደት በእውነት ገልጦ ለማምጣት እንዲያስችለው በመጀመርያ ላይ ከአ-ጥበባትን በአዲስ አበባ ላይ እንዲከፈትና ወደ ስራ እንዲገባ አደረገ፡፡ ከእዚህ ጋር በማያያዝም ይህንን ሀሳብ ወደ ተግባር ለመለውጥ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማግኘት እንዲችል ከሀገር ውጪ ማለትም በኢንግሊዝ ሀገር ህጋዊ በሆነ መንገድ አቦል ማይክሮ ፋይናንስን ከፈተ፡፡ ይህም አሁን ያለበትን የገንዘብ ችግርን ከመፍታት ባሻገር በዓለማቀፍ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የፋይናንስ መስመር ለመቆጣጠር የሚያስችል አመቺ ሁኔታዎችን ይፈጥርለታል፡፡ ከእዚህ በመቀጥል በመላው አሜሪካ ምርቶቹን መሸጥ የሚያስችለውን ወይም የከአ-ጥበባት አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሊሆነው የሚችለውን የንግድ ፍቃድ በአሜሪካን አገር አወጣ፡፡ እንግዲህ በአለፉት ዘጠና አንድ ቀናት ወስጥ አድሜሽ ሥርዓተ መዋቅር እጅግ አስቸጋሪ የሚባሉ ታላላቅ ተቋማትን በአጭር ጊዜ ውስጥ በእዚህ ሁኔታ ለመመስረት በቃ፡፡
አድሜሽ ሥርዓተ መዋቅር በቀጣዩ አውድ ወይም በመጪዎቹ ዘጠና አንድ ቀናት ውስጥ እነዚህን ተቋማት እርስ በእርስ የማስተሳሰር እንዲሁም ተጨማሪ የማምረቻ ፋብሪካዎችን የመገንባት ሂደቱን የሚዘረጋ ይሆናል፡፡ አቦል ማይክሮ ፋይናንስ በመጪው ሳምንት ዓለማቀፍ ከሆኑ ገንዘብ አበዳሪ ተቋማት ጋር መነሻ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት ድርድሮችን የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ሲቀጥልም የድርድሩ ሂደት የተሳካ ከሆነ ከእነዚህ ተቋማት የተገኘው ገንዘብ ሀገር ውስጥ ከሚገኙ የገንዘብ ተቋማት ወይም በሀገራችን ህግ መሰረት የተገኘው ገንዘብ ለከአ- ጥበባት /ኢትዮጵያ/ እንዲደርሰው ያደርጋል፡፡ ሲቀጥልም ከአ-ጥበባት /ኢትዮጵያ/ በሀገሪቱ ህግ መሰረት ተመንዝሮ በአገኘው ገንዘብ እሱ ያመረታቸውን እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የጥበብ ስራዎች ማለትም የሸክላ ስራዎች፣ ባህላዊ አልባሳት፣ ከዕጽዋት የተገኙ ባህላዊ መድሃኒቶችን፣ በቆዳ እንዲሁም በተለያዩ መአድናት የተሰሩና የተቅረጹ ስዕሎች፣ ምልክቶችና ጠልሰሞችን እንዲሁም በሳር የተሰሩ ስፊቶችን/ ሰፊድ፣ እንቅብ፣ አገልግል…/ በቀጥታ ከአማራቾች ላይ በመግዛት የሀገራችንን ህግ በሚፈቅደው መሰረት ወደ አሜሪካን ከአ- ጥበባት ይልካቸዋል፡፡ ከአ-ጥበባት አሜሪካም እነዚህን ምርቶች ተቀብሎ በመላው አሜሪካ ሲቀጥም በአውሮፓ ገበያ ላይ እንዲሸጡ ያደርጋል፡፡ ከእዚህ ሽያጭ በሚያገኘው ገንዘብ አቦል ማይክሮ ፍይናነስ ከዓለማቀፍ አበዳሪ ድርጅቶች የተበደረው ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ በእዚህም ሂደት ጥበባችን፣ እነዚህን የጥበብ ስራዎችን በብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው በማምረት ላይ ያሉ ግለሰቦች፣ ሀገር እንዲሁም ዓለማቀፍ ተቋማት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በቀጣይም ይህ ሂደት መሰረቱን እያሰፋ በመምጣት በምስራቅ አፍሪካ ሲቀጥልም በአፍሪካ ደረጃ ትልቅ ለውጦችን የሚያመጣ ይሆናል፡፡
እንግዲህ በአለፉት ዘጠና አንድ ቀናት ያለፍናቸው መንገዶች እነዚህ ናቸው፡፡ በእርግጥ እኛም ደጋግመን እንደምንናገረው ምንም እንኳን ጅማሪያችን ትንሽ ቢሆንም ፍጻሚያችን ግን ታላቅ እንደሚሆን ጥርጥር የለንም፣ ወይም ምንም ያህል ዛሬ ባለን እኛነታችን ታይተን ደካማና ደሆች ብንመስልም ነገ ላይ ግን ብዙዎችን ጠንካሮችና ባለጸጎች እናደርጋለን፡፡
2024/06/24 17:04:24
Back to Top
HTML Embed Code: