Telegram Group Search
"መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡"
ቅዱስ ሲኖዶስ

@ortodoxtewahedo
✤✤✤ #ሐምሌ_ቅድስት_ሥላሴ
ቅድስት ቀደሰ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣና ትርጕሙም ልዩ ማለት ሲኾን የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ልዩ (የሥላሴን አንድነትና ሦስትነትን የሚመስል ስለሌለ፤ ቢመስልም ምሳሌ ዘየኀጽጽ) ስለኾነ ሥላሴን ቅድስት በሚል ቅጽል እንጠራለን፡፡

#ሐምሌ_7_ቀን_ቅድስት_ሥላሴ_ለአብርሃም_የተገለጹበት_ነው፡፡ ይኸውም ስለ ፫ት ምክንያቶች ነው፤
#፩ኛ) ለመልካም ነገር /በአብርሃም አንግዳ መቀበል ፀር የኾነ ሰይጣንን ለማሳፈር/ (ሰይጣን በምቀኝነት አብርሃም እንግዳ እንዳይቀበል የውሸቱን ወደ አብርሃም ቤት በሚወስድ መንገድ ላይ ግንባሩን ገምሶ፥ ደሙን አፍስሶ ሰዎች አብርሃም እንዲህ መጥፎ ነውን እንዲሉና እንግዶች ወደ ቤቱ ሂደው እንዳይስተናገዱ አድርጓል፤ አብርሃምም ለ3 ቀናት እንግዳ እየጠበቀ ጾሙን ውሎ ነበር፡፡ ይህን የሰይጣን ክፋት የአብርሃምን እምነትና እንግዳ መቀበል የተመለከቱ ፥ ምግብን የማይመገቡ ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው እሳት ቅቤን እንደሚበላ ተስተናግደዋልና ነው፡፡ መስተናገዳቸውንም መምህረ ጋሥጫ የኾነው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ እንዲህ በግጥም አስቀምጦታል፤
ለንግሥክሙ ሰገደ አብርሃም በርእሱ፡፡
ቤተ ገብርክሙ እንዘ ይብል ገሐሡ፤
አጋዕዝትየ ዘትሤለሱ ግናይ ለክሙ፡፡
እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባው አምላካችንም ኾነ ቅዱሳን መላእክት ለአብርሃምና ለሌሎችም ቅዱሳን በተለያየ አምሳል መገለጻቸውን ልብ ይሏል፡፡ ለአብነትም፤
፠ ለአብርሃም በአምሳለ አረጋዊ፤
፠ ለሕዝቅኤል በዘባነ ኪሩብ፤
፠ ለዳንኤል በአረጋዊ፣
፠ ለዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ በተለያየ አምሳል፤
፠ ለደብረ መጕናው (ሞጊና) ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን አቡነ አብሳዲ ደግሞ ራሱ መድኀኔዓለም ተገልጾላቸውና ተቀብለውት እንደ አብርሃም እግሩን ያጠቡት መኾኑን ልብ ይሏል፡፡

#፪ኛ) ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ፥ እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛልሃለሁ ያሉት ሥላሴ ቃሉ የማይታበይ መኾኑን ለማሳየት (ሰማይና ምድር ያልፋል ፥ ቃሌ ግን አያልፍም ብሎ በኋለኛው ዘመን ጌታችንም እንዳረጋገጠው)፤ ለአብርሃምና ለሣራ ልጅ ሊሰጧቸው፡፡ አባታችን አብርሃም 99 ዓመት ፥ እናታችን ሣራ 89 ዓመት መልቷቸውና የመውለጃ ጊዜያቸው ባለፈበት ሰዐት እንደሚወልዱ ለማብሰር፡፡

#፫ኛ) ምግብ ተመግበን ካበቃን በኋላ አምላካችንን ማመሰገን እንደሚገባን ለማስተማር፡፡ (የታረደው ወይፈንም በተዓምራት ተነሥቶ ስብሐት ብሎ አመሰግኗል፤ ይህንንም መምህረ ጋሥጫ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በመልክአ ሕማማት ድርሰቱ በግጥም እንዲህ አስቀምጦታል፤
ድኅረ በላዕክሙ ላሕመ እንበይነ ፍቅረ ሰብእ ፍጹም ፤
ዘበኀይልሙ ሐይወ ላሕም፤
ሥላሴ ክቡራነ ስም፡፡ ግናይ ለክሙ፡፡

@ortodoxtewahedo
#ሐምሌ_7_የቤተ_ክርስቲያን_ማኅቶት#አፈ_በረከት_ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ#ወልዱ_ለአቡነ_በጸሎተ_ሚካኤል_ልደቱና_እረፍቱ_ነው፡፡
ዕረፍቱ የኾነው በሐምሌ 7 (6,705 ዓመተ ዓለም፥ በ2ት እንድቅትዮን፥ በአልቦ አበቅቴ፥ በ7ት ጥንተ ዮን፥ በወንጌላዊው ማቴዎስ ዘመን በዕለተ ረቡዕ) ነው፡፡ ያረፈውም በአፄ ይስሐቅ ጥያቄ የጋራ መናገሻ መድኀኔ ዓለም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ባርኮ ሲመለስ በደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ሲኾን ፤ አርድዕቱ ሥጋውን ይዘው ሂደው በአባቱ መካን በደብረ ጎል (አሁን በደብረ ባሕርይ) አሳርፈውታል፡፡
፠ይህ አባት ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ፤ ጸሓፊ፥ ቅዱስና ጻድቅ፥ ፈላስፋና ደራሲ፥ መናኝና ባሕታዊ፥ ሊቅና ተመራማሪ፥ ገጣሚና በለቅኔ፥ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፤ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፤
፠ዳግማዊ ቄርሎስ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ)፥
፠ ዐምደ ሃይማኖት
፠ ዳግማይ ቅዱስ ያሬድ፤
፠ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ፤
፠ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት፥
፠ አፈ በረከት
፠ የከሃድያን ዘላፊ፥ የቅዱሳን ፀሐይ …….ተብሏል

ከ40 በላይ ድርሰቶቹ መካከል በአብዛኞቻችን ዘንድ የሚታወቁት 34ቶቹ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፤
1. ✼ ኆኀተ ብርሃን
2. ✼ መዝሙረ ኢየሱስ (ሰላመ ማርያም)
3. ✼ መዝሙረ ድንግል
4. ✼ የማርያም የምስጋና ሰላምታ
5. ✼ ውዳሴ መላእክት
6. ✼ ውዳሴ ነቢያት
7. ✼ ውዳሴ ሐዋርያት
8. ✼ ውዳሴ ሰማዕታት
9. ✼ ውዳሴ ጻድቃን
10. ✼ መጽሐፈ ብርሃን
11. ✼ መጽሐፈ ምሥጢር
12. ✼ መጽሐፈ ሰዐታት ዘመዓልት ወዘሌሊት
13. ✼ መጽሐፈ አርጋኖን
14. ✼ አርጋኖነ ውዳሴ
15. ✼ መሰንቆ መዝሙር
16. ✼ እንዚራ ስብሐት
17. ✼ ውዳሴ መስቀል
18. ✼ ፍካሬ ሃይማኖት
19. ✼ ፍካሬ ሐዋርያት
20. ✼ መጻሕፍተ ቅዳሴያት
21. ✼ ቅዳሴ እግዚእ ካልዕ
22. ✼ መዐዛ ቅዳሴ
23. ✼ ሕይወታ ለማርያም (ሕይወተ ማርያም)
24. ✼ ውዳሴ ስብሐት
25. ✼ ውዳሴ ማርያም ካልዕ
26. ✼ ውዳሴ ስብሐት ወሰላምታ
27. ✼ ማኅሌት ዘነቢያት ወዘሐዋርያት
28. ✼ የሰባቱ ጊዜያት ጸሎት (መልክአ ሕማማት)
29. ✼ ጸሎተ ፈትቶ (ጸሎተ ማዕድ)
30. ✼ ጸሎት ዘ(ቤት)ውስተ ቤት
31. ✼ መልክአ ቊርባን
32. ✼ ተአምኆ ቅዱሳን
33. ✼ ተአምኆታ ለእግዝእትነ ማርያም
34. ✼ ክብረ ቅዱሳን

(በፎቶ ላይ የምታዩት ገዳም፤ በዓለም ብቸኛው የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ገዳም የኾነው ደብረ ባሕርይ ነው፡፡ የቦታው አቀማመጥ እጅግ በጣም ማራኪና እንደ ደብረ ዳሞ ሲሆን የሚወጣው በመሰላል ነው፡፡)፤ ገዳሙ የሚገኘው #በደቡብ_ወሎ_በቦረና_አውራጃ ነው፡፡

(አስተጋባኢ /ይህንን ጽሑፍ ከአባቶች በመጠየቅ ፥ መጻሕፍትን በማንበብ ፥ ከታላቁ ገዳም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫ ድረስ ሂዶ ያዘጋጀው የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ነው/፡፡)
አምላከ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የሀበነ በረከተ ወረድኤወረድኤተ

@ortodoxtewahedo
"+ እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም #ሥላሴ አመታዊ በዓል አደረሳቹ

"+ #ሥሉስ_ቅዱስ +"

=>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት)
የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር ነው:: #አብ : #ወልድ : #መንፈስ_ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና::

+ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " #ቅድስት_ሥላሴ " እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው
ያድራሉ::

+ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን #ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል::

+አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት::

#ቅድስት_ሣራ ሳቀች::እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው " #ይስሐቅ" የተባለው::

+ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና::

=>የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና
አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን::

"+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ:- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: +

"+ (ዕብ.6:13)

"+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+
(ቆሮ. 13:)


@ortodoxtewahedo
Audio
አንደበቱ ተከፈተ ||የሰው ተከታይ አትሁኑ
        
Size:-22.6MB
Length:-1:04:53

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
😱 የስልኮትን የመጨረሻ ቁጥር ብቻ በመንካት  በሚደርሳቹ ነገር ደስታን ይቋጥሩ ቁጥር መደጋገም አይቻልም 🙈
2024/07/18 05:01:25
Back to Top
HTML Embed Code: