Telegram Group Search
TIKVAH-MAGAZINE
በኢትዮጵያ በኩንታል 2 ሚሊዮን ብር የሚሸጥ አልጌ ለማምረት የመስክ ሙከራ እየተደረገ ነው ተባለ። ኢትዮጵያ በኪሎ 20 ሺሕ ብር በኩንታል ደግሞ እስከ 2 ሚሊየን ብር የሚሸጥ ዋቅላሚ (አልጌ) በስፋት ለማምረት የመስክ ሙከራ እየተደረገ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከሰሞኑ ባዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ መገለፁን አዲስ ዋልታ ዘግቧል። የዚህ ደቂቅ ህዋስ ሳይንሳዊ አጠራር ስፓሩሊና (spirulina)…
#Update: በመቀንጨር ለተጠቁ ህፃናት የሚጠቅም አልጌ የሚያመርት ማዕከል ተመርቆ ሥራ ጀመረ

በህጻናት ላይ የመቀንጨር ችግር በሰፊው ጎልቶ ይታያል በተባለባት ኢትዮጵያ በመቀንጨር ለተጠቁ ህፃናት የሚጠቅም ዋቅላሚ (አልጌ) የሚያመርት ማዕከል ተመርቆ ሥራ መጀመሩን የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በሳይንሳዊ አጠራር ስፓይሩሊናን የሚያመርተው የምርምርና ማምረቻ ማዕከሉ በአዳሚ ቱሉ ግብርና ምርምር ማዕከል መገንባቱ ሲገለፅ 8 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተነግሯል።

ማዕከሉ የሚያመርተው ዋቅላሚ (አልጌ) በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ተፈላጊ ብሎም በዋጋው ውድ መሆኑ የሚነገር ሲሆን በኪሎ 20 ሺ ብር በኩንታል ደግሞ እስከ 2 ሚሊዮን ብር የሚሸጥ መሆኑ መገለፁ ይታወሳል።

@TikvahethMagazine
#ETHIO_ISTANBUL

ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ላብራቶሪ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው አክሬዲቴሽን ሠርተፊኬት አግኝቷል።

የኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃን ተድላ አክሬዲቴሽኑ በዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ጠቅሰው የዕውቅና ሠርተፊኬቱ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እንደሚረዳ ጠቅሰዋል።

በቀጣይም የሆስፒታሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ዓለም አቀፍ ደረጃን ያሟላ ስለመሆኑ በሶስተኛ ወገን እንዲረጋገጥ  እንደሚደረግም ተናግረዋል።

ሆስፒታላችን አክሬዲቴሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያለው ሲሆን ይኽ የተገኘውም ለ4 ወራት ያህል በላብራቶሪው ላይ ተገቢው ፍተሻ በኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት ከተከናወነ በኋላ ነው።

ዜጎች ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ለህክምና የሚያወጡትን ከፍተኛ ወጪ እና እንግልት በመቀነስ ሆስፒታላችን ትልቅ ሥራ እየሰራ ይገኛል። ማኀበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትም በዓመት 300 ያህል የልብ ሕሙማን ሕፃናት የነፃ ሕክምና ይሰጣል።
መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ መበደር የሚችለው የገንዘብ መጠን በአዲስ ረቂቅ ሕግ ሊገደብ ነው

ላለፉት 16 ዓመታት ያለገደብ ከብሔራዊ ባንክ ገንዘብ ሲበደር የነበረው የፌደራል መንግሥት፤ ከአገር ውስጥ ገቢ ከ15 በመቶ የበለጠ ገንዘብ በብድር ማግኘት እንዳይችል የሚገድብ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

ረቂቅ አዋጁ መንግሥት የተበደረውን ገንዘብ በአንድ ዓመት ውስጥ ካልመለሰ ከተቋሙ ሌላ ብድር መውሰድ እንደማይችልም ያስቀመጠ ሲሆን፤ መንግሥት ከብሔራዊ ባንክ ያለገደብ ብድር እንዲወስድ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደውን በ2000 ዓ.ም. የወጣውን አዋጅ የሚቀይር እንደሆነ ተነግሯል።

የአገሪቱን ማዕከላዊ ባንክ ለመምራት ከ1955 ዓ.ም. ጀምሮ አራት አዋጆች የጸደቁ ሲሆን፣ አሁን በሥራ ላይ ካለው አዋጅ በስተቀር ቀሪዎቹ አራት አዋጆች ለመንግሥት በሚሰጥ የቀጥታ ብድር ላይ ገደብ ያስቀመጡ እና ገንዘቡ የሚመለስበት ጊዜ የወሰኑ ነበር።

በሥራ ላይ ያለው አዋጅ በአንጻሩ፤ “ባንኩ ለመንግሥት እና ለፋይናንስ ተቋማት ብቻ ብድር እንደሚሰጥ ከመግለጽ ውጭ ለመንግሥት በሚሰጠው ቀጥታ ብድር ላይ ግን ምንም ገደብ ሳይጥል በለሆሳስ ያለፈ የመጀመሪያው አዋጅ” እንደሆነ ከአዲሱ ረቂቅ ጋር የቀረበው ማብራሪያ ጠቅሷል።

Credit: BBC Amharic

@TikvahethMagazine
TIKVAH-MAGAZINE
ኢትዮጵያ የዲጂታል ምንዛሬ (Digital Currency) እንቅስቃሴ ጅማሮ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በኢትዮጵያ የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (ሲ.ቢ.ዲ.ሲ) (Central Bank Digital Currency (CBDC) ) ማስተዋወቅ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ የሚያወጣውን ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል። ይህ አሰራር ማለትም የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (CBDC) ከባህላዊ…
የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (CBDC) ሙከራዎች

#ቁልፍ_ቃል - CBDC (Central Bank Digital Currencies የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ )

ኢትዮጵያ የራሷን የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ ለመተግበር ረቂቅ አዋጅ በሚኒስቴሮች ም/ቤት ማጽደቋ ይታወሳል። ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (CBDC) ን ድንበርን በማጥናት እና በሙከራ ላይ ይገኛሉ።

የተወሰኑ ሀገራትን ልምዳቸውንና አንዳንድ የመጀመሪያ ውጤቶቻቸውን በወፍ በረር እንቃኝ፦

🇳🇬 ናይጄሪያ፡ ናይጄሪያ ጥንቃቄ የተሞላበት አካሄድ የወሰደች ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2021 መገባደጃ ላይ ለ “ፕሮጀክት ካታሊስት” የማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ምንዛሪ (CBDC) የሙከራ ፕሮግራም ጀምራለች።

ይህ የተገደበ ሙከራ የቴክኖሎጂው ድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎችን የመፈጸም አቅምን መፈተሽ ላይ ያተኮረ ነበር። የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክም በግብይት ቅልጥፍና እና ደህንነት ረገድ አወንታዊ ውጤቶችን አስመዝግቧል።

ሆኖም ግን ሙከራው የ CBDCን በሰፊው ጥቅም ላይ መዋልን ለማረጋገጥ፣ የሚያስፈልጉትን  መሰረታዊ መሠረተ ልማቶችን የበለጠ ማጎልበት እንደሚያስፈልግ አመልክቷል።

🇬🇭 ጋና፡ ጋና እ.ኤ.አ በ2020 CBDCsን የሚያጠና ግብረ ሃይል በማቋቋም የበለጠ ንቁ እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለች። አሁንም በምርምር እና በማጎልበት ደረጃ ላይ ናቸው፣ ነገር ግን ያሉት ጥረቶች ወደፊት የራሳቸው CBDCs ሊኖራቸው እንደሚችል ያመለክታል።

🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ፡ የደቡብ አፍሪካ ሪዘርቭ ባንክ ተጠባብቆ ያለውን ነገር ማየት (wait-and-see) አካሄድ ላይ ናቸው። የCBDCsን  እምቅ አቅምን እንደተገነዘቡ አሳይተዋል ነገር ግን እስካሁን ምንም ተጨባጭ ዕቅዶችን አላሳወቁም።

ከአፍሪካ ባሻገር፡-

🇧🇸 ባሃማስ፡ ባሃማስ እ.ኤ.አ በ2020 መገባደጃ ላይ " Sand Dollar" በማለት የሰየሙትን የCBDC አገልግሎት በዓለም የመጀመሪያ ሆነዋል።

ገና ብዙ ጊዜ ባይሆነውም፣ የባሃማስ ማዕከላዊ ባንክ ሩቅ በሆኑ (ገጠራማ) አካባቢዎችን የሃገሪቱ ፋይናንስ ላይ አካታችነት መጨመሩን እንደ ተስፋ ሰጪ ውጤት ዘግቧል። ሆኖም የCBDC አጠቃላይ ተቀባይነት እና በኢኮኖሚው ላይ ያለው ተፅእኖ አሁንም እየተገመገመ ይገኛል።

🇨🇳 ቻይና፡ ቻይና CBDC ውድድር ውስጥ ዋና ተዋናይ ነች። የእነርሱ የዲጂታል ዩዋን ሙከራ ሰፊ ሲሆን፣ ምኞታቸውም በዓለም የመጀመሪያው ዋና ሉዓላዊ ዲጂታል ምንዛሪ ለማድረግ ነው።

የመጀመሪያዎቹ ሪፖርቶችም በተወሰኑት የሙከራ አካባቢዎች ውስጥ የግብይት (ገንዘብ ዝውውር) ፍጥነት መጨመር እና የገንዘብ ማዘዋወሪያ (መላኪያ) ወጪ መቀነስን ይጠቁማሉ።

ነገር ግን፣ የዲጂታል ገንዘብ ዋና መነሻው አንድ ሃያል ተቆጣጣሪ የሌለው መገበያያ መፍጠር ስለነበረ፣  ከማዕከላዊ ባንክ ቁጥጥር የሚደረግበት ዲጂታል ምንዛሪ (ገንዘብ) ጋር የተዛመደ ክትትል እና ቁጥጥርን በተመለከተ ስጋቶች አሉ።

የእነዚህ አገሮች ተሞክሮዎች በCBDC ዙሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ፍላጎት ያሳያል። እንደ ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ያሉ ጥቂት ሃገራት የመጀመሪያ እርምጃቸውን ሲወስዱ ሌሎች ደግሞ በልማት (CBDCን በማሳደግ) መንገድ ላይ ናቸው።

መጪዎቹ ዓመታት አገሮች በዚህ ቴክኖሎጂ  ላይ የተለያዩ ሙከራ በማድረግ  በCBDC ትግበራ ላይ ከፍተኛ መስፋፋት እና እድገት እንደሚኖር ይገመታል፤ አፍሪካም በዚህ ትግበራ ላይ ትልቅ ሚና እንደምትጫወት ካሁኑ ማየት ይቻላል።

#TikvahTechTeam  #CBDC  #Cryptocurrencies  #DigitalCurrency

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
" ትላንት ሰኔ15/10/16 ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ዶልፊን  መኪና ታርጋ ቁጥር ኦሮ  03702 ከቀኑ 7:30 ገደማ  ቤተል ተቅዋ መስጂድ ጀርባ ተሰርቆብናል።

መኪናውን ያያቹ በተከታዩ ስልክ ቁጥር እንድትደውሉልን በትህትና እንጠይቃለን።

0995010856 መሀሐድ ሀሰን
0912050715 ረውዳ አብደላህ "

@tikvahethmagazine
* አፋልጉኝ

" ማክሰኞ (11/10/2016) ከሰዓት በኋላ ከአዲሱ ገበያ ወደ ፒያሳ መንገድ ላይ በርካታ ዶክመንቶች ጠፍተውብኛል።

- የትምህርት ማስረጃዎች
-የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪና
- የድሮ ፖስፖርት
- student copy
- የዩንቨርስቲ acceptance እና
ሌሎች ማስረጃዎች ጋር ካኪ ፖስታ ውስጥ አብሮ ጠፍቶበብኝ።

ያገኘ ሰው ካለ ይተባበረኝ።

የትምህርት መረጃው ላይ ያለው ስም ሻሎም ንጉሤ ተክሌ (Shalom Nigussie Teklie)

ስልክ ቁ፡ 0921787893 ወይም 0912665211

አመሠግናለሁ። "

(ሻሎም ንጉሴ)

@tikvahethmagazine
+251916716110

65% የተገነባ በ 10% ቅድመ ክፍያ
ሳይታችን የሚገኘው መሐል አዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ አጠገብ

➣ 2 መዋኛ ገንዳ
➣ ቅርጫት ኳስ መጫወቻ
➣ አስተማማኝ የመኪና ቻርጀር  እና ፓርኪንግ
➣ ጅም እና ስፓ
➣ ጋርቤጅ ቹተር
➣ ስታንድ ባይ ጄኔሬተር
➣ የከርሰምድር ውሀ
➣ የበረዶ መንሸራተቻ (Ice Sekating)

በዚ አይገረሙ ልዩ የሄሊኮፕተር ማረፊያ ያለው የዚህ ትውልድ ድንቅ የጥበብ አሻራ ያረፈበት የዘመናዊው ኑሮ  ፈርቀዳጅ  ድንቅ የዕደ-ጥበብ ማሳያ ነው ከ ባለ አንድ መኝታ 86 ካሬ እስከ ፔንታ ሀውስ 646 ካሬ አማራጮችን አዘጋጅተን እርሰዎን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን አሚባራ ፕሮፐርቲስ በልዩነት የተገነባ
"በክልሉ የወባ በሽታ በመከሰቱ ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል" የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ

በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለፈው ሳምንት 177 ሺ 561 ሰዎች በወባ በሽታ ሲያዙ በሀረሪ ክልል በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 237 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ያሲን አብዱላሂ በሰጡት መግለጫ ጠቅሰዋል።

በተለይ በሽታው በክልሉ ሶፊ ፤ ድሬ ጠያራ እና አሚር ኑር ወረዳ መስተዋሉን የጠቆሙት ሀላፊው ኅብረተሰቡ ለወባ ትንኝ መራቢያ አመቺ የሆኑ ያቆሩ ውሃዎችን በማፋሰስ እንዲደርቁ ከማድረግ ጀምሮ የመኝታ አጎበሮችን በመጠቀም በሽታውን አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት ፣እራስ ምታት እና ማንቀጥቀጥ የመሳሰሉ የወባ በሽታ ምልክት የተስተዋሉባቸውን ሰዎች በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም በመውሰድ ተገቢውን የጤና ምርመራ እና ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
በሴራሊዮን ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጃገረዶችን ማግባት እስከ 15 ዓመት እስራት ሊያስቀጣ ነው፤ በኢትዮጵያስ?

የሴራሊዮን ፓርላማ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጃገረዶችን ማግባት እስከ 15 ዓመት እስራት በሚደርስ የወንጀል ጥፋት እና ከ2,000 ዶላር ጋር የሚመጣጠን ቅጣት የሚጥል ህግ አጽድቋል።

በተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) መሰረት በሴራሊዮን ከሚገኙት ወጣት ሴቶች መካከል አንድ ሶስተኛ ያህሉ የተዳሩት 18 ዓመት ሳይሞላቸው ነው።

እንደ ዩኒሴፍ መረጃ በሀገሪቱ 800,000 የሚሆኑ እድሜያቸው ሳይደርስ የተዳሩ ሴቶች ያሉ ሲሆን 400,000 የሚያህሉት ጋብቻ የፈጸሙት ከ15 ዓመታቸው በፊት ነው።

የሴራሊዮን ፓርላማ ያጸደቀው ህግ ከኢትዮጵያ ሲነጻጸር፦

እንደ ዩኒሴፍ መረጃ በኢትዮጵያ ከ15 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ እድሜያቸው ሳይደርስ የተዳሩ ሴቶች ያሉ ሲሆን 6 ሚሊየኑ ጋብቻ የፈጸሙት ከ15 ዓመታቸው በፊት ነው።

በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ መሰረት ለጋብቻ ዝቅተኛው እድሜ ለሁለቱም ጾታዎች 18 ዓመት ሆኖ ተቀምጧል። የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ ደግሞ ያለ እድሜ ጋብቻ ላይ ከ3 እስከ 7 ዓመት እስራት የሚደርስ ቅጣት ያስቀምጣል።

@tikvahethmagazine
ክላውድ ብሪጂ ማሰልጠኛ ተቋም

📣 የሽያጭ(Sales Training)ስልጠና ጀምረናል📣

- አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለዉጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!
- እኛጋ ለመሰልጠን ኮምፕዩተር መግዛት አያስፈልግዎትም!
- የብዙ አመት ልምድ እና ብቃት ባላቸዉ አሰልጣኞች ይሰልጥኑ!

FREE SEMINAR EVERY FRIDAY 💥💥

☎️ ለመመዝገብ:0942280000

🎯አድራሻ:መገናኛ ሲቲ ሞል ህንፃ ላይ (wow burger ያለበት) 6ኛ ፎቅ

Register online
https://cloudbridgeacademy.com/registration

📱 👉 TIKTOK 📱 👉 Telegram :
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
+251916716110

65% የተገነባ በ 10% ቅድመ ክፍያ
ሳይታችን የሚገኘው መሐል አዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ አጠገብ

➣ 2 መዋኛ ገንዳ
➣ ቅርጫት ኳስ መጫወቻ
➣ አስተማማኝ የመኪና ቻርጀር  እና ፓርኪንግ
➣ ጅም እና ስፓ
➣ ጋርቤጅ ቹተር
➣ ስታንድ ባይ ጄኔሬተር
➣ የከርሰምድር ውሀ
➣ የበረዶ መንሸራተቻ (Ice Sekating)

በዚ አይገረሙ ልዩ የሄሊኮፕተር ማረፊያ ያለው የዚህ ትውልድ ድንቅ የጥበብ አሻራ ያረፈበት የዘመናዊው ኑሮ  ፈርቀዳጅ  ድንቅ የዕደ-ጥበብ ማሳያ ነው ከ ባለ አንድ መኝታ 86 ካሬ እስከ ፔንታ ሀውስ 646 ካሬ አማራጮችን አዘጋጅተን እርሰዎን በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን አሚባራ ፕሮፐርቲስ በልዩነት የተገነባ
ተመራማሪዎች የመኪና አደጋን ለመከላከል የሚያስችል ምን አይነት አዲስ ቴክኖሎጂ ሰሩ?

የመኪና አደጋ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ባላደጉ አገሮች በስፋት ይስተዋላል። ከአህጉሪቱ ናይጄሪያ በመኪና አደጋ በርካታ ሰዎችን ላጣለች ቢባልም ችግሩ በኢትዮጵያም እጅግ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል።

የመኪና አደጋ መንስኤዎች የተለያዩ ቢሆኑም ፍጥነት፣ በግዴለሽነት ማሽከርከር፣ ከአደንዛዥ እፅ ባለፈ ደግሞ አልኮል ተጠቅሞ ማሽከርከር በዋነኝነት ከሚጠቀሱት መሃከል አንደኛው እንደሆነ ይነገራል።

ይህንን ታሳቢ በማድረግ በአውስትራሊያ የሚገኘው የኤዲት ኮዋን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በካሜራ የተቀረፀ መረጃን ተንርሶ አንድ አሽከርካሪ አልኮል መጠጣቱን መለየት የሚያችል አዲስ የኮምፒዩተር መከታተያ ቴክኖሎጂ እያበለፀጉ ነው።

ተመራማሪዎቹ ፓወር ፍሊት ከተሰኘው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በመሆን አልኮል የወሰዱ የአሽከርካሪዎችን ለመለየት እንዲረዳቸው ተከታታይ ቪዲዮዎች ለሙከራ አውለዋል።

ሙከራው ተፈጥሯዊ በሆነ ከባቢ ላይ የተደረገ ሲሆን አሽከርካሪዎቹ መጠነኛ፣ ዝቅተኛ እና ከባድ በተባለ የስካር ደረጃ ላይ ሆነው በቪዲዮ የእንቅስቃሴአቸው መረጃ ተሰብስቧል።

በመቀጠልም ተመራማሪዎቹ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈርጅ በሆነው የማሽን ለርኒንግ ሲስተም በመጠቀም የአሽከርካሪዎቹን የፊት ገጽታ፣ የእይታ አቅጣጫ እና የጭንቅላት አቀማመጥ የመሰሉ ምልክቶችን ከቪዲዮው ላይ በመውሰድ የአልኮሉን መጠን መመዘን ችለዋል።

በዚህም በሶስት ደረጃ ተከፍለው በተደረጉት ሙከራዎች ይህ የቴክኖሎጂ ስርዓት (System) 75 በመቶ አልኮል የወሰዱ አሽከርካሪዎችን በትክክለኛ መንገድ መለየት እንደቻለ ተመራማሪዎቹ አሳውቀዋል።

ይህ ቴክኖሎጂ አልኮል በመውሰዳቸው ምክንያት ማሽከርከር የተሳናቸው አሽከርካሪዎችን በመለየት የቅድመ መከላከል ስራን ለመስራት ያግዛል ሲባል በስማርት ስልኮች ሊሰራ የሚችልበት አማራጭ ስለተካተተበት የበለጠ ውጤታማ ይሆናል ተብሏል።

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

በዳግማዊ ምኒሊክ በአታ ለማርያም ገዳም በክረምት መርሃ ግብር የአብነት ትምህርት ለማስተማር ምዝገባ ተጀምሯል።

ትምህርቱ በመደበኛ ቀን ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በዳግማዊ ምኒሊክ በአታ ለማርያም ገዳም መምህራንና ካህናት ማሰልጠኛ መንፈሳዊ ግቢ ውስጥ በተመረጡ አዳሪ ደቀ መዛሙርት መምህራን የሚሰጥ የደቂቀ ቅዱስ እስጢፋኖስ   የክረምት መረሀ ግብር ነው ተብሏል።

በመሆኑም በዚህ መርሃግብር ላይ ልጆችን ለማስመዝገብ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል ማስመዝገብ እንድትችሉ ጥቆማ ቀርቧል።

0955252387
 0922675398

@tikvahethmagazine
በሱስ የተጠቁ ወገኖችን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመው የጎዳና ላይ ሩጫ መቼ ይደረጋል?

በአዲስ አበባ በሱስ የተጠቁ ወገኖችን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ የጎዳና ላይ ሩጫ የፊታችን ሀምሌ 28 የሚደረግ ሲሆን ለዚህም የቲኬት ሽያጩ ተጀምሯል።

"ተገኝቷል" ሁለንተናዊ የወንጌል አማኞች ተቋም ያዘጋጀው ይህ ውድድር፤ መነሻው ጀሞ 3 ሲሆን መዳረሻውን ሀጫሉ ሁንዴሳ መንገድ ጋርመንት  ያደርጋል።

ተቋሙ ወጣቶች ላይ በሱሰኝነት፣ በሴተኛ አዳሪነት ዙሪያ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በውድድሩ የሚገኘው ገቢ የወጣቶች የሱስ ማገገሚያ ተቋም ለማቋቋም ይውላል ተብሏል።

ሩጫው ከጠዋቱ 12 ሰዓት ተጀምሮ ረፋድ 3:30 የሚጠናቀቅ ሲሆን ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው runtohold.com ድረገፅ ላይ ቲኬቱን በ500 ብር በመግዛት መሳተፍ እንዲችሉ ጥቆማ ቅርቧል።

@tikvahethmagazine
በድምጽ ያሉ መጽሐፍትን (Audio Book) ጨምሮ ባለፉት 9 ወራት ምን ያህል መጽሐፍ አንብበዋል?
Anonymous Poll
18%
ከ10 በላይ መጽሐፍትን ማንበብ ችያለሁ
23%
ያነበብኩት መጽሐፍ ከሦስት አይበልጥም
59%
በዚህ ጊዜ ምንም መጽሐፍ አላነበብኩም
2024/06/26 01:40:50
Back to Top
HTML Embed Code: