tg-me.com/MEZMURA/80
Last Update:
#እናቴ እመቤቴ
እናቴ እመቤቴ/ የማትጠፊው ከአፌ/2/
በረከቴ አንቺ ነሽ/ የመስቀል ስር ትርፌ /2/
አምላኬ ሸልሞኝ ለዘላለም ያዝኩሽ
ጌታን የማይብሽ ብሌኔ አደረኩሽ
በልቤ ላይ ይፍሰስ የፍቅርሽ ፀዳሉ
የሚጣፍጥ ስምሽ መድኃኒት ለሁሉ
ተወዳጁ ልጅሽ ፀጋውን ያብዛልኝ
እድሜዬ እስኪ ፈፀም ለክብርሽ እንድቀኝ
/አዝ====
ነፍሴ እንዳትጎዳ እንዳትቀር ባክና
ብርታት ሆኖልኛል የስምሽ ምስጋና
እኖራለሁ ገና ንኢ ንኢ ስልሽ
ክብሬ ነሽ ጌጤ ነሽ ከአፌ የማልነጥልሽ
/አዝ =====
ሲነጋም ጠራሁሽ ሲመሽም ጠራሁሽ
ስዕልሽ ፊት ቆሜ ሰአሊ ለነ እያልኩሽ
አሜን የምልብሽ መነጋገሪያዬ
የአማኑኤል እናት አንቺ ነሽ ቋንቋዬ
/አዝ=====
መች በስጋ ጥበብ ሰው ለአንቺ ይቀኛል
ከአምላክ ከአልተላከ ከፊትሽ ይቆማል
አንቺን ማመስገኔ አንቺን ማወደሴ
በልቡ ያሰበሽ ፈቅዶ ነው ስላሴ
/አዝ=====
ብዙ ተቀብዬ ጥቂት አልዘምርም
ለእናትነት ፍቅርሽ ከቶ ዝም አልልም
እኔን በእደ ፍቅርሽ የምትባርኪ
ኦ ምልዕይተ ፀጋ ድንግል ሰላም ለኪ
@MEZMURA
BY mezmurat
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/MEZMURA/80