Telegram Group Search
Forwarded from HEY Online Market
Samsung Galaxy S22 Ultra
256 GB - 67,000 ETB
512 GB - 78,000 ETB

Samsung Galaxy S23 Ultra
256 GB - 92,000 ETB
512 GB - 109,000 ETB

Samsung Galaxy S24 Ultra
256 GB - 109,000 ETB
512 GB - 124,000 ETB

Exchange Available
🏍️ Free Delivery

Contact us :
0925927457 @eBRO4
@Heyonlinemarket
ቤኒ ማካርቲ ከዩናይትድ ጋር ይለያያል !

የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኞች ቡድን አባሉ ቤኒ ማካርቲ በዚህ ወር ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ቀያዮቹ ሴጣኖችን እንደሚለቅ ተገልጿል።

የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ቤኒ ማካርቲ ከሁለት አመት አመት የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን መሾም ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ መቀላቀሉ ይታወሳል።

በአያክስ ፣ ሴልታቪጎ እና ፖርቶ በፊት መስመር አጥቂነት ተጫውቶ ያሳለፈው ቤኒ ማካርቲ ኬፕ ታውን ሲቲ እና አማዙሉን በአሰልጣኝነትም መርቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊዮኔል ሜሲ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞታል ! የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ በትናንቱ ምሽቱ የቺሊ የኮፓ አሜሪካ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል። የጨዋታውን ሙሉ ዘጠና ደቂቃ ተጫውቶ ያጠናቀቀው ሊዮኔል ሜሲ ይሁን እንጂ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ምቾት እንዳልተሰማው ተናግሯል። " በቀኝ እግሬ ላይ ከመጀመሪያው ምቾት እየተሰማኝ አልነበረም ነገርግን ጨዋታውን…
ሊዮኔል ሜሲ በፔሩ ጨዋታ ላይሳተፍ ይችላል !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ላለበት የኮፓ አሜሪካ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ትላንት ባደረገው ልምምድ አለመሳተፉ ተገልጿል።

ሊዮኔል ሜሲ ለሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ዝግጁ እንዲሆን አርጀንቲና ቅዳሜ ሌሊት ከፔሩ ጋር በምታደርገው የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ እረፍት ሊያደርግ እንደሚችል ተነግሯል።

ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀሏን ያረጋገጠችው አርጀንቲና ምድቧን አንደኛ ሆና የምታጠናቅቅ ከሆነ በቀጣይ በሩብ ፍፃሜው ከሜክሲኮ ወይም ኢኳዶር ጋር የምትገናኝ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአሜሪካ ተጨዋች የዘረኝነት ጥቃት ደረሰባቸው !

የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ትላንት ሌሊቲ ከፓናማ ጋር ያደረገውን የኮፓ አሜሪካ ጨዋታ 2ለ1 መሸነፉን ተከትሎ ተጨዋቾቹ የዘረኝነት ጥቃት እንደደረሳቸው ተገልጿል።

ከሽንፈቱ በኋላ ቲሞቲ ዊሀን ጨምሮ ሌሎች የብሔራዊ ቡድኑን ተጨዋቾች ኢላማ ያደረጉ የዘረኝነት ጥቃቶች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ሲሰነዘሩ ተስተውለዋል።

በጨዋታው ከተሰለፉ ስድስት የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጥቁር ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ቲሞቲ ዊሀ 18ኛው ደቂቃ ላይ የተቃራኒን ተጨዋች በመማታቱ ቀይ ካርድ ተመልክቶ ነበር።

የአሜሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ የተሰነዘሩ የዘረኝነት ጥቃቶች እንዳሳሰቡት ገልፆ " ለዘረኝነት ጥቃቶች ቦታ የለንም እንደ ተቋም ከምንጠቀመው የመከባበር እሴት ተቃራኒ ነው " ብሏል።

በቀጣይም በዘረኝነት ጥቃቱ ምክንያት የስነልቦና ድጋፍ ለሚፈልጉ ተጨዋቾች እና የብሔራዊ ቡድኑ አባላት እንደሚዘጋጅላቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤድመንድ ታፕሶባ በሀገሩ ፋውንዴሽን አቋቁሟል !

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሌቨርኩሰኑ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ኤድመንድ ታፕሶባ በትውልድ ሀገሩ ቡርኪናፋሶ የራሱን ፋውንዴሽን ማቋቋሙን ይፋ አድርጓል።

ኤድመንድ ታፕሶባ የመሰረተው ፋውንዴሽን በሀገሩ ቡርኪናፋሶ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ተቸግረው ለሚገኙ ተረጂዎች ዘላቂነት ያለው ድጋፍ ለመስጠት ማለሙ ተገልጿል።

ኤድመንድ ታፕሶባ በሰጠው አስተያየትም " ቡርኪናፋሶ ውስጥ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት በርካቶች ሰብዓዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል መርዳት የፈለግኩትም ለዚህ ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንቶኒዮ ሩዲገር ለነገው የዴንማርክ ጨዋታ ይደርሳል !

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አንቶኒዮ ሩዲገር ብሔራዊ ቡድን ከነገው የዴንማርክ ጨዋታ በፊት በሰራው የመጨረሻ ልምምድ ላይ መሳተፉ ተገልጿል።

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞት የነበረው አንቶኒዮ ሩዲገር ለነገው የዴንማርክ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ዝግጁ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ጀርመን ከዴንማርክ ጋር የሚያደርጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ነገ ምሽት 4:00 ሰዓት የሚጀምር ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🚀 የአቪዬተር ሻሞ - በረራ በነጻ!
የአቪዬተር ሻሞ ሽጦታዎች ዛሬም ቀጥለዋል!
እስከ 4ሺብር ዋጋ ያላቸው ነጻ የመወራረጃ እጣዎች እርስዎን እየጠበቁ ነው።
አሁኑኑ የራስዎ ያርጓቸው - 👉ln.run/k_QQW
Forwarded from WANAW SPORT
📢 አሁንም ልዩ ቅናሽ ከ #ዋናው!

👉🏾 በቀላሉ በዋናው አዲስ ቦት የስፖርት አልባሳትን በማዘዝ ልዩ የ5% ቅናሽ ያግኙ።

➡️ @WanawSportBot ⬅️

👉🏾 #እንዳያመልጥዎ፣ አሁኑኑ ይዘዙን!

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ንግግር ጀመሩ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀልን ለማስፈረም ሌስተር ሲቲን ማነጋገር መጀመራቸው ተገልጿል። ይሁን እንጂ ሰማያዊዎቹ ኬርናን ዴውስቡሪ ሀልን ለማስፈረም እስካሁን ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ለሌስተር ሲቲ አለማቅረባቸው ተነግሯል። የ 25ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀል የልጅነት ክለቡ ሌስተር…
ቼልሲ ለሌስተር ይፋዊ ጥያቄ አቅርበዋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀልን ለማስፈረም ለሌስተር ሲቲ ይፋዊ ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ቼልሲ እና ሌስተር ሲቲ በተጨዋቹ ዝውውር ዙሪያ ዴቪድ ፎፋና እና ሴሳር ካሳዴን የዝውውሩ አካል ለማድረግ በመነጋገር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

የ 25ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀል በቀጣይ ክለቦች ከስምምነት የሚደርሱ ከሆነ በቼልሲ የረጅም ጊዜ ኮንትራት እንደሚፈረም ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ቪንሰስን የላሊጋ አምባሳደር ማድረግ እንፈልጋለን " ቴባስ

የስፔን ላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ጫማውን ሲስቅል የላሊጋው አምባሳደርነት ሚና እንደሚሰጡት ገልፀዋል።

" ቪንሰስ ጁኒየር ብዙ ጥቃቶች ደርሰውበታል ምክንያቱም እሱ የዘረኝነት ፍልሚያው መሪ ስለሆነ ነው " ያሉት ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ እሱ ጫማውን ሲሰቅል የላሊጋው አምባሳደር እንዲሆን ሀላፊነቱን እናቀርብለታለን " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🔥 ከከባድ የምድብ ጨዋታዎች በኋላ የአዉሮፓ ጨዋታ ቅዳሜ ምሽት ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይጀምራሉ!

🤔  ፉክክሩም አይሏል! እነማን ወደ ሩብ ፍፃሜ ያልፋሉ? ለናንተ ምርጡ ቡድንስ ማነው? መልሶቻችሁን ከስር አጋሩን!

👉 እነዚን ድንቅ ፍልሚያዎች ጨምሮ ሌሎች የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎችን በቀጥታ በዲኤስቲቪ በጎጆ ፓኬጅ 350 ብር በ SS Football 225 ይከታተሉ።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#Euro2024onDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ኢትዮጵያ መድን ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግብ ወገኔ ገዛኸኝ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኢትዮጵያ መድን ካለፉት አስራ ሁለት ጨዋታዎች የተሸነፈው በአንዱ ብቻ ሲሆን ስምንቱን በአሸናፊነት መወጣት ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

8️⃣ ኢትዮጵያ መድን :- 40 ነጥብ

1️⃣0️⃣ ሀድያ ሆሳዕና :- 38 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

እሮብ - ሀድያ ሆሳዕና ከ ኢትዮጵያ ቡና

ቅዳሜ - ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እኔን በግራ መስመር ተከላካይ ማጫወት መፍትሔ አያመጣም " ሳካ

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ የቀድሞ ተጨዋች ኢያን ራይት የሰጠው እሱን ቦታ ቀይሮ የማጫወት አስተያየት መፍትሔ እንደማያመጣ ተናግሯል።

የቀድሞ የአርሰናል ታሪካዊ ተጨዋች ኢያን ራይት ቡካዩ ሳካ በአውሮፓ ዋንጫው ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በግራ መስመር ተከላካይ ሆኖ እንዲሞከር ሀሳቡን ሰጥቶ ነበር።

ለኢያን ራይት አስተያየት ምላሽ የሰጠው ቡካዩ ሳካ " የእኔን መጫወቻ ቦታ ቀይሮ ማጫወት ለእንግሊዝ መፍትሔ አይሆንም ፣ ነገርግን ሁሉም በሳውዝጌት እጅ ነው እሱ በሚመርጠው ማመን አለብን።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሆሴሉ ሪያል ማድሪድን ሊለቅ ነው ! ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከሪያል ማድሪድ ጋር ላለመቀጠል ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል። ሪያል ማድሪድ በሆሴሉ የውሰት ውል ውስጥ የተካተተውን አማራጭ ተጠቅመው 1.5 ሚልዮን ዩሮ ወጪ በማድረግ በቋሚነት ለማስፈረም መወስናቸው ይታወሳል። ይሁን እንጂ ሆሴሉ ኪሊያን ምባፔ እና ኢንድሪክ ወደ ሪያል ማድሪድ መምጣታቸውን ተከትሎ ሎስ…
ሆሴሉ የኳታሩን ክለብ አል ሀራፋ በይፋ ተቀላቀለ

ያለፈውን የውድድር አመት በሪያል ማድሪድ ቤት ያሳለፈው ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ የኳታሩን ክለብ አል ሀራፋ በይፋ ተቀላቅሏል።

የኳታሩ ክለብ አል ሀራፋ ተጫዋቹን በ1.5 ሚልዮን ዩሮ የኮንትራት ማፍረሻ ሒሳብ ለአንድ ተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ ባካተተ የሁለት አመት ውል ማስፈረማቸው ይፋ ሆኗል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ተጨዋቹ ከክለባቸው ጋር መለያየቱን ባወጡት ይፋዊ መግለጫ ያረጋገጡ ሲሆን ሆሴሉ በክለቡ ለሰጠው ትልቅ ግልጋሎት ምስጋና አቅርበዋል።

ሪያል ማድሪድ ሆሴሉን በክለቡ የማቆየት ፍላጎት ቢኖራቸውም ተጨዋቹ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል መፈለጉ መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጄሴ ማርሽ አርጀንቲና እንድትቀጣ ጠይቀዋል ! የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጄሴ ማርሽ የትላንት ተጋጣሚያቸው አርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ቅጣት እንዲጣልበት አወዳዳሪውን አካል ጠይቀዋል። አሰልጣኙ ቅጣቱ እንዲጣል የጠየቁት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከእረፍት መልስ ከመልበሻ ቤት ለመውጣት የተወሰኑ ደቂቃዎች መዘግየታቸውን ተከትሎ ነው። አሰልጣኝ ጄሴ ማርሽ በንግግራቸውም " ከእኛ ጋር…
አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ቅጣት ተጣለባቸው !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ የአንድ ጨዋታ እገዳ ቅጣት እንደተጣለባቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ቅጣቱ የተጣለባቸው አርጀንቲና ከካናዳ ጋር በነበራት የኮፓ አሜሪካ የመጀመሪያ ጨዋታ በእረፍት ሰዓት ተጨዋቾች ማዘግየታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ አርጀንቲና ነገ ሌሊት ከፔሩ ጋር በምታደርገው የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ቡድኑን የማይመሩ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ማትያስ ዴሊትን ማስፈረም ይፈልጋል !

ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የባየር ሙኒክ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማትያስ ዴሊት በዚህ ክረምት ለማስፈረም በማሰብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ተጨዋቹን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ቢጀምሩም እስካሁን ይፋዊ ጥያቄ እንዳላቀረቡ እና ከባየር ሙኒክ ጋርም ንግግር እንዳልጀመሩ ተዘግቧል።

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ማትያስ ዴሊትን አሁን ላይ የመጀመሪያ ምርጫ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አስቶን ቪላ ተጨዋች አስፈርመዋል !

አስቶን ቪላ ኔዘርላንዳዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አያን ማትሰን ከምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በቦርስያ ዶርትመንድ ቤት ያሳለፈው አያን ማትሰን አስቶን ቪላን በስድስት አመት ኮንትራት መቀላቀሉ ተገልጿል።

የቀጣይ የውድድር አመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው አስቶን ቪላ ለተጨዋቹ ዝውውር 44 ሚልዮን ዩሮ ማውጣታቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊዮኔል ሜሲ በፔሩ ጨዋታ ላይሳተፍ ይችላል ! የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ላለበት የኮፓ አሜሪካ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ትላንት ባደረገው ልምምድ አለመሳተፉ ተገልጿል። ሊዮኔል ሜሲ ለሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ዝግጁ እንዲሆን አርጀንቲና ቅዳሜ ሌሊት ከፔሩ ጋር በምታደርገው የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ እረፍት ሊያደርግ እንደሚችል ተነግሯል። ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀሏን ያረጋገጠችው…
ሊዮኔል ሜሲ በፔሩ ጨዋታ ውጪ ሆነ !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ በጉዳት ምክንያት ከነገው የፔሩ የኮፓ አሜሪካ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ውጪ እንደሚሆን ተገልጿል።

ከቀናት በፊት አርጀንቲና ቺሊን ባሸነፈችበት ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞት የነበረው ሊዮኔል ሜሲ ትላንት በነበረው የቡድኑ ልምምድ ላይም ሳይሳተፍ ቀርቶ ነበር።

የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲና በሩብ ፍፃሜው ለምታደርገው ጨዋታ ወደ ሜዳ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማኑኤል ኡጋርት ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ?

ማንችስተር ዩናይትድ ዩራጓዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ለማስፈረም ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ጋር ንግግር ማድረጋቸው ተገልጿል።

የ 23ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ማንችስተር ዩናይትድ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ባይሳተፍም እንኳን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል።

ባለፈው አመት ፒኤስጂን ከስፖርቲንግ ሊስበን በአምስት አመት ኮንትራት የተቀላቀለው ማኑኤል ኡጋርት በዚህ ክረምት ክለቡን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ተጨዋቹ በሌሎች ክለቦችም እንደሚፈለግ የተገለፀ ሲሆን ቀያዮቹ ሴጣኖች አስካሁን ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ #እንዳላቀረቡ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/06/29 02:12:02
Back to Top
HTML Embed Code: