Telegram Group Search
ፈለገ አእምሮ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት የሐዲሳት መጻሕፍት ትርጓሜ ደቀ መዛሙርትን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመረቀ።

ሰኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት ቤተ ክህነት መቄት ወረዳ ቤተ ክህነት የአስፋ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈለገ አእምሮ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት 11 የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ ደቀመዛሙርትን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም አስመርቋል።

ደቀመዛሙርቱ ባለፉት 5 ዓመታት የሐዲሳት ትርጓሜ መጻሕፍት ትምህርትን በሚገባ ተምረው በማጠናቀቃቸው በመምህርነት ተመርቀዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ወደ ጵጵስና ማዕረግ ከመምጣታቸው በፊት የንስሐ ልጆቻቸውን በማስተባበር ያስጀመሩት የፈለገ አእምሮ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት በ5 ጉባኤ ቤቶች በርካታ ደቀመዛሙርትን ተቀብሎ በአዳሪነት እያስተማረ ሲሆን በሐዲሳት መጻሕፍት ትርጓሜ 11 መምህራንን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመርቋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም የበላይ ጠባቂ፥ ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የላከውን  “አንተ ግን ባመንኸው እምነት በተማርኸው ትምህርት ጸንተህ ኑር” የሚለውን መልእክት በማስታወስ ለተመራቂዎች አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜን ተምራችሁ የጨረሳችሁና በመመረቅ ላይ ያላችሁ ደቀመዛሙርት ቅዱስ ጳውሎስ ለቅዱስ ጢሞቴዎስ የሰጠው መመሪያ መመሪያችን ነው ብላችሁ በመቀበል በእምነት የጸናችሁ፥ በምግባር የቀናችሁ ልትሆኑ ይገባል ብለዋል ብፁዕነታቸው።

የኮቪድ 19 ዓለም ዐቀፍ ተላላፊ በሽታና ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያልቆመው የእርስ በርስ ጦርነት ተግዳሮቶች ቢሆኑም ርቧችሁ፣ ጠምቷችሁ፣ በርዷችሁና የመማሪያ ቁሳቁስ አጥታችሁ እንዳትበተኑና ትምህርታችሁ እንዳይቋረጥ የተደረገላችሁን እንክብካቤ በማስታወስ በመከራ ጸንታችሁ ሀገርንና ቤተክርስቲያንን እንድታገለግሉ በማለት አደራ ሰጥተዋል። ብፁዕነታቸው አያይዘውም፥ ጀምራችሁ በመፈጸማችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ሐሳባቸውን አዋልደው በተግባር በማሳደግ የትምህርት ተቋሙን የፈጠሩና ተማሪዎችንም ለማስመረቅ ያበቁ ከ17 ዓመታት በላይ ያለምንም መታከት አብረዋቸው ያሉ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የዐቢይ ኮሚቴ አባላትና በሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በደቀ መዝሙርነትና በመምህርነት ሳሉ መምህረ ንስሐ በመሆን ሲያገለግሏቸው የነበሩ፥ በጸጋቸው ኹሉ ለመንፈሳዊ ትምህርት ቤቱ መቋቋም ምክንያት ለሆኑ የመንፈስ ልጆቻቸው፣ በሰሜን አሜሪካ የዚሁ ትምህርት ቤት የቦርድ አባላት፣ ተቋሙን ለማስፋፋት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ኹለንተናዊ ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙትን ኹሉ አመስግነዋል።

በመርሐ ግብሩ ወረብ፣ ቅኔና ሌሎች መርሐ ግብራት የተከናወኑ ሲሆን አብላጫ ውጤት በማስመዘገብ ከ1ኛ-3ኛ ደረጃ ይዘው ላጠናቀቁ ተመራቂ ሊቃውንት፣ ትምህርት ቤቱን በማስተዳደርና ምግብ አብስሎ በመመገብ የሚያገለግሉ መነኰሳትን በመመደብ ትልቁን ኃላፊነት እየተወጣ ለሚገኘው ኃይላ ለጥበብ ወምዕራፈ ቅዱሳን ተከዜ ሐዋርያ ክርስቶስ አንድነት ገዳም የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

የአስፋ ገነተ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ፈለገ አእምሮ መንፈሳዊ ከፍተኛ ትምህርት ቤት በ5 ጉባኤ ቤቶች ከ75 በላይ ደቀ መዛሙርትንና 21 ሠራተኞችን እያስተዳደረ ሲሆን በግንባታ ላይ የሚገኘው B+G+7 ማስፋፊያ ግንባታ ሲጠናቀቅ የመቀበል አቅሙን ወደ 500  ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።

#የሰሜን_ወሎ_ሀገረስብከት_የሚዲያ አማራጮችን ይወዳጁ። ለሌሎችም ያጋሩ።

የሀገረ ስብከቱን ዩቲዩብ subscribe ያድርጉ
https://youtube.com/c/NorthWolloDioceseMedia Subscribe, ለወዳጅ ዘመድዎ share ያድርጉ።

የሀገረ ስብከቱን ድረገጽ ይጎብኙ
https://eotc-nw.org

ፌስቡክ   like, share ያድርጉ
https://www.facebook.com/EOTCNWD?mibextid=ZbWK
ሕልማቸው ተሳካ! ደስታቸውን በእንባ ገለጹ
አልቅሰው አስለቀሱን። ለምን አለቀሱ? ምንስ እየሠሩ ነው? እዩት ለሌሎችም አጋሩት።
https://youtu.be/wFNd5BJDuzk

ውድ የፈለገ አእምሮ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ደጋፊዎች በእግዚአብሔር እርዳታ በእናንተ ድጋፍ ፍሬ ማፍራት ጀምሯል።

ብፁዕነታቸው በምረቃ መርሐ ግብሩ ያደረጉት ልብ የሚነካ ንግግር እንድትመለከቱ ጋብዘናል
#የምስራች

#መልክአ_ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ በአረቋቴ ኤፍራታ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ቂርቆስ ወቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አንድነት ገዳም ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ለገበያ ቀረበ።

#መጽሐፉን
አዲስ አበባ 5 ኪሎ ቅድስት ማርያም ከማኅበሩ ሕንፃ ፊት ለፊት ባኮስ መጻሕፍት መደብር - Bakos Book Store ያገኙታል!

#ለበለጠ_መረጃ 0920888887 ይደውሉ።

✥✥✽✞═•┉✽✥✥✽┉•═✞✽✥✥

"ሰላም ለዝክረ ስምከ፤

ፍካሬው ፊትን የሚያስደስት እጅ መንሻ ሐሤት ለሚባልና ትርጉሙ ደስታ ለተባለ የስም አጠራርህ ሰላምታ ይገባል፡፡ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጩኸቷን የምትሰማ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ሆይ! ጩኸቴን በየሰዓቱ ስማ ፤ ነፍሴንም አንጻት ከኃጢአት አገዛዝም ነጻ እወጣ ዘንድ ንስሓን ስጠኝ፡፡"

(መልክአ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
መሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከእስር ተፈቱ።

የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ  መሪጌታ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ከእስር መለቀቃቸውን የማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ዋና ሥራ አስኪያጁ ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ነበር ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ለእስር የተዳረጉት።

ከሁለት ወራት በኋላ ዛሬ ሰኔ 25 ቀን 2016  ዓ.ም  ከእስር  መለቀቃቸውን  ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ተችሏል።
2024/07/04 05:43:37
Back to Top
HTML Embed Code: