Telegram Group Search
ዲያቆን ዘማርያም ዘለቀ እንኳን ለዚህ ክብር አበቃህ መምህር 🙏


#ድምፀ_ተዋህዶ
ድንግልናን ማጣት የሚያስከትለው ችግር

       (ክፍል ሦስት)

🔸በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተገለጸው #ከጋብቻ_ውጪ የሚደረግ የግብረ ሥጋ ግንኙነት #ዝሙት ነውና በነፍሱ ይቀጣበታል፡፡

🔸በባልና ሚስት በኩል ደስታን ፣ #መተማመንን ፣ ፍቅርን ይቀንሳል፡፡

🔸#አለመታመን#አለመታገስ እና #አለመፅናትን ያስከትላል ፤ መንፈሳዊ ፀጋዎችን ያሳጣል፡፡

🔸#የጋብቻ_መዘግየትን ያመጣል፡፡ ጓጉታችሁ ወደጋብቻ የምትገቡበት ምክንያት አይኖራችሁም፡፡ ከጋብቻ በፊት ስሜቱን መቆጣጠር ያልቻለ ፣ መታቀብም ያልቻለ ከጋብቻም በኋላ አይታቀብም፡፡

🔸ከጋብቻ በፊት ግንኙት መፈፀም እንደአምኖንና ትዕማር ታሪክም ሊፈጠር ይችላል፡፡ አምኖን በትዕማር የዓይን ፍቅር ተማረከ፡፡ ከዛ ክፉ መንገድ ተጠቅሞ አስነወራት፡፡ ልክ ሩካቤ (sex ) ከፈፀሙ በኋላ ግን #ያቺ_በፍቅር_የታመመላት_ትዕማር #ለዓይኑ_አስጠላችው፡፡ “ ይህችን ሴት ዓይኗን ማየት አልፈልግም : አስወጡልኝ::“ አለ፡፡ ተመለከትክ ወንድሜ ከሩካቤ በኋላ እንዲህ መጠላላትም አለ፡፡ #ኃጢአት_የምታስጎመጀው እስክንፈጽማት ነው፣ ከፈጸምናት በኋላ ግን #እንደሬት_ትመረናለች፡፡
🔸ያጡትን ሲያስቡ መፀፀትንና #ሰላም_ማጣትን ይፈጥራል፡፡

🔸ለተለያዩ በሽታዎች ፣ ላልታሰበ እርግዝና እና ውርጃ ያጋልጣል፡፡

🔸ለከፋ #የዝሙት_ተግባር ይገፋፋል፡፡

በአጠቃላይ #ስሜታችንን_ለመግለጽ#ስለምንተማመን_ብናደርግ_ችግር_የለውም#ፍቅራችን_እንዲፀና#ለመጠናናት… ወዘተ በሚሉ ምክንያቶች ድንግልናችንን ከትዳር በፊት ማጣት የለብንም፡፡ ስሜት_መግለጫ ሌሎች ብዙ መልካም መንገዶች አሉ፤ ከተማመንንም እሰየው ፣ ከትዳር በኋላ እንደርስበታለን፡፡ ሩካቤ የፍቅር ስሜታችንን ቢቀንስ እንጂ አይጨምርም፡፡ ለመጠናናትም የሚያስፈልገው ሩካቤ ሳይሆን የእጮኝነት ግዜ ማሳለፍ ነው፡፡

ወንድሞቼና እኅቶቼ #ፍቅራችሁ_እንዲበረታ#ትዳራችሁ_እንዲሰምር ፣ በዘመናችን እንደምናየው 80ቸውን በወሩ እንደሚቀዱት እንዳትሆኑ ፣ ከትዳር አጋራችሁም #እምነትና #እርካታ እንድታገኙ በድንግልና ኑሩ፡፡ ከእጮኛችሁም ጋር ከትዳራችሁ በፊት ሩካቤ ከማድረግ ተከልከሉ፡፡ “ መልካሙን የድንግልና ሥጦታዬን በጋብቻ ግዜ እሰጥሀለሁ/ሻለሁ/” ተባባሉ፡፡ ስለዚህ ድንግልናችንን እስከጋብቻ መጠበቅ የማንችልበት ምንም ምክንያት የለምና እንጠብቅ ፤ እንታገስ፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች #ድንግልናችንን_ያጣን ደግሞ ያለፈው አልፏል ፤ መመለስ አንችልም፡፡ ከአሁን በኋላ ላለው ግን #ታቅቦ መኖር ይገባል፡፡ “አንዴ አጥቼዋለሁና…” ብለን ካሰብን ግን ከማጣት የከፉ ዓዘቅቶች ውስጥ ያስገባናል፡፡ ድንግል ለሆናችሁ #ለተክሊል_ጋብቻ ፣ ድንግል ላልሆናችሁ #ለቁርባን_ጋብቻ ያብቃችሁ ፤ አሜን፡፡

🌾#ወስብሐት_ለእግዚአብሔር🌾

👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
         👇👇👇
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW
https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
        አንድ 60 ሰው የገደለ ወንበዴ👨‍🎤 ወደ አንድ አባት መጥቶ ንስሐ ስጡኝ 60 ሰው ገድያለሁ አላቸው እሳቸው አንተማ ሰይጣን 😈 ነህ ከኔ ራቅ ቢሉት እሳቸውንም ገደላቸውና ሄደ። ሌላ ቄስ አገኘ "አባቴ ንስሐ ይስጡኝ 60 ሰው ገድያለሁ ይህንንም ብዬ የጠየኳቸው ካህን ሰይጣን ብለውኝ እሳቸውንም ገድያለሁ " ካህኑም አንተ አረመኔ ? ?እኔንም ልትገለኝ ነውን? ቢሉት እሳቸውንም ገደላቸው በዚህ ሁኔታ ሌላ ሁለት ካህናትንም ገድሎ ወደ ለመደው ውንብዳናው እየሄደ ሳለ አንድ ሽማግሌ 👳‍♂ መነኩሴ ውኃ ሲቀዱ አገኘና አንቱ ሽማግሌ ይቁሙ አላቸው። "አቤት ልጄ" "60 ሰዎችን ገድዬ ንስሐ ልገባ ብጠይቅ አልፈቅድም ብለውኝ 4 ካህናት ገድያለው እርሶንም እርሶንም ንስሐ የማይሰጡኝ ከሆነ እገድሎታለሁ አላቸው። እሳቸውም ሥቅሰቅ ብለው አለቀሱለት " በእውነት #እግዚአብሔርን በድለሃል አስከፍተሃል ግን መሃሪ አምላክ ነው። "አሉት ከዛም ወደ ጉድጓድ ወሰዱትና " ላንተ እፀልይልህ ዘንድ የፀሎት መጽሐፌ 📖 እዚህ ወድቋልና አውጣልኝ " አሉት ከዛም ወደ ጥልቁ በገመድ አንጠልጥለው አስገቡት መግባቱን ሲያረጋግጡ ገመዱን ቆረጡ። "አንተ ሽማግሌ እገድልሀለሁ" እያለ መዛት ጀመረ ትተውት ሄዱ። ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ ቂጣና ውኃ ይዘው መጥተው "ልጄ እንዴት ነህ አሉት" እገድልሀለው አለ"። ምግቡን ሰጥተውት ሄዱ።  ከ12ሰዓት በኋላ ተመለሱ" ልጄ እንደምን አለህ " ደከም ባለ ድምጽ "እገድልሃለሁ አለቅህም " ምግብ ሰጥተውት ሄዱ ።
1 ቀን ቆይተው መጡ " ልጄ እንደምን አለህ " ሲሉት "እ..ገ..ድል..ሀለው" አለ እጅግ በደከመ ድምጽ ምግቡን ሰጥተውት ሄዱ አንድ ቀን ቆይተው ተመለሱና " ልጄ እንደምን ዋልክ" ሲሉት "እግዚአብሔር ይመስገን " አለ ትዕቢቱ በጾም ተሸነፈ ነፍስ ስጋን አሸነፈች እሳቸውም በገመድ አውጥተው ንሰሃን ሰጡት የአምላክ ባሪያ ሆነ ኖረ።
ለሁላችንም ፈርሃ እግዚአብሔር ትዕግስትን ማስተዋልን ይስጠን አሜን።
ትልቁ ነገር ደግሞ ለንስሐ ሞት ያብቃን ማለት ነው አሜን ያብቃን!!
      🙏🙏መልካም አዳር 🙏🙏
          
#ድምፀ_ተዋህዶ

👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
🐴የአህያዋ ፍትሀት
ለመንደሩ ሰው ውሃ እየቀዱ በሚያገኙት ገቢ የሚተዳደሩ አንድ አዛውንት👳 ነበሩ።ሥራቸው ባለቻቸው አንዲት አህያ ለአካባቢው ኅብረተሰብ ውሃ በመቅዳት የዕለት ጉርሳቸውንና የዓመት ልብሳቸውን ተጣጥሮ መሸፈን ነው። ጉልበቱ ከምላሱ ላይ የሆነ አንድ አለሌ መናፍቅ ውሃውን ሊቀዱ ሲወርዱና ሲወጡ ከመንገድ እየጠበቀ ማብቂያ በሌለው ንዝንዝ ሲያውካቸው ይኖራል።ከእለታት አንድ ቀን አህያቸው ትሞትባቸውና የውሃውን መቅጂያ እራሳቸው ተሸክመው ማመላለሱን ይቀጥላሉ። በሸክም ውሃ የሚቀዱትን ሽማግሌ የታዘበው መናፍቅ "አባቴ አህያዋ የት ገባች?" ይላቸዋል "አዬ! እሷማ ሞተች እኮ" ቢሉት "በጣም ያሳዝናል ለመሆኑ ፍትሐት ተፈጽሞላታል? የትስ ተቀበረች" አለ። ብልሁ ሽማግሌም "አዬ ልጄ!  አህያዋማ መናፍቅ ስለነበረች አልተፈታችም የጅብ ራት ሆና ቀረች" አሉትና እንደ እባብ በጥበብ አናቱን አሉት ይባላል"

#ድምፀ_ተዋህዶ

👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
🐁🐁የአይጦች ዕድሜ🐁🐁
          ------------------------
በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያስተምር አንድ መምህር ማስተማር ስልችት ብሎት ኖሮ አርባ አምስቷን ደቂቃ ቀልዶ ለመውጣት አሰበና ገና ወደ ክፍሉ እንደዘለቀ ጥቁሩን ሰሌዳ ጠርጎ ሲያበቃ በነጩ ጠመኔ በትልቁ "የአይጦች ዕድሜ" ስንት ነው ብሎ ጻፈና ተደላድሎ ተቀመጠ። ጉዳዩን ያልተረዱት ልጆች በልጅ አእምሯቸው እየተረባረቡ እኔ እኔ ይመልሱ ጀመር ......አንዱ 3 ሲል ሌላው 6 ይላል መምህሩ አይደለም እያለ ሌላኛውን ያስነሳል። እንዲህ እንዲህ እየተባለ ደቂቃዋ ስትጋልብ ብስጭት ያለው አንድ ተማሪ በመምህሩ ተናዶ በተማሪዋቹ አዝኖ ብድግ አለና "እኔ መምህር" ብሎ እጁን ያወጣል መምህሩም እንደለመዱት መስሏቸው በሹፈት እሺ አንተ ሲሉት "መምህር የአይጦች ዕድሜን በተመለከተ ይኽ የድመቶች ጉዳይ ነው እኛ ወደ ትምህርቱ ብንሄድ ይሻላል አለና ከሁሉም ተሽሎ ተገኘ።
💥💥💥💥💥💥💥💥💥
⭐️⭐️ዓላምህን ሊያደናቅፍብህ ከዓላማህ ሊያወጣህ የሚሞክር ዓላማ የለሹ ሥራ ፈት ሰው ሲያጋስጥምህ አብረህ መንገድ መሳት ሳይሆን ልትመስለው ይገባል።
........ውድ የድምፅ ተዋህዶ ተከታታዮች ከዚህ በታች ያለውን ለወዳጅዎ በመላክ እንዲቀላቀሉ ያድርጓቸው
 
#ድምፀ_ተዋህዶ

👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
👳ይፍቱኝ👳
አንድ በእድሜ ጠና ያሉ ካህን የከተማ አውቶብስ ውስጥ ናቸው አውቶብሱ ሞልቷል እንኳንስ መቀመጫ የእግር መቆሚያ ቦታ የለውም መቼስ መሳፈሩ ግድ ነውና ሰው በሰው ላይ ተዛዝሎ በሩም በግድ ተዘግቶ ጉዞው ቀጥሏል ካህኑ መቀመጫ በማጣታቸው የአውቶብሱን ብረት ይዘው ከወዲያ ወዲህ እየተወዛወዙ ሳለ አንድ የኪስ ቀበኛ በኪሳቸው እጁን ጥልቅ ሲያረግ ካህኑም የሌባውን እጅ ከኪሳቸው ጋር ጨምድደው ይይዙታል ይሄኔ ሌባው ኮስተር ብሎ ከካህን መስቀል እንደሚሳለም ምእመን ራሱን ወደ ምድር ዝቅ አድርጎ "ይፍቱኝ" ይላል የሌባው ድፍረትና ዓይን አውጣነት የገረማቸው ካህንም "ወቸው ጉድ እንኳን ተፈተህ ታስረህስ መች ተቻልክ" አሉት ይባላል "
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
የንስሐ መጀመርያው እየሠሩ ካሉውት ኃጥያት መለየት ነው #ማቴ ፳፮ ፣ ፸፭
ሰው ከእግዚአብሔር ምህረት መጠየቅ ያለበት የበደለውን ክሶ የቀማውን መልሶ ሊሆን ይገባል 👈
#ድምፀ_ተዋህዶ

👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌

❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
🔘እናንተን ባላውቃችሁ ...🔘
🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘

አንድ የቆሎ ተማሪ ወደ አንድ ትልቅ ከተማ ሄደና የድቁና መዕረግ ተቀብሎ በእግሩ ወደ ሀገሩ ሲሄድ ርሀብ ልቡን ያጠፋዋል።

እንደ አጋጣሚ ግን ሰዎች በደቦ ውለው በግምት ፰ሰዓት ሲሆን ሽውታ እንዳይመታቸው ነጠላ ተሸፋፍነው ምግብ ሲመገቡ ይደርሳል።

ተማሪውም "እንዴት ዋላችሁ ወገኖቼ" ሳይል ሰዎቹ የተሸፋፈኑትን ነጠላ ገለጥ አድርጎ አብሯቸው መብላት ይጀምራል።
ገበሬዎቹም ተገርመው "ተሜ አብረህ ማዕድ የምትቀርበው የት ታውቀናለህ?" ብለው ይጠይቁታል።

ተማሪውም ደበሎውን እያንጓፈፈ "እናንተን ባላውቃችሁ እህሉን አውቀዋለሁ" ብሎ እየቆረሰ ሲጎርስ ሰዎቹ "እውነቱን እኮ ነው ብለው ተገረሙበት"

(ቅኔና ቅኔያዊ ጨዋታ ለትዝታ)
🔺🔻🔺🔻🔺🔻🔺🔻🔺🔻

በፊት እንዲህ ነበር አሉ አሁን ላይስ?

#ድምፀ_ተዋህዶ

ትምህርቱን YouTube ላይ
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽

https://youtu.be/rkeWwC9MjMY
https://youtu.be/rkeWwC9MjMY
https://youtu.be/rkeWwC9MjMY
🕺  #እብዶቹ🕺
በአንድ ሀገር ሁለት እብዶች በጠራራ ፀሐይ ይከራከራሉ ሁለቱም እህል ውሃ የሚያሰኝ ዱላ ይዘዋል። የክርክራቸው ርእሰ ጉዳይ ፀሐይዋ ናት። አንደኛው እብድ "አሁን ከሌሊቱ ፮(6) ሰዓት ነው ካላመንክ ይኧው ጨረቃዋ ይለዋል" ሌላኛው እብድ " አይደለም ከቀኑ ፮(6) ነው!ይህች ጨረቃ ሳትሆን ፀሐይ ናት" ይላል በዚህ ሁኔታ ሲሟገቱ አንድ መንገደኛ አጠገባቸው ይደርስና እንዲያውም እሱ ይጠየቅ ብለው ሁለቱም እብዶች እየሮጡ ወደ መንገደኛው ተጠጉ "ይህች ፀሐይ አይደለችም?" አለ አንዱ እብድ ....ሁለተኛውም ቀጠለና "ይህቺ ጨረቃ አይደለች?" አለ .....አይደለችም አሁን ከቀኑ 6 ሰዓት ነው አለ የመጀመርያው እብድ "ኧረ አይደለም ከለሊቱ 6 ሰዓት ነው"አለ እሽ እሱ ይመስክር ተባባሉና ዝም አሉ። መንገደኛው ጨረቃ ናት ቢል ፀሐይ ነች ያለው በያዘው ዱላ አይለቀውም። ፀሐይ ነች ቢል ደግሞ ጨረቃ ናት ባዩ ማይለቀው ሆነ። ስለዚህ አውጥቶ አውርዶ "ወዳጆቼ እኔ እዚህ ሰፈር አይደለሁም ሌላ ሰው ጠይቁ" ብሎ ተገላገለ ይባላል
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
የተጠየቅነውን ጥያቄ ሁሉ እንደመጣልን ከመመለስ የጥሞና ጊዜ ወስደን ልንመረምር ይገባናል። ክርስቶስ አይሁድ የሚጠይቁትን የተንኮል ጥያቄ ሁሉ እንዴት ይመልስ እንደነበር መዘንጋት የለብንም።🙏🙏

#ድምፀ_ተዋህዶ

ትምህርቱን YouTube ላይ
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
🔸🔸🔸በጨው ደንደስ🔸🔸
              ~~~~
እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነው ዝሆንና ሚጥጥየዋ እንቁራሪት ጓድኝነት መሰረቱ። ይህ ባልከፋ ከእለታት አንድ ቀን አንድ ትልቅ ድልድይ ሲሻገሩ  እንቁራሪቷ ዘወትር እንደምታደርገው ዝሆኑ ትከሻ ላይ ቂብ አለች። ከእድሜው ብዛት የተነሳ ያረጀው ድልድይ ዝሆኑ ሲራመድበት ሲጢጥ እያለ ጩኸቱን አቀለጠው። ይኼኔ እንቁራሪቷ ወደ ዝሆኑ ጆሮ ጠጋ ብላ "ፐ! ድልድዩን አነቃነቅነው አይደል" አለች አሉ......
ድንቄም...
🐘🐘🐘🐘🐘🐘🐘
የክርስትና ጉዞ የማህበር፣የአንድነት፣የፍቅር ጉዞ ነው። በዚህ ጉዞ የዝሆንን ያህል አስተዋጽኦ ካላቸው በልጠው የእንቁራሪት ያህል አስተዋጽኦ ያላቸው ሰዎች መታበይ የለባቸውም።

ትምህርቱን YouTube ላይ
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
እንኳን ለብርሃነ  ዕርገቱ በሰላም አደረሰን።

"አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር  በመለከት ድምጽ አረገ።"
                መዝሙር ዘዳዊት 46፤5
❗️❗️❗️አስደሳች ዜና


የክረምት ልዩ የቤት ለቤት ስልጠና
።።።።።። ክራር
።።።።።።። በገና
።።።።።።። መሰንቆ
።።።።።።። ከበሮ
በሚፈልጉት ቀን እና ሰአት ከሰኞ እስከ እሁድ

❗️❗️እንዲሁም ለአንድ ወር የሚቆይ ዩቲዩብ ለመስራት ያሰባችሁ❗️❗️❗️❗️ ከመጀመርያ እስከ ገንዘብ ክፍያ ያለውን ሂደት አሰራር  በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሚሆኑበትን መንገድ እናሳያለን
☎️ +251900819497 ይደውሉ
💥  ታፍራለች 💥
ልጅቷ ባል ትፈልጋለች ሃይማኖቷ በሚፈቅደው ሕግና ስርዓት መሠረት ዘወትር ወደ እግዚአብሔር ትጸልያለች። ዳሩ ግን አንድም ቀን እግዚአብሔርን በቀጥታ ጥሩ ባል ጥሩ ትዳር እንዲሰጣት ለምናው አታውቅም። ለምን ቢባል ታፍራለች። "እግዚአብሔር እንዴት ስለ ባል ይጠየቃል?" የሚል ደካማ አመለካከት አላት። እግዚአብሔርንም ጥሩ ባል ስጠኝ ብላ መለመን ያሳፍራታል። እንዳትተወው ደግሞ ባል ያስፈልጋታል። ታድያ አንድ ቀን ሲጨንቃት እንዲህ ብላ ጸለየች፤ "ፈጣሪዬ እባክህን ለእናቴ ጥሩ አማች ስጣት"
😊😊😊😊😊😊
በእርግጥ እግዚአብሔርን ስንለምን "የምትለምኑትን አታውቁምን" ተብለው እንደተወቀሱት ሰዎች እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን። ለብዙዋች ግን የሚያሳፍረው ሳያሳፍራቸው፤ የማያሳፍረው ያሳፍራቸዋል

#ድምፀ_ተዋህዶ

ትምህርቱን YouTube ላይ
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
❖ ሰኔ ፲፪ ❖

✞ ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት [በነገዱ ውስጥ፥ በመላእክት ሁሉ ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት..፣ በእስክንድርያ ከተማ ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት..፣ የሞት መልእክት የተጻፈባትን የቅዱስ ባሕራንን ደብዳቤ የለወጠበት..፣ ቅድስት አፎምያን ያዳነበት..፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ምሕረትን የሚለምንበት..በእለኚህ ምክንያት ነው በዓሉን የምናከብረው] ✞

"ሰላም ለሚካኤል መሐሪ ውእቱ፤ ወተአዛዚ ለሰብእ በዲበ ሠናይቱ፤ ለቀርነ ዝንቱ መልአክ በድምፀ ንፍሐቱ፤ በከመ ኮነ ቀዳሚ ውስተ ሰማያት ዕርገቱ፤ ለእግዚአብሔር ይከውን ዳግመ ምጽአቱ።"

ትምህርቱን YouTube ላይ
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
🐂🐂🐂🐂🐂
ሰውየው ሌሊቱን ሙሉ በቅዥትና በፍርሃት አሳልፎ በማለዳ ጎረቤቱ ከሆኑ የእድሜ ባለጸጋ 👳👳ይቀርብና ቅዥቱን ያስረዳል። አባቴ ዛሬ ሌሊት ስጨነቅ ነው ያነጋሁት አንድ ቀንዳም በሬ🐂🐂 እየመጣ በትኛሁበት መልሼ ካልወጋሁ ይለኛል። እኔም ቀንድና ቀንዱን ይዤ እታገለዋለሁ.......ስነቃ ግን ላብ በላብ ሆኜ ራሴን አልጋዬ ላይ አገኘዋለሁ..........ተረጋግቼ  ስተኛም ያንኑ አያለሁ በዚህ ሁኔታ ሌሊቱን ሁሉ ስሰቃይ ነው ያደርኩት። ይልና ምላሽ በሚጠብቅ ተስፋ ሽማግሌውን ያያል። ሽማግሌውም ትንሽ ጊዜ በዝምታ ቆዪና ለመሆኑ የምትተኛው ምን ላይ ነው ብለው ጠየቁት ሰውየውም የሣር ፍራሽ ላይ ነው አባቴ ሲል ይመልሳል። ሽማግሌውም ቀልደኛ ኖረው ታዲያ ምን ይደረግ ምግቡ ላይ ተኝተህበት አሉት ይባላል።
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ዝንብን የሚሰበስባት ቆሻሻ መሆኑ ግልጽ ነው። አንዳንዴ ለሰይጣን ታማኝ አገልጋይ በመሆናችን ምክንያት የሚመጣብንን መከራ ተሳቀን እግዚአብሔርን ድረስልኝ እንለዋለን። ሁላችንም ከክፉ ሥራ እንላቀቅ እንጸልይም።....ጴጥሮስ ጌታን ከካደበት ግቢ ወጥቶ ምርር ብሎ እንዳለቀሰ.....ሉቃ 22÷62

#ድምፀ_ተዋህዶ

ትምህርቱን YouTube ላይ
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
👹👹👹ሰይጣን👹👹👹
አንድ ጊዜ እቡይ ሰው እራሱ ብቻ በሚያውቀው ጉዳይ ከነ ጫማው ዛፍ ላይ ለመውጣት ይታገላል። የሰውየውን ድርጊት ባሻገር ሆኖ ሲታዘብ የነበረውና የልቡን ጥመት የተረዳው ሰይጣን ለመንደሩ ሰው አሰምቶ /ጮኾ/ "ይህንን ምክንያታም ሰው እዩልኝ ከነጫማው ዛፍ ላይ ለመውጣት ሲታገል.....በኋላ ቢወድቅ ሰይጣን ነው የጣለኝ ሊል ነው......" አለ ይባላል።
😁😁😁😁😁😁
አንዳንድ ሰው ራሱ ከሚፈጥረው ሰህተትና ውጤቱ ራሱን ከመውቀስ ይልቅ ማላከክ ይቀናዋል።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ሁላችንም ራሳችንን እንይ፣ ራሳችንን እንውቀስ።
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸

#ድምፀ_ተዋህዶ

ትምህርቱን YouTube ላይ
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡ በሌላ አገላለጽ ብነግራችኁ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ጾመ ሐዋርያት (ሰኔ ጸም) ነገ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም
(JUNE 23/2024 G.C) ይገባል፡፡

#ድምፀ_ተዋህዶ

ትምህርቱን YouTube ላይ
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 pinned «#ሥርዓተቤተክርስቲያን!!! #ጥያቄ፡- በቤተ-ክርስቲያናችን አስተምህሮ ለጋብቻ የሚፈቀደው አንድ ወንድ ለአንድ ሴት ነው፡፡ እና አንድ ልጅና አንዲት ልጅ ከልብ ተዋድደው ሊጋቡ ነው፡፡ ከመዋደዳቸው የተነሳ ሳይተያዩ ካደሩ ምግብ አይቀምሱም፡፡ ሥራ መሥራት አይችሉም፡፡ ብቻ ስሜት የሚባለው ነገር በጣም ገኖባቸዋል፡፡ በቤተ-ክርስቲያችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል? ነው ወይስ የራሱ እስከሆነች…»
👆👆 #ወደ #ላይ #እይ  👀
             ---------------------
ሌባው ከአንድ ግቢ ይገባል።ጊዜው ጨለማ ነው። የግቢው ባለቤት እግቢው ከሚገኘው ዛፍ 🌴🌴ላይ ወጥቶ ሌባውን ይመለከታል። ሌባው እሮጦ መጥቶ ዛፉ ሥር ቆመ። አሁን ባለቤት ከላይ ሌባ ከታች ሆነዋል። ሌባው አያይም ባለቤት ግን ሌባውን ያየዋል። ሌባው ዛፉ ሥር እንደቆመ ቅኝት ይጀምራል። ወደ ፊት፣ ወደ ኋላ ወደ ቀኝና ወደ ግራ እየተዟዟረ ዐየ.......ይሄኔ የቤቱ ባለቤት እዛፍ ላይ ሆኖ አንዲት የዛፍ ፍሬ ወደ ታች ለቀቀበትና ፍሬዋም የሌባውን አናት ዳብሳ ወደቀች። ይሄኔ ሌባው ቀና ብሎ ወደ ላይ ዐየ። ከቤቱ ባለቤት ጋርም ተፋጠጠ ......የቤቱ ባለቤትም "ሁሌ ልትሰርቅ ባሰብክ ጊዜ "ወደ ቀኝና ወደ ግራ ብቻ ሳይሆን ወደ ላይም ማየት እንዳለብህ ላስታውስህ ፈልጌ ነው" አለው ይባላል።
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
#ሰው አያውቅብንምና ዐያየንም ብለን የምን ሠራውን መጥፎ ሥራ ሁሉ #እግዚአብሔር ያውቅብናል ብለን ልንተወው ይገባል። ክርስቲያን በሁሉ ቦታ ታማኝ ነው። ዐይነ ስጋችንንም ሆነ ዐይነ ልቡናችንን ሁልጊዜ ወደ ላይ ወደ እግዚአብሔር ልዕልናና ክብር ሊያይ ይገባል።
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

ትምህርቱን YouTube ላይ
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
         የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
💚💚💚💛💛💛❤️❤️❤️
 
እንካን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አምታዊ በ ዓል አደረሰን:: ስምሽ ጉልበት ሆኖኝ ወጣሁት ዳገቱን  ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ አለፍኩት ዳገቱን::

    #መልካም እለት

     #ድምፀ_ተዋህዶ
2024/06/28 23:04:27
Back to Top
HTML Embed Code: