Telegram Group Search
በምሥጋና ዐረገ፤ ቤተ ክርስቲያኑንም ከፍ ከፍ አደረጋት።
***
እየታያቸው ከፍ ከፍ አለ፤ የባሕርይ ክብሩን የምታመለክት ደመና ተቀበለችው። በእርሱ ዕርገትም አካሉ የሆነች ቤተ ክርስቲያን በእርሱ ሆና ከፍ ያለች እና በሰማያዊ ሥፍራ የተቀመጠች ሆነች።
የዚህ ዓለም ኃያላን የሚያናንቋት ሐረገ ወይን የተባለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥሯ በምድር ቢሆን ቅርንጫፎቿ በሰማይ ናቸው። ይህ ምን ይደንቅ!
አንዳንድ አገልጋዮቿ በሥርዓተ አምልኮዋ በዘፈቀደ እና በቸልተኝነት የምንመላለስባት ቤተ ክርስቲያን በመንቀጥቀጥ የሚያገለግሉ ሰማያውያን መላእክት ጋር ኅብረት ያላት ናት። በላይ በበጉ ዙፋን የምትቀድስ ናት! ለዚህ ጸጋዋ አንክሮ ይገባል!
ይህ ሁሉ የሆነው ግን ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ አባቱ ያቀርበን ዘንድ በእኛ ሥጋ ከፍ ከፍ ብሎ በአብ ቀኝ በመቀመጡ የተሰጠን ጸጋ ነው።
***
"እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።
ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።
እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥
ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።"
***
(ሉቃ. 24፥50-53)
ከንቱ ውዳሴን አልወድም ያለ ሰው ሲሰድቡት ከተከፋ በከንቱ ውዳሴ ላይ ውሸታምነትን ደርቦ የያዘ መሆኑን እንረዳለን። ሲሰድቡት ለምን ተሰደብኩ ብሎ ለክብሩ የሚጨነቅ፣ አንድ ሰው ክፉ ቃል ተናገረኝ ብሎ የሚቦልክ ወይም ከጓደኝነት የሚያወጣ ሰው ሐዋርያዊ አይደለም። ሐዋርያት ጌታን ሲከተሉ መጀመሪያ እከብር ባይ ልቡናን ትተው ነው። እውነትን በመናገራቸው የደረሰባቸውን ነቀፋ፣ ስድብ፣ መደብደብ፣ በሰይፍ መቀላት በደስታ ተቀብለውታል እንጂ አላጉረመረሙም። ሐዋርያዊ የሆነ ሰው መሪው ክርስቲያናዊ ዓላማው ነው እንጂ የሰዎች ሙገሳና ጩኸት አይደለም። ከንቱ ውዳሴን አምርረን መጥላት አለብን። መመስገን ያለበት በሁሉ ፍጹም የሆነ እግዚአብሔር ነው። አንድም ተጋድሏቸውን ጨርሰው በአፀደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳን ናቸው። ክርስቲያን እንደ ጌታው ከምድር ከፍ ብሎ መውጣት (ማረግ) ይገባዋል። ሐዋርያት የሰውን ሙገሳ ንቀው የኖሩት ከሰው ተለይተው እንደ ጌታቸው ከፍ ከፍ ብለው በመውጣታቸው ነው።

በሰማይ የሀሉ ልብክሙ
በሰማይ የሀሉ ልብነ

© በትረማርያም አበባው
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "እኔ ሕይወት ነኝ" ብሏል

ክርስቶስ 'እኔ ሕይወት ነኝ' ሲል እውነተኛ ሕይወት በእርሱ ተጀምሯል፣ በእርሱም ትቀጥላለች፣ እናም በእርሱ ያበቃል ማለት ነው። በክርስቶስ አምኖ በእርሱ የሚኖር ሁሉ የዘላለም ሕይወትን ያገኛል፣ እርሱ የማይጠፋ የሕይወት ምንጭ ነውና…

ክርስቶስ ሕይወት ነው ምክንያቱም በኃይሉ ከሞት በመነሣቱ እና በትንሣኤው የዘላለም ሕይወትን መንገድ ስለጠራልን። ከክርስቶስ ጋር ያለን አንድነት ከሕይወት ጋር ያለን አንድነት ነው፣ ዐዲስ እና ክቡር ሕይወት እንድንኖር ብርታት ይሰጠናልና…

በክርስቶስ ያለው ሕይወት እውነተኛ ሰላምና ደስታ የተሞላ ሕይወት ነው። በክርስቶስ ስንሆን፣ ሕይወትን በፍፁም ትርጉሙ፣ ከሞት በላይ የሆነና ጊዜን የሚጋፋ ሕይወት እናገኛለን።

አቡነ ሺኖዳ
“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል።”
(ያዕ. 4፥8)
***
የመልካም ነገር ጅማሮ ከማን ነው? ከእግዚአብሔር ወይስ ከሰው? የዚህ ጥያቄ መልስ ግልጽ ነው፦ የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ከእግዚአብሔር ነው። ታዲያ ያዕቆብ በመልእክቱ "ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል፤" ብሎ ሲናገር መቅረብ ከሰው የሚጀምር ይመስል የእኛን ኃላፊነት ቀድሞ መናገሩ ለምንድር ነው? ብለን እንጠይቃለን። መልሱ የሚከተለው ነው፦ እግዚአብሔርማ ሁሉን ፈጽሞ ትቀበለው ዘንድ እየጠበቀን ነው። ከሰው በኩል ግን መቀበል ይገባል። እንዴት ነው የምንቀበለው? በእምነት፣ በንስሐ፣ ከኃጢአት ጋር ተጋድሎ በማድረግ እና በክርስቶስ ትእዛዛት ለመኖር በመጣር ነው። እነዚህ ነገሮች የጸጋ ሁሉ ምንጭ ወደሆነው እግዚአብሔር ለመቅረብ ጽኑ ፈቃዳችን በውስጥም በውጭም የምንገልጽባቸው ናቸው። እግዚአብሔር በእንዲህ ያለ ተግባር ውስጥ ሲያየን በእኛ ጥረት ሊገኝ የማይችለውን ዘላለማዊ ድኅነት ያጎናጽፈናል፤ የጸጋ አማልክት እስክንባል ደርሰን የእርሱ ጸጋ የሞላብን ያደርገናል። በእርሱ ዘንድ በባሕርዩ ያለ ቅድስናን ወደ እርሱ ቀርበን እናገኘው ዘንድ ይሰጠናል። ይህን ሁሉ የምናገኘው ከእኛ ብቃት ሳይሆን ከእሱ ጸጋ ነው፤ ነገር ግን በየጊዜው በምናደርገው የእምነት መታዘዝ እና ተጋድሎ ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ እና እርሱን ለመምሰል ያለነን በተግባር የተፈተነ ጽኑ ፈቃድ እንገልጣለን።
***
“ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።
ተጨነቁና እዘኑ አልቅሱም፤ ሳቃችሁ ወደ ኀዘን ደስታችሁም ወደ ትካዜ ይለወጥ።
በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል። ...
እንግዲህ በጎ ለማድረግ አውቆ ለማይሠራው ኃጢአት ነው።”
***
(ያዕ. 4፥8-12)

Bereket Azmeraw
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በበዓለ ኀምሳ ምንባብ ላይ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ስለተባለበትና ተስፋ በተሰጣቸው በኀምሳኛው ቀን ወርዶ ስለ ሠራው ሥራ እንዲህ በማለት ያብራራል። ‹‹ወመንፈስ ቅዱስኒ ኢተሰምየ ጰራቅሊጦስሃ ዘእንበለ አመ ይቤሎሙ እግዚእ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ እፌኑ ለክሙ ካልአ ጰራቅሊጦስሃ። ጰራቅሊጦስ ብሂል ናዛዚ ብሂል በነገረ ጽርዕ ……መንፈስ ቅዱስም ጌታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሌላውን አጽናኝ እልክላችኋለሁ›› ከማለቱ በፊት ጰራቅሊጦስ አልተባለም ጰራቅሊጦስ ማለት በጽርዕ ቋንቋ አጽናኝ ማለት ነው ስለምን አጽናኝ ተባለ ደቀ መዛሙርቱ ወልድ ካረገበት ቀን ጀምሮ ጰራቅሊጦስ እስከ ወረደበት ቀን ድረስ  ያለቅሱ ነበረና ስለዚህም ወልድ መንፈስ ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አለው። የስሙ ትርጓሜ ግን አስቀድመን እንደተናገርነው አጽናኝ ማለት ነው። (ዮሐ. ፲፬፥፲፭)
በዓለ ጰራቅሊጦስ የሚከበረው ርደተ መንፈስ ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመሆኑ ምክንያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል ነው፤ በዕለቱም ኢየሩሳሌም በተባለችው ቤተክርስቲያን ስለመጽናት፤ ከግለኝነት ይልቅ መንፈሳዊ አንድነትን ስለማስቀደም እና ስለመጸለይ  እንማራለን፡፡
በዓለ ትንሣኤውን በቸርነቱ በሰላም እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ጠበቀን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ሆነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን፤ ፆሙን የበረከት የምህረት የቸርነት ያርግልን አሜን፡፡
"የእግዚአብሔር ጸጋ የምትሰጠው እምነታቸውን ለሚናገሩት ሳይሆን እምነታቸውን ለሚኖሩት ነው።"
~ ቅዱስ ጎርጎሪዎስ ነባቤ መለኮት

“በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ።”
  — 1ኛ ዮሐንስ 3፥18
የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን መስማት ቤተ ክርስቲያንን መስማት ነው ምክንያቱም ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን አንደበቶች ናቸውና
መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በነቢያት በኋላም በሐዋርያት በኩል እንደተናገረ ዛሬም በተለያዩ መምህራን አድሮ ያስተምራል

በዘመናችን ርቱዕ አንደበት ከዕውቀት ጋር
ትሕትና ከትጋት ጋር
ቅንነት ከሊቅነት ጋር የተባበረላቸው አራት ዓይናው ሊቅ ሊቀ ሊቃውንት ዮሴፍ ደሳለኝ
#ዳቤር በሚል የሚዲያ አማራጭ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራእየ ዮሐንስ በተከታታይ ሊያስተምሩን መጥተዋል
ስለሆነም ይህንን ከታች የተያያዘውን ሊንክ በመጫን ወይም ዳቤር ብለን #youtube ላይ #search በማድረግ እና #Subscribe በማድረግ ሊንኩን ለሌሎችም በማጋራት እንድንከታተል ተጋብዘናል ።
ሊቃውንቱን ወደ መገናኛ ብዙኃን መረብ በማምጣት እናበረታታ

https://youtube.com/@yosef-daber?si=-jwo1UTiPZRMfOte
ወላዲተ_አምላክ_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
352.7 KB
ወላዲተ አምላክ

*እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም "ወላዲተ አምላክ" ትባላለችን? ለምን?

* "ወላዲተ አምላክ" የቃሉ ትርጉም

* የቃሉ ነገረ መለኮታዊ ፋይዳ

* የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት በመጽሀፍ ቅዱስ ትምህርት

* የእመቤታችን ወላዲተ አምላክነት-በቀደምት አበው ትምህርት

+++++++++~~~+++++++

ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስ “ወላዲተ አምላክ” የሚለውን መቃወሙ በነገረ ክርስቶስና በነገረ ድኅነት ላይ የሚያስከትለው ነገር መሠረታዊ የሆነ ኑፋቄ መሆኑን በሚገባ አስረድቷል፡፡ እነዚህን ነገሮችም እንደሚከተለው በሚገባ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡-

ከድንግል ማርያም የተወለደው አካላዊ ቃል የእኛን ባሕርይ ነሥቶ (ተዋሕዶ) ሥግው ቃል ካልሆነና ሰው ብቻ (ዕሩቅ ብእሲ) ከሆነ መዳናችን አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ ምክንያቱም ክርስቶስ የተቀበላቸው ሕማማትና መከራዎች የሥግው ቃል (ሥጋን የተዋሐደውና የእኛን ባሕርይ ባሕርዩ አድርጎ ሰው ሆኖ በሥጋ የተገለጠው አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል) ሕማማትና መከራዎች ሳይሆኑ የዕሩቅ ብእሲ (የስው ብቻ) ይሆናሉና፡፡ ፍጡር በሆነ በሰው ብቻ መዳን አይቻልምና ስለዚህ ድነናል ማለት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ወላዲተ አምላክ የሚለውን ቃል መካድ የአምላክን ሰው የመሆን ምሥጢር (ምሥጢረ ሥጋዌን) እና የሰውን መዳን መካድ ነው፡፡

እንደዚሁም አካላዊ ቃል አዲሱን ሰው ዳግማዊ አዳምን ለመፍጠር አካላዊ ቃል ከእኛ ባሕርይ ጋር ሊያደርግ የሚያስፈልገው ተዋሕዶ፡ ንስጥሮስ እንዳለው ዓይነት አፍኣዊና የጉርብትና ዓይነት ዝምድና ሳይሆን፣ ውሳጣዊና ባሕርያዊ የሆነ ጥብቅ እና አማናዊ የሆነ ተዋሕዶ ያስፈልገው ነበር፡፡ ይህ አይደለም ከተባለ የባሕርያችን መታደስ፡ በሐዲስ ተፈጥሮ የመዳናችን ነገር ሁሉ ከንቱ ይሆናል፡፡

#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
2. መዳናችንን እንፈጽማለን
3. እንድናለን
«ወንድምህን አትናቀው»

ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል። "እንዴት?"  ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እሱን ናቅኸው ማለት ክርቶስን ናቅኸው ማለት ነው። ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም። ስለዘህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
" ካንተ ጋር ተዋህጄ ምሥጢር ከማየት የከለከለችኝ ኃጢያቴን አርቅ ዘንድ ካንተ ጋር አንድነትን ስጠኝ፤ በንጽሐ ሥጋ የሚሰጥ ልዩ ብርሃንህን በመዋሃድ ደስ ይለኝ ዘንድ፣ በንጽሐ ነፍስ በሚሰጥ ልዑል ስፉህ በሚሆን ብርሃን በንጽሐ ልቦና በሚሰጥ በረቂቅ ብርሃንህ ደስ ይለኝ ዘንድ፤ መልክህን ከማየት የሚከለክሉኝ ሰይጣናት እንዳያዩኝ፣ አቤቱ ልቦናዬ በዚህም ዓለም ግብር በማሰብ እንዳይደክም ጌትነትህን ብርሃንህን ለማየት እንድማረክ አድርገኝ፤  አቤቱ ከፍቅርህ ሊለየኝ የሚቻለው አይኑር፤  የመላእክት ክብራቸው ዕውቀታቸው ተድላ ደስታቸው፣  ሁልጊዜ ጌትነትህን የሚያመሰግኑ ሁልጊዜ በፍቅርህ የሚቃጠሉ በፍቅርህ ብርሃን ገጽ ልቡናቸው የሚያሸበርቅ፣ ከሁሉ በምትበልጥ ተዋህዶ ካንተ ጋር በመዋሃድ ፊታቸው የሚያሸበርቅ፣ እውነት ነው፤ አቤቱ ሀብታት ምሥጢራትህን  ካንተ እሻለሁ፤ አንድነትህን ሦስትነትህን የማውቅበትን ዕውቀት በልቡናዬ ትገልጽ ዘንድ እማልድሃለኁ። "

አረጋዊ መንፈሳዊ
ቅዱስ ጳውሎስን በትክክል ስለመረዳት
***
ሐዋርያው በገላትያ እና ሮሜ መልእክቶቹ ስለ 'ኦሪት ሕግ' የተናገራቸው ጉዳዮች አሉ። አነዚህን ነገሮች በትክክል ለመረዳት ሐዋርያው ከማን ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል። ጉዳዩ ከአይሁድ ዘመም ክርስቲያኖች ጋር ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ሕጉ የተሰጠበትን ዓላማ በሚገባ አና በጥልቀት ካልተረዱ ሰዎች ጋር ነው ጉዳዩ። የመጀመሪያው ያልተረዱት ጉዳይ ሕግ እስራኤልን ከሌሎች አሕዛብ ለመለየት የተሰጠው ተግባር ማብቃቱን እና አሕዛብም በአብርሃም በኩል የተገባላቸው ኪዳን መድረሱን ባለመረዳት በክርስቶስ አንድ ሆነው ሲያበቁ ከአይሁድ የመጡት ከአሕዛብ ከመጡት ለመለየት ሕጉን መጠቀም መፈለጋቸው ነው። ያ ተፈጽሞአል። ክርስቶስ እስራኤልን ከአሕዛብ የሚለየው ሕግ ፍጻሜ ነው፤ ለሁሉም መጥቶአልና። ሁለተኛው ደግሞ ሕግ ያለ ክርስቶስ ማዳን እና ጸጋ ብቻውን ሊያድን እንደማይችል በመዘንጋታቸው እና ከክርስቶስ ማዳን ጋር ማፎካከራቸው ነው። ሕግ ኃጢኣትን በመግለጥ እና መርገምን በማምጣት ለሞት አሳልፎ ይሰጣል። ይህ የሆነው ሕጉ መጥፎ ሆኖ ሳይሆን የሰው ልጅ የነበረበት የድካም ሁኔታ ያደረገው ነው። በክርስቶስ ማዳን መንፈሳዊ ጸጋ ሲሰጥ ግን ሕጉ የባርነት መሆኑ ቀርቶ 'የሕይወት እና የእምነት ሕግ' ሆነ። በቀድሞ ሁኔታው 'የሞት ሕግ' ያለውን በአዲሱ ሁኔታ 'የክርስቶስ ሕግ' እያለ መጥራት ጀመረ። በመሆኑም ሕጉ በክርስቶስ አዲስ ኃይል እና ተግባር እንዳገኘ ተናገረ። ሕጉ አሁንም እንደሚጠቅም ግን ደጋግሞ ተናግሮአል። "ኃጢኣት በሕግ ይታወቃልና" በማለት ሰዎች ኃጢኣት የሆነውን ለይተን እናውቅ ዘንድ ሕጉ የግድ እንደሚያስፈልገን ተናግሮአል። (ሮሜ. 3፥20) በመሆኑም የቅዱስ ጳውሎስ ችግር 'ቅዱስ፣ ጻድቅ እና በጎ' ብሎ ከጠራ ከሕግ ጋር ሳይሆን ሕጉን በተሳሳተ እና ግልብ በሆነ መንገድ ከተረዱ ሐሰተኛ ወንድሞች ጋር ነበር። (ሮሜ. 7፥12)
የሚያሳዘው ግን የ15ኛው መ/ክ/ዘመን የተሐድሶ አራማጆችም በዚሁ መሰናክል መውደቃቸው ነው። ቅዱስ ጳውሎስን ከትክክለኛው መልእክታቱን በጻፈበት ዘመን ከነበረው ነባራዊ ዓውድ አንጻር ሳይሆን በመካከለኛቹ ዘመናት በሮም ቤተ ክርስቲያን የነበረው ቀውስ በፈጠረው ሌላ ዓውድ ለመረዳት የመሞከር ስህተት ፈጽመዋልና።
Dn. Bereket Azmeraw

ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን #በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።

በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።

ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ  በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!

#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ)
2024/07/04 14:53:52
Back to Top
HTML Embed Code: