Telegram Group Search
#የወጣቱን_ሕይወት_እንታደግ

የ23 አመት ወጣት ነው ሙሴ አሻግሬ ይባላል ተወልዶ ያደገው ወልድያ ከተማ ሲሆን ዛሬ ላይ ሁለት ኩላሊቶቹ መስራት አቁመው የኩላሊት የንቅለ ተከላ ህክምና አስፈልጎት አድኑኝ እያለ ይማጸናል።

እህቱ ፍሩታ አሻግሬ አረብ ሀገር ተንከራትታ ያጠራቀመችውን ገንዘብና ያላትን ጌጣ ጌጥ ሳይቀር ሽጣ ስታሳክም ነበር። አሁን ላይ ሳትሰስት ኩላሊቷን ለወንድሟ ለመስጠት ኢትዮጵያ ገብታለች።

እናም እናንት ደጋግ ኢትዮጵያውያን ይህንን ወጣት ህይወቱን ለማትረፍ አነሰ በዛ ሳትሉ የእርዳታ እጃችሁን ትዘረጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
                   ፍሩታ አሻግሬ
             የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
              1000629004045

ለበለጠ መረጃ
➛ ፍሩታ አሻግሬ - 0969886929
➛ ደህንነት አሻግሬ - 0925009689
+ የተሠጠህን ቁጠር +

ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው። የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም። ዕባብ ደግሞ የስይጣን አንደበት ነበረ።

ሰይጣን እንዲህ አላት:- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም። የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው:: ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ። ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ።

ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም። ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር። ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቷት ሔደ። ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች። የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች።

ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል

በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን። ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ። ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ። አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ። ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር።

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ቆመና "ጌታ ሆይ ተመልከት እጆቼ ንፁሃን ናቸው። ደም አላፈሰሱም የሰው ገንዘብ አልቀሙም" አለ እግዚአብሔርም መለሰለት "ልጄ ሆይ! አዎ እጆችህ ንፁሃን ናቸው ግን ባዶዎች ናቸው" አለው ይባላል።

ያልገደለ እጅ ግን ያላዳነ፣ ያልሰረቀ አጅ ግን ያልመፀወተ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ የለውም። እውነተኛው መልካምነት ክፋ አለማድረግ ብቻ ሳይሆን መልካም ማድረግም ነው። የሚጎዳንን መተው ብቻ ሳይሆን ስለ ሌሎች ጥቅም መድከምም ነው።
#የወጣቱን_ሕይወት_እንታደግ

የ23 አመት ወጣት ነው ሙሴ አሻግሬ ይባላል ተወልዶ ያደገው ወልድያ ከተማ ሲሆን ዛሬ ላይ ሁለት ኩላሊቶቹ መስራት አቁመው የኩላሊት የንቅለ ተከላ ህክምና አስፈልጎት አድኑኝ እያለ ይማጸናል።

እህቱ ፍሩታ አሻግሬ አረብ ሀገር ተንከራትታ ያጠራቀመችውን ገንዘብና ያላትን ጌጣ ጌጥ ሳይቀር ሽጣ ስታሳክም ነበር። አሁን ላይ ሳትሰስት ኩላሊቷን ለወንድሟ ለመስጠት ኢትዮጵያ ገብታለች።

እናም እናንት ደጋግ ኢትዮጵያውያን ይህንን ወጣት ህይወቱን ለማትረፍ አነሰ በዛ ሳትሉ የእርዳታ እጃችሁን ትዘረጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
                   ፍሩታ አሻግሬ
             የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
              1000629004045

ለበለጠ መረጃ
➛ ፍሩታ አሻግሬ - 0969886929
➛ ደህንነት አሻግሬ - 0925009689
+ መልአኩ ነው +

ሰዓቱ ሌሊት ነው ፤ እንደ አጋጣሚ ሆኖ በዚያ ሌሊት መላው የቤተሰባችን አባል አምሽቶ እየተጫወተ ነው፡፡ ከዚህ የቤተሰብ ስብስብ መካከል ሳይገኝ የቀረው አንድ በወኅኒ ቤት የታሰረ ወንድማችን ብቻ ነበር፡፡ ድንገት ግን የጊቢው በር በተደጋጋሚ ተንኳኳና ሁላችንም ጨዋታችንን አቋረጥን፡፡ በሌሊት የሚያንኳኳው ማን ነው ?

ሠራተኛችን ሮጣ ሔደች:: ወዲያው ግን በሩን ሳትከፍተው ተመልሳ እየሮጠች መጣች፡፡ በደስታ ሰክራ ‹‹የታሰረው ልጃችን በር ላይ ቆሟል!›› ብላ ተናገረች፡፡ "በድምፁ አወቅኩት!› እያለች ዘለለች፡፡ ከሁኔታዋ የተነሣ ‹አብደሻል እንዴ!?› አላት ቤተሰቡ ሁሉ፡፡

እስዋ ግን በእርግጠኝነት ተናገረች! በቀን የታሰረው ልጅ በሌሊት ተፈቶ መምጣቱ ፈጽሞ ሊታመንን የማይችል ነገር ነው፡፡ ቤተሰቡ ሁሉ የታሰረው ልጅ መጣ ብሎ አላመነም፡፡ ባይሆን የመንግሥት ወታደሮች የቀረነውን ሊወስዱን ይሆን? ማን ሊሆን ይችላል? ብሎ ተብሰለሰለ:: በመጨረሻም የሁሉም ግምት አንድ ነገር ላይ አረፈ:: ሁሉም ሰው በአንድ ድምፅ አንድ ቃል ተናገረ "መልአኩ ነው!"

መልአኩ የሰው ስም አይደለም:: ቤተሰቡ የተስማማው "ደጅ የቆመው የታሰረው ልጃችን ሳይሆን እሱን ለመጠበቅ ከእግዚአብሔር የተሠጠው ጠባቂ መልአኩ ይሆናል›› ብሎ ነበር፡፡ የበሩ መንኳኳት አሁንም ስላልቆመ ቤተሰቡ ግር ብሎ ወጣና ተቻኩሎ በሩን ከፈተ፡፡ በደጅ የቆመው ግን እንደተባለው የታሰረው ልጅ ራሱ ነበር፡፡ ሁሉም ተደሰተ!!!

ይህ ገጠመኝ በአሁን ዘመን የተፈጸመ ነው ብዬ ብናገር ማን ያምነኛል? እውነት በሌሊት የቤታችን በር ሲንኳኳ መልአክ ነው ብለን እንገምታለን? ይህ ቤተሰብ ምን ዓይነት ቤተሰብ ነው?

በብዙዎቻችን አእምሮ ውስጥ መጀመሪያ የሚመጣው ጥርጣሬ ‹ሌባ ሊገባ ይሆን?› የሚል ስለሚሆን ዱላ ፍለጋ እናማትራለን፡፡ ወይ ደግሞ ሌሊቱ ወደ መንጋቱ እየተቃረበ ከሆነ ‹‹የምን መርዶ ሊያረዱኝ ይሆን? የቱ ዘመዴ ሞቶ ይሆን?› የሚል ጭንቀት ይፈጠራል፡፡

‹የሚያንኳኳው የእግዚአብሔርመልአክ ይሆናል› ብሎ የሚጠረጥር ሰው ግን በዚህ ዘመን ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ እንዲህ ብሎ ግምቱን የሚናገር ሰው ከቤተሰባችንመካከል ቢገኝ እንኳን እንደ ዕብድ ልንቆጥረው እንችላለን፡፡ ታዲያ ይህን ገጠመኝ ከየት አመጣኸው ትሉኝ ከሆነ መልሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚል ነው፡፡

በሐዋርያት ዘመን ሔሮድስ የተባለው ንጉሥ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስን ወኅኒ ቤት ውስጥ ወርውሮት ነበር፡፡ የቀሩት ደቀመዛሙርትና ክርስቲያኖች በዚያ ሰሞን ሲጸልዩ ከርመዋል፡፡ በአንድ ሌሊት በማርቆስ እናት ቤት ውስጥ ተሰብስበው አምሽተው ነበር፡፡ ድንገት የቤቱ በር ሲንኳኳ ሮዴ የምትባል የቤት ሠራተኛ ደጁን ልትከፍት ወጣች፡፡ ማነው ብላ ስትሰማ የቆመው እስረኛው ቅዱስ ጴጥሮስ መሆኑን በድምፁ አወቀች፡፡ ደስታ ግራ ሲያጋባት በሩን መክፈትን ረስታ ወደ ውስጥ ሮጠችና ጴጥሮስ መምጣቱን ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን አላመኑአትም፡፡ ጤንነቷን ተጠራጥረው ‹አብደሻል› አሏት፡፡ እርግጠኛ ሆና ተናገረች፡፡ እነርሱ ግን መልሰው ‹‹የቆመው ጴጥሮስ ሳይሆን መልአኩ ነው፡፡›› አሉ፡፡ ይደንቃል የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች እንዲህ በር ሲንኳኳ ‹መልአክ ነው› ብለው የሚገምቱ መንፈሳዊያን ነበሩ፡፡ (ሐዋ. 12፡12-15)

ቅዱሳንመላእክት እኛ የሰው ልጆች ከመፈጠራችን ቀድመው የተፈጠሩ ታላቅ ወንድሞቻችን ናቸው፡፡ እንዲያውም ምድርና የሰው ልጅ ሲፈጠር ደስ እያላቸው ‹‹እልል›› ይሉ ነበር፡፡ (ኢዮ. 38፡6) ቅዱሳን መላእክትን እግዚአብሔር ለእንዳንዳችን ጠባቂዎች አድርጎ ሠጥቶናል፡፡ ከክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብለው የተማሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ስለ መላእክት ጠባቂነት ጋር ይህን ያህል እምነት ከነበራቸው እኛም የመላእክቱን ጠባቂነት ማመን ለዚህ ዘመን ክርስቲያኖችም ምን ያህል ይገባን ይሆን? ቅዱሳን መላእክት በክርስትና ሕይወት ለሚኖርሰው ሁሉ የመላእክት ረዳትነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለሁሉ ብርታት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን በሥጋው ወራት በተያዘባት ምሽት ሲጸልይ ‹‹ከሰማይም መጥቶ የሚያበረታው መልአክ ታየው›› ተብሎ ተጽፏል፡፡ (ሉቃ. 22፡43) ይህም ቀርበው አገለገሉት‹ለከ ኃይል› እያሉ አመሰገኑት ማለት ሲሆን ለእኛም የመላእክት ርዳታ አያስፈልገኝም እንዳንል የሚያስተምረን ነው፡፡

ቅዱሳን መላእክት በምድር የሚሆነውን ያውቃሉ:: (2 ሳሙ 14:20) በበደላችን ስንጸጸት "ኃጢአትህ ተሠረየችልህ" ይላሉ (ኢሳ 6:7) በክፋታችን ጸንተን ከቀጠልን ደግሞ "ይቅር አይሉም" (ዘጸ 23:20)
ስለእኛ በእግዚአብሔር ፊት ቆመው "የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?" ብለው ያማልዳሉ:: (ዘካ 1:12)

ባለንበት ዘመን በዓለም ሁሉ በበሽታ የሚሠቃየው ብዙ ነው:: በሕመም ለሚሠቃየው ሁሉ

"መልአክ ቢገኝለት እየራራለት [ለእግዚአብሔር] ፡— ቤዛ አግኝቻለሁና ወደ ጕድጓድ እንዳይወርድ አድነው፡ ቢለው፥ ሥጋው እንደ ሕፃን ሥጋ ይለመልማል፤ ወደ ጕብዝናውም ዘመን ይመለሳል" ኢዮ 33:23-25

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
የጸሎት ጥበብ - ፩

ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርን የተረዳ ያወቀ ሰው እግዚአብሔርን እንደሚገባ'ው አድርጎ ሲያነጋግረው ከዚያን ጊዜ አንሥቶ መልአክ ይኾናል፡፡ ነፍስ ከፈቃዳተ ሥጋ ሰንሰለት ነጻ የምትወጣው በዚህ መንገድ ነውና፤ ሕሊና ከፍ ከፍ የሚለው በዚህ መንገድ ነውና! ማደሪያችን ወደ ሰማይ የሚሻገረው በዚህ መንገድ ነውና፤ አንድ ሰው ግብረ ዓለምን የሚንቀው በዚህ መንገድ ነውና፤ አንድ ሰው የቱንም ያህል ነዳይ ወይም ባሪያ ወይም ተራ ወይም ዝቅ ያለ ቢኾንም እንኳን በንጉሥ ዙፋን ፊት የሚቆመው በዚህ መንገድ ነውና፡፡ እግዚአብሔር የሚመለከተው የንግግርን ውበት ወይም የቃልን ርቱዕነት ሳይኾን የመንፈስን ንጹህነት ነውና፡፡ በዚህ መንገድ መጥተን ወደ አእምሮአችን የመጣውን ብንናገርም እንኳን፥ ጸሎታችን ግዳጅ የሚፈጽም ኾኖናልን እንመለሳለን፡፡

እንግዲህ ይህን ማድረግ ምን ያህል ቀላል እንደ ኾነ ታስተውላለህን? በዚህ ዓለም ሰዎች ዘንድ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ለመለመን የንግግር ክህሎት (ብልሐት) ያሻዋል፡፡ የሚለመነው ሰው በቀላሉ የማይገኝ ከኾነ ደግሞ አጃቢዎቹን ማሳመን ይኖርበታል፡፡ ጥሮ ለፍቶ ካገኘው በኋላም ጉዳዩን በዝርዝር ማስረዳት ይጠበቅበታል፡፡ እግዚአብሔርን ለማናገር ግን የዚሁ ተቃራኒ ነው፡፡ ከተሰበረ ልብ በቀር ሌላ ምንም ምን አያስፈልግም፤ ወደ እርሱ ለመቅረብም የሚከለክል ማንም አይኖርም፡፡ “እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ ሩቅ አምላክ አይደለሁም” ይላልና (ኤር.23፥23)፤ የምንርቀው እኛ ነን እንጂ እርሱ ዘወትር ቅርብ ነው፡፡

እግዚአብሔርን ለማነጋገር የንግግር ክህሎት (ብልሐት) አያስፈልገንም የምለውስ ለምንድን ነው? እንዲያውም ብዙ ጊዜ ድምፅም ቢኾን አያስፈልገንም፡፡ አንተ በልብህ ብትናገርና እግዚአብሔርን ማናገር እንዲገባ'ህ ብታናግረው እርሱ ጸሎትህን ለመስማት ዘንበል ይላል፡፡ ሙሴ ጸሎቱ የተሰማው በዚህ መንገድ ነውና፤ ሐና ጸሎትዋ የተሰማው በዚህ መንገድ ነውና፡፡ ወደ እግዚአብሔር እንዳይቀርቡ ብሎ ሕዝቡን ለማራቅ የሚቆም ወታደር የለም፤ አሁን ሰዓቱ አይደለም ብሎ የሚከለክል ዘበኛም የለም፡፡ እግዚአብሔርም፦ “አሁን ላነጋግርህ አልችልም፤ ሌላ ጊዜ ተመለስ” አይልም፡፡ ይልቅ ልታነጋግረው በመጣህበት ቅጽበት አንተን ለመስማት ይቆማል፡፦፥ የምሳ ሰዓትም ቢኾን፣ የአራት ሰዓትም ቢኾን፤ እጅግ አስቸጋሪ ጊዜም ቢኾን፣ በገበያ ቦታም ቢኾን፣ በመንገድ ላይም ቢኾን፤ በባሕር ውስጥም ቢኾን፣፤ በዳኛ ፊት በምትቆምበት በችሎት ፊትም ቢኾን፥ እግዚአብሔርን ብትጠራው መጥራት እንደሚገባህ አድርገህ እስከ ጠራኸው ድረስ ጸሎትህን እንዳይሰማ የሚከለክለው ግድግዳ የለም፡፡ ...

("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 18-19 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

@beteafework
@beteafework
የጸሎት ጥበብ -፪

ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት ልንነጋገር እንደሚገባን እንወቅ፡፡ ጸሎት ማድረስ ያለብን እንዴት እንደ ኾነ እንረዳ፡፥ ይህን ለማወቅ ወዶ ቤተ መጻሕፍት መኼድ፤ ወይም ገንዘብ መክፈል፤ ወይም የንግግር ክህሎትን ለመማር ጊዜ መመደብ አያሻንም፡፡ የተገባ ጸሎትን ስማድረስ መሻት ብቻ በቂ ነው፤ ክህሎቱ በራሱ ይመጣልና፡፥ በዚህ [መንፈሳዊ] ችሎት ፊት የምትናገረውም ለራስህ ብቻ አይደለም! ለሌሎች ለብዙ ሰዎችም ጭምር ነው እንጂ፡፡

በጸሎት ውስጥ ሊኖር የሚገባው ክህሎትስ ምንድን ነው? የጸሎት ጥበብ፥ ይኸውም፦፡ የተዋረደ ልብና የተሰበረ መንፈስ መያዝ፤ በውሒዘ አንብዕ (በዕንባ ጅረት) መቅረብ፤ ከዚህ ዓለም የኾነውን ምንም ነገር አለመሻት፤ የወዲያኛው ዓለም የኾኑ ነገሮችን (ክብሮችን) መሻት፣ መንፈሳዊ ምግባራትን መለመን፤ እግዚአብሔር በጠላቶቻችን ላይ መዓት እንዲያዘንብ አለመለመን፤ ቂም በቀልን ማራቅ፤ [ሥጋዊ] ሁከትን ኹሉ ከነፍስ ማስወገድ፣፤ በተሰበረ ልብ መቅረብ፣ ትሑት መኾን፤ የውሃትን እጅግ መለማመድ፣ ስለ ሌሉች ሰዎች ስንናገር በጎ በጎውን መናገር፤ ከክፉዎች ኅብረት መለየት፣ የዓለም (የሰው) ኹሉ ጠላት ከኾነው ከዲያብሎስ ጋር ምንም ምን አንድነት አለማድረግ ነው፡፡

የዚህ ዓለም ሕጎች እንኳን ሳይቀሩ አንድ ሰው ስለ ንጉሥ ለሌሎች የሚናገር፤ በተለይም ከንጉሥ ጠላቶች ጋር የሚገናኝ ከኾነ ጽኑ ቅጣት ያገኘዋል፡፡ ስለዚህ አንተም ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ራስህና ስለ ሌሎች ስትነጋገር የሰዎች ኹሉ ጠላት ከኾነው ከዲያብሎስ ጋራ ምንም ምን አንድነት ሊኖርህ አይገባም፡፡

ስለዚህ የጸሎትን ጥበብ ገንዘብ አድርግ፡፡ ይህንን ጥበብም (ከቀራጩ) ከመጸብሐዊው ተማር፤ እርሱን መምህር አድርገህ ለመቀበልም አታወላውል፡፡ እርሱ ከአፍአ ሲመረመሩ እዚህ ግባ የማይባሉ ቃላትን በመናገር ማግኘት ያለበትን ኹሉ ለማግኘት የተገባ ኾኗልና (ሉቃ.18፥9-14)፡፡ ተመልከት! በጽርይት ሕሊና በንጽህት ልቡና ስለ ቀረበ አንዲቱ ቃሉ ብቻ ደጀ ሰማያትን ለመክፈት በቂ ነበረች፡፡ ይህችንስ እንዴት ነበር ያቀረባት?
➛ኃጢአቱን በማመን፤
➛ ደረቱን በመድቃት፤
➛ዓይኑን እንኳን ወደ ላይ ወደ ሰማይ ቀና ባለማድረግ!

አንተም እንደዚህ ብትጸልይ ጸሎትህ ፈጥና ግዳጅ የምትፈጽም ትኾንልሃለች፡፡ ኃጥኡ እንደዚህ በመጸለዩ ጻድቅ ከኾነ፥ ጻድቅ ሰው እንደዚህ አድርጎ ጸሎት ማድረስን ቢያወቅ ደግሞ እንደ ምን ያማረ የተወደደ ሊኾን አንደሚችል ልብ ብለህ አስተውል፡፡

("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 20-21 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
#እንደ_ኃጢአት_አዋራጅ_የለም

እንደ ኃጢአት አዋራጅ የለም፡፡ ኃጢአትን የሚያደርግ ሰው በሐፍረት ካባ ብቻ የሚከናነብ አይደለም፤ አስቀድሞ ከነበረው ማስተዋልና ማገናዘብም ይዋረዳል እንጂ፡፡ ይህንንም ለመረዳት የአዳም የቀድሞ ክብሩን ማሰብ እንቸችላለን፡፡ ዳግመኛም ኃጢአትን ከሠራ በኋላ ያገኘውን ውርደት እንመልከተው፡፡ “በሰርክ ጊዜ ጌታ በገነት ውስጥ ድምፀ ሰናኮ ብእሲ እያሰማ ወደነርሱ ሲመጣ በሰሙ ጊዜ አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር ፊት በገነት ዕንጨት መካስከል ተሰወሩ” (ዘፍ.3፥8)፡፡ በዚህስ አዳም እንደ ምን ባለ ውርደት እንደ ተያዘ ታስተውላላችሁን? ምሉእ በኩለሄ ከኾነው፣ ፍጥረታትን ካለ መኖር ወደ መኖር ካመጣው፤ የተሰወረውን ኹሉ ከሚያውቀው፤ የሰውን ልቡና የፈጠረና በኀልዮ የሠሩትን ዐውቆ ከሚፈርደው (መዝ.33፥15)፤ ልብ ያሰበውን ኩላሊት ያጤሰውን መርምሮ ከሚያውቀው (መዝ.7፥9)፤ ልቡናችን ያሰበውን ከሚያውቀው (መዝ.44፥21) ከእግዚአብሔር ሊሸሸግ መውደዱ ከማወቅ ወደ ድንቁርና ከክብር ወደ ኃሣር እንደ ኼደ ያመለክታልነ፡፡ እኛም ኃጢአት ስንሠራ እንደዚህ ነው፡፡ መሸሸግ ባንችል እንኳን መሰወርን እንሻለን፡፡ ይህን ማድረጋችንም በኃጢአታችን ምክንያት ክብራችን እንደ ምን እንዳጣን፤ ሐፍረታችንን መሸፈንም እንደ ምን እንዳቃተን ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን የሠራ ሰው እንኳንስ በረኻ በኾነች በዚህች ምድር በገነት መካከልም መደበቅ አይችልም፡፡

("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 81 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
#ቅዱስ_ሚናስ

ቅዱስ ሚናስ በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው። በግብጻውያን ልዩ ቦታ አለው ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም። ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው። በተለይ ለታመመ ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ ባለ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው።

ቅዱስ ሚናስ ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው። የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ፣ በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ፣ በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ፣ ሃብትን ክብርን ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ፣ በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ በአላውያን ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ህዳር 15 በሰማዕትነት ያረፈ ሲሆን ሰኔ 15 ቤተ ክርስቲያኑ መርዩጥ በተባለ አገር የከበረችበት ነው።

በአንድ ወቅት 18 ቀሳውስት በሥራ ጉዳይ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛን ለማነጋገር ወደ ቅዱስ ሚናስ ገዳም ጉዞ ጀመሩ። ቀሳውስቱ በጉዟቸው መንገድ ስተው ሲባዝኑ ከአንድ የበረሓ ሰው ጋር ተገናኙ።

የበረሓው ሰው መርዩጥ የሚገኘው የቅዱስ ሚናስ ገዳም ለመሄድ መንገድ እንደሳቱ ቀድሞ ተረድቶ ነበርና "የማር ሚናስን ገዳም ነው የምትፈልጉት? በማለት ይጠይቃቸዋል። እነርሱም ችግራቸውን እንዴት እንዳወቀ በልባቸው እያደነቁ "አዎን" አሉት። ሰውዬውም እየመራ ከገዳሙ አደረሳቸው አቡነ ቄርሎስም ወደ በር ወጥተው ተቀበሏቸው።

ከዚያ "ምነው ዘገያችሁ? መንገድ ሳታችሁ እንዴ?" ብለው እንደ ቀልድ ጠየቋቸው። እነርሱም "አዎን! በጣም ተቸግረን ሳለን ይህ የበረሓ ሰው ደርሶልን መንገዱን አሳየን" ብለው ወደ ሰውየው ለማመልከት ዘወር ሲሉ እርሱ በአካባቢው የለም። አቡነ ቄርሎስም "መንገድ እንደጠፋችሁ ስለተረዳሁ ሚናስን ልኬላችሁ ይዟችሁ የመጣው እርሱ ነው" አሏቸው።

አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን!
“ደጋግመህ ኃጢአት ብትሠራም ደጋግመህ ንስሐ ግባ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሐኪም ቤት እንጂ ፍርድ ቤት አይደለችምና፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በዓለ መንፈስ ቅዱስ / ጰራቅሊጦስ

ይህች ታላቅ ዕለት ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት አንስት የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡ አስቀድሞ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ደብረ ዘይት በተባለ ታላቅ ተራራ ላይ ሳሉ እንዲህ ብሎ አስተምሯቸው ነበር “ኃይልን ከአርያም እስክልክላችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም በጸሎት ቆዩ፡፡”/ሉቃ 24፡36/ መቶ ሃያው ቤተሰብም በኢየሩሳሌም ሀገር በምትገኝ በቤተ መቅደስ በአንድነት ሆነው በጸሎት በመትጋት ቆዩ፡፡ 120ው ቤተሰብ የሚባሉት 12ቱ ሐዋርያት፣ 72ቱ አርድእት/አገልጋዮች/ እና 36ቱ ቅዱሳን አንስት/ሴቶች/ ናቸው፡፡

ከዕርገት በኋላ በአሥረኛው ቀን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ወዳሉበት፣ በጸሎትና በምሥጋና ወደ ሚተጉበት ሥፍራ በእሳት አምሳል /ምሳሌ/ ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው፡፡ ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ ምስጢር ተገለጠላቸው፣ ይፈሩ የነበሩት ሐዋርያትም ወንጌልን ለማስተማር ደፋሮች ሆኑ፣ በተለያየ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እውቀት ተሰጣቸው፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ፡፡ ይህንን ታላቅ ኀይል እና ሰማያዊ ስጦታን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን በታላቅ ዝማሬና እልልታ አመሰገኑት፡፡

በዚያም ዕለት  በዓለ ሃምሳ የሚባለውን የአይሁድን በዓል ለማክበር ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቁጥራቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሐዋርያቱን ታላቅ የዝማሬና የእልልታ ድምፅ ሰሙ፡፡ ከመቶ ሃያው ቤተሰብ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ የተሰበሰቡት ሁሉም እንዲሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ አስተማራቸው፡፡ “እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ እኛን የሰው ልጆችን ለማዳን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር መጥቶ ከክፉ ሥራ ተመለሱ፣ ኀጢአትን አታድርጉ፣ በቅድስና ኑሩ፣ ወደ እኔም ተመለሱ ቢላችሁ፤ እናንተ ግን ምንም በደል ሳይኖርበት ገረፋችሁት፣ አንገላታችሁት፣ በመስቀል ላይም ሰቀላችሁት፡፡ እርሱ ግን እግዚአብሔር ነውና ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፡፡ እርሱ ግን አሁንም ይቅር ባይ ነውና ከኀጢአታችሁ ተመለሱ ንስሐም ግቡ፡፡” በማለት አስተማራቸው፡፡ የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያት በፊት የሚያውቁት አንድ ቋንቋ ብቻ ነበረ፡፡ በዚህ ሰዓት ግን ሰባ ሁለት ቋንቋን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው ለሁሉም በየቋንቋቸው አስተማሯቸው፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር ከተመለከቱት ብዙዎች እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ወደ ሐዋርያትም ቀርበው “አባቶቻችን እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁና ምከሩን፡፡ እንደ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆንና በቅድስና እንድንኖር ምን እናድርግ?” በማለት ጠየቁ፡ በዚያች ቀን ቁጥራቸው ሦስት ሺ ያህል ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ክርስቲያን ለመሆን ቀረቡ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፡፡ “እነሆ ሁላችሁም ንስሐ ግቡ፡፡ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት አምናችሁ ተጠመቁ፡፡” አላቸው በዚያው ዕለትም ሦስት ሺ ሰዎች ወደ ሐዋርያት በመቅረብ ኀጢአታቸውን ተናገሩ፤ ሐዋርያትም እግዚአብሔር ይፍታችሁ እያሉ ልጅነትን የሚያሰጣቸውን ጥምቀት አጠመቁዋቸው፡፡
ከዚያ ቀን ጀምሮም በየዓመቱ ይህችን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውን በዓለ ጰራቅሊጦስን ክርስቲያኖች በታላቅ ደስታና ምሥጋና እናከብራታለን፡፡

በጽርሐ ፅዮን የወረደው የአብ በረከት፣ የወልድ ፍቅር ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችንም ጋር ይሁን!!!

@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡ በሌላ አገላለጽ ብነግራችኁ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ጾመ ሐዋርያት (ሰኔ ጸም) ነገ ሰኔ 17/2016 ዓ.ም
(JUNE 23/2024 G.C) ይገባል፡፡

@beteafework         @beteafework
@beteafework         @beteafework
@beteafework         @beteafework
Live

አስፍሐ ገነተ ጽጌ የፈለገ አእምሮ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ደቀ መዛሙርት የምረቃ መርህ ግብር

https://www.youtube.com/live/AbIBgz7OmVc?si=45kxDNZTLOR5XnVj
አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።

ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው ቤት አለ። "የምን ቤት?" ብለህ ብትጠይቀኝ "ልብህ ነዋ" ብዬ እመልስልሃለሁ፤ "ማን ይኖርበታል?" ካልኸኝም "እግዚአብሔር ነዋ" እልሃለሁ።

አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?

እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል?

(Dn Abel Kassahun Mekuria )
2024/06/25 00:10:50
Back to Top
HTML Embed Code: