Telegram Group Search
የተሳሳተ መረጃን አንከተል🙏🙏

ከአረፋ በአል ከኡዱህያ እርድ ጋር ተያይዞ ለከተማችን በርካታው ማህበረሰብ እስከ 200 ከብት አርደን አዳርሰናል በእለቱም እርዱን ለማከናወን በመጡ እንግዶች የበአል ስጦታ በቄራ ግቢ ለተገኙ የተወሰኑ መሳኪኖች ከ3000–5000 ብር አበርክተዋል በድምሩ የመቶ ሺ ብር ሰደቃ አድርገው እዛው የጨረሱት ሲሆን የተሳሳተ መረጃን በመያዝ በተደጋጋሚ ሀላል በጎ አድራጎት ቢሮ ድረስ በመምጣት ከንዘብ እየሰጣቹ ነው ተብላል ስጡን በማለት ለብዙ ድካምና እንግልት መሳኪኑ ተጋልጣል።ለእያንዳንዱ ስራ ከኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን የራሳቸው ሰው መድበውበት ስራው በተሳካ መልኩ ተጠናቋል። ምንም አይነት የገንዘብም ሆነ የቁስ እደላ የለም በአላህ ፍቃድ እንግዶቻችን በኛ አስተባባሪነት ተደስተው ተመልሰዋል።በሌላ ማህበረሰብ ሊጠቅምና ሊገነባ በሚችል ሰፊ ስራ እንገናኛለን  ኢንሻ አላህ እስከዛ በዱአ እንበርታ አላህ ያቆየን ያቆያቹ።

🥀 ስለሆነም ማህበሩን በተለያየ መልኩ ለማገዝና ከወጣቶቹም ጎን በመሆን የቻላችሁትን አስተዋፆ ማበርከት የምትሹ አካላት በሚከተሉት አድራሻዎች ልታገኙዋቸው ትችላላችሁ።

👉 አድራሻ፦ ቢላል_መስጂድ_ህንፃ_አንደኛ_ፎቅ
     ስልክ፦ 09-12-33-00-91
               09-10-88-30-37
               09-30-66-66-13

#ሀላል_በጎ_አድራጎት_ማህበር
#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!
https://www.tg-me.com/ሀላል መረዳጃ ዲላ/com.halale_merdaja_dilla
ሀላል በጎ አድራጎት በዲላ ማረሚያ

አካባቢው ለሚታረሙ ሙስሊም ማህበረሰቦች በበቂ ሁኔታ የኡዱህያ ስጋ የማከፋፈል መርሀ ግብሩን በተሳካ መልኩ አጠናቋል።ከኢማን ኢስላሚክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር እናመሰግናለን

👋 ስለሆነም ማህበሩን በተለያየ መልኩ ለማገዝና ከወጣቶቹም ጎን በመሆን የቻላችሁትን አስተዋፆ ማበርከት የምትሹ አካላት በሚከተሉት አድራሻዎች ልታገኙዋቸው ትችላላችሁ።

👉 አድራሻ፦ ቢላል_መስጂድ_ህንፃ_አንደኛ_ፎቅ
     ስልክ፦ 09-12-33-00-91
               09-10-88-30-37
               09-30-66-66-13

#ሀላል_በጎ_አድራጎት_ማህበር
#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!
https://www.tg-me.com/ሀላል መረዳጃ ዲላ/com.halale_merdaja_dilla
"የልጅነት-ውጥን፤ የአፍላነት-ጥረት፤ የወጣትነት-ስኬት"

🌹 ክብር ለሚገባው ክብርን ምስጋና ለሚያሻውም ምስጋናን እንቸራለን። እኛ ከራሳችን አንዳች ነገርን ለማድረግ አቅሙም ብልሀቱም የለንም የአላህ መልካም ፍቃድ ቢታከልበት እንጂ። ይህን ድንቅ ስኬትም ላሳየን አምላክ የሚገባውን ያህል ምስጋና እናደርሳለን፥ አልሀምዱሊላሒ-ረቢል አለሚን።

🌹 በያዝነው ሳምንት በከተማችን ዲላ ብሎም በአካባቢያችን ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማይታወቅ ድንቅ ተግባር በጌታችን ይሁንታ ለመሳካት ችሏል። ለአመታት በሌሎች አካባቢዎች ሲከወን ተመልክተን እንከጅለው የነበረን መልካም ስራ ተራው ደርሶን እኛም የእድሉ ተካፋይ ለመሆን በቅተናል።

🌹 "ሀላል" የተሰኘው የልበ-ቀናዎች ስብስብ ልግስናና ቸርነት ከሞላቸው ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ጋር በፈጠረው ጠንካራ ግንኙነት ከ200 በላይ ወይፈን እና ቁጥራቸው ሰባት የሚደርሱ በጎችን ለተከበረው የአረፋ በዓል መስዋዕት በማድረግ ከሰባት ያላነሱ ከተሞችን፤ 12 ወረዳዎችን እንዲሁም በከተማችን ዲላ የሚገኙ ነዋሪዎችና ተቋማትን (ዩኒቨርሲቲ፣ ማረሚያ እና መሳጂዶችን) ጨምሮ ቁጥራቸው ከ3,000 ለሚልቁ ቤተሰቦች በዓሉን በደስታ ያሳልፉ ዘንድ የስጋ እደላ ፕሮግራም ሲያከናውን ውሎ አምሽቷል።

🌹 "ሀላል መረዳጃ ማህበር" በአስደናቂ የአመራር ብቃት፤ በቀልጣፋ አገልግሎት፤ አክብሮት በተሞላው መስተንግዶ እንዲሁም ጨዋነትን በተላበሰ አፈፃፀም የ1445ኛውን ዓመተ-ሒጅራ የአረፋ በዓል ታሪክ በሚያወሳው መልኩ በሰደቃ አድምቀውት ውለዋል፥ ይህን ሰናይ ተግባር አድንቀናል አመስግነናልም።

🌹 "ሀላል" ዛሬ ላይ ከሚፈፅማቸው ግሩም ተግባራት በተጨማሪ በቀጣይም ለመስራት ያሰባቸው በርካታ ውጥኖች አሉት። እነኚህ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ዛሬ ላይ የማይቻሉ መስለው ቢታዩም በአላህ ፍቃድ ሁሉም እውን እንደሚሆን ባለሙሉ ተስፋ ነን፥ ኢንሻአላህ።

👉 በመጨረሻም "ሀላል" የወጣቶች ስብስብ እንደመሆኑ በርካታ እገዛዎችን ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይሻል። ይህን መሰል ባለራዕይ፤ ትጉህ እና ቆራጥ ስብስብ ወደ ተሻለ ደረጃ ማድረስ የሁሉም ሀላፊነት ሊሆን ይገባዋል።

🥀 ስለሆነም ማህበሩን በተለያየ መልኩ ለማገዝና ከወጣቶቹም ጎን በመሆን የቻላችሁትን አስተዋፆ ማበርከት የምትሹ አካላት በሚከተሉት አድራሻዎች ልታገኙዋቸው ትችላላችሁ።

👉 አድራሻ፦ ቢላል_መስጂድ_ህንፃ_አንደኛ_ፎቅ
ስልክ፦ 09-12-33-00-91
09-10-88-30-37
09-30-66-66-13

#ሀላል_በጎ_አድራጎት_ማህበር
#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!
https://www.tg-me.com/ሀላል መረዳጃ ዲላ/com.halale_merdaja_dilla

By:-Arefate abdulgefar
በቅርቡ በሀላል በጎ አድራጎት አማካኝነት ለመመረቅ ቀናቶች ብቻ የቀሩት መስጂድ ኢንሻ አላህ በቅርብ ቀን 💪💪💪


ስለሆነም ማህበሩን በተለያየ መልኩ ለማገዝና ከወጣቶቹም ጎን በመሆን የቻላችሁትን አስተዋፆ ማበርከት የምትሹ አካላት በሚከተሉት አድራሻዎች ልታገኙዋቸው ትችላላችሁ።

👉 አድራሻ፦ ቢላል_መስጂድ_ህንፃ_አንደኛ_ፎቅ
     ስልክ፦ 09-12-33-00-91
               09-10-88-30-37
               09-30-66-66-13

#ሀላል_በጎ_አድራጎት_ማህበር
#ኑ_በጋራ_ሆነን_የተሻለ_ማህበረሰብ_ለመፍጠር_እንትጋ!
https://www.tg-me.com/ሀላል መረዳጃ ዲላ/com.halale_merdaja_dilla
2024/06/28 13:52:49
Back to Top
HTML Embed Code: