Telegram Group Search
Audio
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘረቡዕ
#ወንጌል

ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በቅዳሴ ሰዓት የሚነበቡ ምንባባት እና ቅድመ ወንጌል የሚባል ምስባክ
ሳይንስ እና ሃይማኖት
መግቢያ

ይህ መጽሐፍ በሁለት ክፍሎች የተከፈሉ ስምንት ምዕራፎች አሉት። የመጀመሪያው ክፍል ስድስት (6) ምዕራፎች ያሉት ሲሆን፣ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ ሁለት (2) ምዕራፎች አሉት።
የመጀመሪያው ክፍል በሳይንስ፣ በምክንያትና ሃይማኖት ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው። ሳይንስ ምንድን ነው? ከሚለው መሠረታዊ ጥያቄ በመነሣት ሳይንሳዊ የእውቀት መንገድ (Scientific Method) የሚባለውንና ስለ ሳይንስ የሚነገሩ ነገሮችን ይዳስሳል። ይህን ጉዳይ መዳሰስ ያስፈለገበት ምክንያት፣ የሳይንሳዊ የእውቀት መንገድን ምንነትና የዐቅም ዳርቻና ወሰን በአግባቡ ካለመገንዘብ የሚፈጠሩ ብዙ ችግሮች ስለሚታዩ ነው።

ሳይንስ በሥነ-ፍጥረት ውስጥ ያሉ ነገሮችን ለማወቅ የሚደረግ የሰዎች ፍለጋና ጥረት እንደ መሆኑ፣ በዚህ ሂደት ውስጥ ያሉትን ዘርፈ- ብዙ የሆኑ ሰብአዊ ሁኔታዎች ማወቅና መረዳት በእጅጉ አስፈላጊ ነው። በተለይም ደግሞ ሳይንሳዊውን የእውቀት መንገድ ከሥር መሠረቱ ደኅና አድርገው የሚማሩበት አጋጣሚ ያላገኙና ሳይንስን ከሆነው በላይ አግዝፈው የሚመለከቱ ወገኖች ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ ነገርን ከሥሩ ውኃን ከጥሩ እንዲሉ ከዚህ ለመጀመር ነው።

ሳይንስ የሚጀምረው በሳይንሳዊ መንገድ ከተረጋገጡ እውቀቶች ነውን? ፍጹም እውነትስ ነውን? ሳይንሳዊ እውቀት ቋሚ ነውን? ሳይንስ ከግላዊ እሳቤና አመለካከት የጸዳ “ነጻ' ነውን? ፍጹም ገለልተኛስ (objective) ነውን? የሚሉ ጉዳዮችን ማየት አስፈላጊ በመሆን መጽሐፉ በምዕራፍ አንድ ላይ እነዚህን ጉዳዮች በመዳሰስ ይጀምራል።
ምዕራፍ ሁለት ስለ ሳይንቲዝም (Scientism) ምንነትና በእርሱ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን የሚመለከት ነው። ሳይንቲዝም (Scientism) ማለት ስለ እውነታና ስለ ዐለም ትክክለኛውን ሊነግረን የሚችለው ሳይንስ እና ሳይንሳዊው መንገድ ብቻ ነው የሚል እሳቤ ነው። ሳይንቲዝም፣ “ከሚታየውና ከሚዳሰሰው ውጭ ሌላ ምንም ነገር የለም፣ ብቸኛው የእውቀት ምንጭም ሳይንስ ነው" የሚል እምነት ነው። እንዲህ ያሉት የሳይንስ አማኞች፣ እውነት ሊገኝ የሚችለው በሳይንሳዊ መንገድ ብቻ ስለሆነ ከሳይንስ ውጭ ያለው ነገር ሁሉ (ሃይማኖትም ጭምር) ከግለሰቦች ተራ አመለካከትነት ያለፈ ቁም ነገርነት የለውም ይላሉ።

ታዲያ ይህ የሳይንቲዝም አማኞች አስተሳሰብና አቋም ሳይንሳዊ መሠረት ያለው ነውን? ሳይንቲዝም ራሱ “ሳይንሳዊ” ነውን? ሳይንስስ እነርሱ እንደሚሉት ስለ እውነታና ስለ ህልውና እርግጡን ሊነግረን ይችላልን? የሚሉ ጉዳዮችን መዳሰስ አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ምዕራፍ እነዚህን ነገሮች ይዳስሳል።

ከዚህም ጋር የሳይንቲዝም ታሪካዊና ፍልስፍናዊ መነሻና ሂደት፣ ሳይንቲዝም ዛሬ ያለበት ሁኔታ፣ የሥነ-አመክንዮ ችግሮቹ፣ ሳይንስና ድኅረ-ዘመናዊነት (Post-Modernism) ፣ እና በሳይንስ ላይ የሚቀርቡ የአሁን-ዘመን ቅሬታዎች ተዳስሰዋል። በተለይም ደግሞ ልዩ ልዩ ዓላማ ያላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ሳይንስን ከሆነው በላይ በማግዘፍና ወደ ሃይማኖትነት ደረጃ በማሳደግና አይነኬ በማድረግ በሳይንስ ስም የራሳቸውን ግላዊና ቡድናዊ ፍላጎት የማስፈጸም ጤናማ ያልሆኑ ነገሮች በስፋት ስላሉ ይህን ጉዳይ መዳሰስ አስፈልጓል።

ምዕራፍ ሦስት፣ ሳይንስ ወሰን/ገደብ አለው ወይስ የለውም? የሚለውን መሠረታዊ ጉዳይ የሚዳስስ ነው። ሳይንስ የራሱን የእውቀት መንገድ (scientific method) ወይንም ደግሞ መነሻ መሠረቶቹን ትክክል ስለ መሆን አለመሆናቸው በሳይንሳዊ መንገድ ማረጋገጥ ይችላልን? በሳይንሳዊ መንገድ የሚመራመሩ ወገኖች ሥራቸውን የሚጀምሩት ሁሉንም ነገር በሳይንሳዊ መንገድ አረጋግጠው ነውን? የየት-መጣ (መገኛ) ጥያቄን፣ የመኖርን ትርጉምና የፍጻሜን ጥያቄ፣ ሥነ-መለኰታዊና ሃይማኖታዊ፣ ሥነ-ምግባራዊ፣ ፍልስፍናዊ እና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ ያሉ ጥያቄዎችንስ ሳይንስ የመመለስ ዐቅም አለውን? የሚሉ ጉዳዮችን መመልከት ተገቢ በመሆኑ ይህ ምዕራፍ እነዚህን ጉዳዮች የሚዳስስ ነው።

እንደዚሁም፣ ቁሳዊ ሀልዎት ካላቸው ነገሮች ባሻገር የሆኑ መንፈሳዊ (ረቂቃን) ነገሮች (ነፍስ፣ መላእክት፣ እግዚአብሔር) መኖር አለመኖራቸውን በሳይንሳዊ መንገድ ማወቅና ማረጋገጥ ይቻላልን? ሳይንስ ይህን በመሰሉ ነገሮች ላይ የመናገርና የመበየን ሥልጣንስ አለውን? ስለ እግዚአብሔር መኖርና ስለ ማንነቱስ ልናውቅ እንችላለንን? ከተቻለስ እንዴት? ሳይንስ ሃይማኖትን ማረጋገጥም ሆነ ውድቅ ማድረግ ይችላልን? ሳይንስ ሊያውቃቸው/ ሊያረጋግጣቸው የማይችላቸው ጉዳዮች አሉን? ካሉስ ምንድን ናቸው? ሳይንሳዊ እውቀት ወሰኑና ዳርቻው የት ነው? የሚሉ ዐበይት ጉዳዮችን መመልከት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ምዕራፍ እነዚህንና መሰል ሐሳቦችን የሚቃኝ ነው።




ምዕራፍ ዐራት ደግሞ ሳይንስ እና ሃይማኖት አብረው ሊሄዱ ይችላሉን? የሚለውን ጉዳይ የሚዳሰስ ነው። ከሳይንስ ወገን ነን ከሚሉ አካላት በሃይማኖት ላይ የሚቀርቡ የተለያዩ ክሶች አሉ። በዋናነትም፣ ሃይማኖታዊ እምነት “ሳይንሳዊ አይደለም”፣ “ሊረጋገጥ የሚችል አይደለም (Unprovable)”፣ “በማስረጃ የተደገፈ አይደለም”፣ “አላስፈላጊ ነው” የሚሉ ክሶች ስለሚቀርቡ፣ እነዚህ ነገሮች እንደሚባለው ናቸው ወይስ አይደሉም? የሚለውን መዳሰስ አስፈላጊ በመሆኑ ነው።

እንደዚሁም ሳይንስ ለክርስቲያኖች ምን ያረግላቸዋል? ሳይንስ ለአማኞች ያስፈልጋቸዋልን? የሚለውን ጉዳይ መዳሰስም አስፈላጊ ነው። ከዚህም ጋር “እኛ ከትውፊት ነጻ ነን”፣ “እኛ አስተሳሰባችንም ሆነ አሠራራችን ማናቸውንም ነገር መርምሮና ፈትሾ የሚቀበል እንጂ ከባለፈው የተቀበልነውና የምንቀበለው ነገር (ትውፊት) የለም የሚሉ አካላት ስላሉ፣ ይህ አባባል ምን ያህል እውነት ነው? ከትውፊት ነጻ የሆነ እሳቤና አረዳድ ሊኖር ይችላልን? የሰው ምክንያታዊነት ከትውፊት የተነጠለና ከትውፊት ፍጹም ነጻ ነውን? ሳይንስስ ከትውፊት ነጻ ነውን? ትውፊትን መናቅና ማቃለልስ ይቻላልን? የሰው ልጅ አእምሮስ ያለ ምንም ውጫዊ አካል እገዛም ሆነ አስፈላጊነት በራሱ ምርምር ብቻ ሁሉንም የሕይወት እንቆቆልሾች የመፍታት ዐቅም አለውን? እንደዚህ ሲል የነበረው የአውሮፓ ኢንላይትመንት እሳቤስ ውጤቱ ምን ሆነ? የሚሉ ጉዳዮችን መዳሰስ አስፈላጊም ተገቢም በመሆኑ ይህ ምዕራፍ እነዚህንና መሰል ጉዳዮችን የሚዳስስ ነው።

ምዕራፍ አምስት አቴይዝምን (ኢአማኒነትን) የተመለከተ ነው። አቴይዝም ሳይንስ ነው ወይስ እምነት? ከሚለው አንሥቶ የዘመናዊው አቴይዝም ታሪካዊ አመጣጥ በአጭሩ የተዳሰሰበት፣ እንዲሁም አቴይዝም በሰው ልጆች ላይ ያደረሳቸው ጥፋቶች ታሪካዊ ማስረጃ የቀረበበት ነው። ከዚህም ጋር የመጀመሪያውን መነሻ ጥያቄ በተመለከተ መልስ አለው ወይስ የለውም? አቴይዝም እውነት ቢሆን ኖሮ ምን ያስከትል ነበር? የሚሉ ጉዳዮችን የተመለከተ ምዕራፍ ነው።  አቴይስቶች (ኢአማንያን)፣ “እግዚአብሔር ማለት ሰዎች በዐለም ውስጥ ያለውን አሠራር በማያውቁበት ዘመን የፈጠሩት ማብራሪያ ነው፤ አሁን ግን ሳይንስ ነገሮች እንዴት እንደሚሠሩ ምስጢሩን ስለ ገለጠልን እግዚአብሔር የሚያስፈልግበት ምክንያት የለም” ይላሉ። ታዲያ ይህ ሐሳባቸው ትርጉም ያለው ነውን? የምዕራቡን ዐለም ከዚህን ያህል ክርስትና-ጠልነት ያደረሰው ምክንያትስ ምንድን ይሆን?
አቴይስቶች፣ “ሃይማኖት የግጭቶችና የጦርነቶች ዋና ምንጭ ነው" በማለት ለዐለም ሰላምና ለሰው ልጆች ደኅንነት ሃይማኖት- አልባነትን እንደ መልካም አማራጭ ሲሰብኩ ቆይተዋል፣ ዛሬም እየሰበኩ ናቸው። ታዲያ ያለ ሃይማኖት ለመኖር የተደረገው የዘመናችን ሙከራስ ለሰው ልጆች የተሰበከውን ደስታና ምቾት አስገኝቶላቸዋልን? አቴይዝም ለሰው ልጆች ነጻነትን፣ ክብርንና ሰላምን ለማስፈን ፍልስፍናዊ መሠረት አለውን? ሞራል ያለው ኅብረተሰብ ለመፍጠርስ ፍልስፍናዊ መሠረት አለውን? አቴይዝም በምድራችን ላይ ከዳር እስከ ዳር እውን ቢሆን፣ ፍትሕና መተዛዘን የሚባሉ ነገሮች ፍልስፍናዊ መሠረት ሊኖራቸው ይችላልን?

ሰውን ከአምልኮ ነጻ አደርጋለሁ ብሎ የተነሣው አቴይዝም፣ በእውነት ሰዎችን ከአምልኮ ነጻ አድርጓቸዋልን? የግጭትና የጦርነት ዋነኛ ምክንያት የሆነውን ሃይማኖትን በማዳከም ለምድራችን የተሻለ ሰላም እናመጣለን፣ ሃይማኖተኛነት እየደከመ በሄደ መጠን ጦርነቶችና የሰው ልጆች ስቃዮች እየቀነሱ ይሄዳሉ ተብሎ በዘመናዊ ሳይንስና በአቴይስቶች የተሰበከው እውን ሆኗልን? አንዳንዶች እንደሚሉትና ለብዙ ሰዎችም እውነት ሲመስላቸው እንደሚታየው፣ 20ኛውና 21ኛው መ/ክ/ዘ የሰው ልጅ ከጭካኔያዊ ተግባሮች የራቀባቸውና ጦርነትና ግፍ የቀነሰባቸው “የሠለጠኑ” ዘመናት ናቸውን? 21ኛው መ/ክ/ዘ በሰብአዊነትና በርኅራኄ የተሻለና “የሠለጠነ ዘመን ነውን? አቴይዝም እውነት ቢሆን ኖሮስ ምን ያስከትል ነበር? የሚሉ ጉዳዮችን የሚዳስስ ምዕራፍ ነው።

ምዕራፍ ስድስት ደግሞ የሥነ-ፍጥረትን አገኛኘት (አመጣጥ) በተመለከተ ያሉ የተለያዩ አስተሳሰቦችን የሚዳስስ ነው። ፍጥረት እንዴት ተገኘ? ሕይወትስ ከየት መጣ? ለሚሉት መሠረታዊ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የሚሞክሩ የተለያዩ እሳቤዎች (እምነቶች) አሉ። “ፍጥረት አማናዊ አይደለም፣ ቅዠት ነው (The universe is not real, it is illusory)” ፣ “ዐለም ራሱ በራሱ ተፈጠረ (Self-Creation)”፣ “ፍጥረት በዕድል ወይም በአጋጣሚ (Chance) ተገኘ”፣ “ፍጥረት ሁል ጊዜም ያለ ዘለዓለማዊ ነው”፣ ወዘተ የሚሉ ሰው-ሠራሽ አስተሳሰቦችን መፈተሸና መመርመር ተገቢ በመሆኑ የመጀመሪያው ክፍል የመጨረሻ ምዕራፍ የሆነው ይህ ምዕራፍ እነዚህንና መሰል ጉዳዮችን የሚመለከት ነው።

ሁለተኛው ክፍል ደግሞ የክርስትና ሃይማኖት እውነት ስለ መሆኑ ምን ምስክሮች ወይም ማስረጃዎች አሉት? የሚለውን ጉዳይ የሚዳስስ ነው። በምድራችን ላይ እኔ ብቻ ትክክል ነኝ የሚለው ሃይማኖት የክርስትና ሃይማኖት ብቻ አለመሆኑ ይታወቃል። ከእውነተኛው አምላክ የተሰጠ አምላካዊ መጽሐፍ ስለ መሆኑ የሚናገረው መጽሐፍም መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ አይደለም። አማኞቻቸው በመለኮታዊ መገለጥ የተሰጡ አምላካዊ መጻሕፍት ናቸው የሚሉላቸው ሌሎች መጻሕፍትም አሉ።

ታዲያ የክርስትና ሃይማኖት ብቸኛው እውነተኛ ሃይማኖት (የሕይወት መንገድ) እርሱ ስለመሆኑ ከሌሎች በተለየ ምን ማስረጃ አለው? የክርስትና ሃይማኖት መሠረታዊ መጽሐፍ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስስ አማኞቻቸው ከእውነተኛው አምላክ የተገኙ ናቸው ከሚሉላቸው ከሌሎቹ መጻሕፍት የተለየ እውነት ለመሆኑ ጠንካራ ማስረጃዎች አሉትን? ካሉስ ምንድን ናቸው? የሚሉ ጉዳዮችን መመልከት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ክፍል እነዚህን ጉዳዮች የሚዳስስ ነው።

ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስን “እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው” የምንለው እንዲሁ ራሱ ነኝ ስላለ ብቻ አምነን ስለ ተቀበልነው ነውን? መጽሐፍ ቅዱስ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል ስለ መሆኑ ምን ምስክሮች (ማስረጃዎች) አሉ? እነዚህ ምስክሮችስ ማስረጃነታቸው ምን ያህል ጠንካራ ነው? ማስረጃዎቹስ ውስጣዊ ብቻ ናቸውን? ወይስ ውጫዊ የሆኑ ማስረጃዎችም አሉ? የሚሉ ጉዳዮችን መዳሰስ እውነቱን ማወቅ ለሚሻ ሁሉ አስፈላጊ ነው። ለክርስትና ሃይማኖትና ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛነት ያሉትን ዘርፈ-ብዙ ማስረጃዎችና ምስክሮች በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። እነዚህም የውስጥና የውጭ ምስክሮች ናቸው።

ምዕራፍ ሰባት የክርስትና ሃይማኖትን በተመለከተ ያሉትን የውስጥ ምስክሮች (Internal Evidence) የሚዳስስ ሲሆን የመጨረሻው ምዕራፍ - ምዕራፍ ስምንት - ደግሞ የውጭ ምስክሮችን (External Evidence) የሚዳስስ ነው።

መልካም ንባብ!
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
And the only war i know that worth the fight is the war with my inner hell(the sin in me).
ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል

“ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም።”
[ዮሐንስ 6: 53]

ጌታችን ኢየሱስ የሰጠን ትልቁ ምስጢር ቅዱስ ቁርባን የራሱን ሥጋና ደም.. ጌታ ኢየሱስ ያለዚህ ሥጋ እና ደም በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም አለን.. በጣም የሚያሳዝነው ግን ጌታ እንዲህ እያለንም ልክ በራሳችን ሕይወት እንደሚኖረን ነገር ከቅዱስ ቁርባን አንሳተፍም..

የክርስትና ሕይወት ትልቁ ግብ ክርስቶስን መምሰል ነው.. ይህንን ግብ ደግሞ ማሳከት የሚቻለው ከቅዱስ ምስጢር ስንሳተፍ ብቻ ነው.. ሥጋችን ያለ ሥጋዊ ምግብ እንደማያድግ ሁሉ ያለ መንፈሳዊ ምግብም(ቅዱስ ቁርባንም) በመንፈሳዊ ሕይወታችን ማደግ አንችልም.. የጌታ ሥጋና ደም አይሁድ እንደመሰላቸው ሥጋዊ የሆነ አባቶቻቸው በልተውት እንደሞቱት ያለ ሆድን የሚሞላ ሳይሆን ይህ ምግብ መንፈሳዊና ሕይወትን የሚሰጥ ነው.. ስለዚህም ጌታ የተናገረው መንፈስ ነው ሕይወትም ነው..

አንዘናጋ የኔ ተወዳጆች.. በቃ ዘሬ እናስብ ስለ ቅዱስ ቁርባን

መልካም የጌታ ቀን

@Apostolic_Answers
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዚህ በሚገባው ዓመት ማውጣት ያለባችሁ ትልቁ እቅድ በክርስቶስ መደሰት ነው እያሉን ነው አባ.. በጣም ደስ ይላል የተወደዱ አባት..

እንደውም ዓመቱን ራሱ “በክርስቶስ መደሰት” ብለን እንሰይመውና እንጀምረው እንዴ😁😁
አዲሱን ዓመት ለመጀመር ቀናት ቀርተዋል ! ምን አቅደዋል?

በአዲሱ ዓመት እነዚህን ለማድረግና በእግዚአብሔር ሐሳብ እና ፈቃድ ለመመላለስ ብናቅድስ?
እንደምን አመሻችሁ ወዳጆች? አመታችንን የቃኘንበት ቪዲዮ ትናንት ማታ upload ከተደረገ በኋላ በቪድዮው ላይ በተስተዋሉ ችግሮች ምክንያት መልሰን አንስተነው ነበር። ዛሬ እነዚያን ችግሮች ለመቅረፍ ሞክረናል። በጣም ብዙ ወዳጆቻችንም ቪዲዮው private ይላል ብላችሁ ስትነግሩን ነበር። ለተፈጠረው ቴክኒካዊ ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን። ጥቂት ቦታዎች ላይ የተወሰኑ ግድፈቶች ላይጠፉ ይችላሉ። በቀጣይ አመት የምንሰራቸው ጥንቅሮች እንዲህ ካሉ ቴክኒካዊ ችግሮች የፀዱ እንዲሆኑ የቻልነውን እንደምናደርግ ቃል በመግባት ይህንን መሰናዶ ትከታተሉት ዘንድ እንጋብዛለን። ቸር ቆይታ።

https://youtu.be/FCAzJQVD_5k?si=wCuyhywS_w3S2bYy
2024/09/10 06:42:08
Back to Top
HTML Embed Code: