Telegram Group Search
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አርጀንቲናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አሮን አንሴልሚኖ ከቡካ ጁኒየር ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ የ 19ዓመቱን ተከላካይ አሮን አንሴልሚኖን 17 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ በስድስት አመት ኮንትራት እንደሚያስፈርሙ ተነግሯል።

ተጨዋቹ ቼልሲን ከተቀላቀለ በኋላ በውሰት ወደ ስትራስቡርግ ሊያመራ እንደሚችል ተዘግቧል።

በሌላ በኩል ሰማያዊዎቹ ከባርሴሎና ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ማርክ ጉዩ የህክምና ምርመራውን በዛሬው ዕለት እንደሚያደርግ ተገልጿል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
ዩናይትድ አሰልጣኝ ሬኔ ሀኬን መሾም ይፈልጋል !

ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የጎ አሄድ ኤግልስ ዋና አሰልጣኝ ሬኔ ሀኬን በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የአሰልጣኞች ቡድን ውስጥ ለመካተት በመስራት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨማሪም የቀድሞ ኮከባቸውን ሩድ ቫን ኔስትሮይን ወደ ቡድናቸው አሰልጣኝ ስብስብ ለማካተት መቃረባቸው መገለፁ አይዘነጋም።

የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በበኩላቸው በቅርቡ የተጨማሪ ሁለት አመታት ኮንትራት ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ናቾ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለማምራት ተስማማ ! ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናች ፈርናንዴዝ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ካድስያ ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን ማጠናቀቁ ተገልጿል። ናቾ ሪያል ማድሪድን ከሀያ ሶስት አመታት በኋላ በመልቀቅ ለሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ካድስያ የሁለት አመት ኮንትራት እንደሚፈርም ተነግሯል። ናቾ ከዚህ በፊት አል ኢትሀድን ለመቀላቀል ተቃርቦ የነበረ…
" ማድሪድን መልቀቅ የህይወቴ ከባድ ውሳኔ ነው " ናቾ

ስፔናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናቾ ፈርናንዴዝ ሪያል ማድሪድ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ቃዲሲያ መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ከሀያ ሶስት አመታት በኋላ ከሪያል ማድሪድ ጋር የተለያየው ናቾ ፈርናንዴዝ በሳውዲ አረቢያ ሊግ አዲስ አዳጊው አል ቃዲሲያ የሁለት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

" ማድሪድን የመልቀቅ ውሳኔ የህይወቴ ከባዱ ውሳኔ ነው " ሲል የገለፀው ናቾ በክለቡ ባደረግኩት ነገር ደስተኛ ነኝ ሪያል ማድሪድ ውስጥ ምንም የማሳካው ነገር አልቀረኝም።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እኛ ፈረንሳይን አንፈራም " ቫውት ፋስ

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቫውት ፋስ ቡድናቸው ቀጣይ የጥሎ ማለፍ ተጋጣሚው ፈረንሳይን እንደማይፈራ ገልጿል።

የሌስተር ሲቲው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቫውት ፋስ በንግግሩም " እኛ ፈረንሳይ በፍፁም አታስፈራንም " ያለ ሲሆን " እኛ እነሱን ማሸነፍ እንችላለን " በማለት ተናግሯል።

ቫውት ፋስ ቀጥሎም በአሁን ሰዓት ብራዚላዊው ተጨዋች ዴቪድ ሉዊዝ 2014 በነበረው ደረጃ መጫወት እንደሚችል ገልጿል።

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ከፈረንሳይ ጋር የጥሎ ማለፍ ጨዋታቸውን ቀጣይ ሳምንት ሰኞ ምሽት 1:00 ሰዓት ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthiopiaPL 🇪🇹

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባሕር ዳር ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የባሕር ዳር ከተማን ግብ ፍቅረሚካኤል አለሙ ሲያስቆጥር ዓሊ ሱሌይማን ሀዋሳ ከተማን አቻ ማድረግ ችሏል።

ኤርትራዊው የሀዋሳ ከተማ አጥቂ ዓሊ ሱሌይማን በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች አስራ ስምንት በማድረስ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃውን እየመራ ይገኛል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

4️⃣ ባሕር ዳር ከተማ :- 50

1️⃣0️⃣ ሀዋሳ ከተማ :- 38 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

እሮብ - ሀዋሳ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

ሐሙስ - ሲዳማ ቡና ከ ባሕር ዳር ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ለቸኮለ ዘዴ ከ #ዋናው!

🏃🏾‍♂ #ይምጡ#ትጥቅዎን ይውሰዱ!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ናኒ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑ ተገለጸ !

ፖርቹጋላዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ተጨዋች ሉዊስ ናኒ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑን ገልጿል።

ናኒ ወደ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ የሚመጣው የሰማንያኛ አመት ክብረ በዓሉን በማክበር ላይ ለሚገኘው መቻል እግርኳስ ክለብ የክብር እንግዳ ሆኖ እንደሚሆን ተገልጿል።

ናኒ ባስተላለፈው አጭር የቪዲዮ መልዕክትም " ሰላም ኢትዮጵያውያን ሰማንያኛ አመቱን ከሚያከብረው መቻል ግብዣ ስለቀረበልኝ ኩራት እና ደስታ ተሰምቶኛል።

ለእኔ ልዩ ቦታ ያላትን ኢትዮጵያ ለመጎብኘት ጓጉቻለሁ በቅርቡ እንገናኝ።"ሲል ተደምጧል።

ምንጭ :- አራዳ ኤፍኤም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እኛ ሳንሆን መፍራት ያለብን ጣልያን ነች " ሙራት ያኪን

የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሙራት ያኪን የጥሎ ማለፍ ተጋጣሚያቸው ጣልያን ቡድናቸውን ልትፈራ እንደሚገባ ገልጸዋል።

" እኛ በጥሎ ማለፉ ጥሩ ነበርን ጣልያንን ለማሸነፍ የሚያስችል ጥራት ያለው ስብስብ አለን " ያሉት አሰልጣኝ ሙራት ያኪን " መፍራት ያለብን እኛ ሳንሆን ጣልያን ነች " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" እኛ ፈረንሳይን አንፈራም " ቫውት ፋስ የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቫውት ፋስ ቡድናቸው ቀጣይ የጥሎ ማለፍ ተጋጣሚው ፈረንሳይን እንደማይፈራ ገልጿል። የሌስተር ሲቲው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቫውት ፋስ በንግግሩም " እኛ ፈረንሳይ በፍፁም አታስፈራንም " ያለ ሲሆን " እኛ እነሱን ማሸነፍ እንችላለን " በማለት ተናግሯል። ቫውት ፋስ ቀጥሎም በአሁን ሰዓት ብራዚላዊው ተጨዋች…
" እኛም ማንንም አንፈራም ሰኞ እንገናኝ " ሳሊባ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊያም ሳሊባ ቡድናቸው ቤልጂየምንም ሆነ ማንንም እንደማይፈራ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

የቤልጅየሙ ተጨዋች ቫውት ፋስ ለሰጠው አስተያየት ምላሹን የሰጠው ዊሊያም ሳሊባ " እኛ ቤልጂየምንም ሆነ ሌሎችን አንፈራም ፣ እነሱም ካልፈሩ ጥሩ ነው ሰኞ እናያለን።"ሲል ተናግሯል።

ስለ ሮሜሎ ሉካኩ የተጠየቀው ዊሊያም ሳሊባ " ሉካኩ ከአለማችን ምርጥ አጥቂዎች አንዱ ነው ብዙ ተከላካዮች እሱን መጋፈጥ አይፈልጉም " ሲል ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲዳማ ቡና ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ኢማኑኤል ላርዬ እና ደስታ ዮሀንስ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

8️⃣ ድሬዳዋ ከተማ :- 40

1️⃣2️⃣ ሲዳማ ቡና :- 37 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

ሐሙስ - ሲዳማ ቡና ከ ባሕር ዳር ከተማ

ቅዳሜ - መቻል ከ ድሬዳዋ ከተማ 

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ንግግር ጀመሩ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀልን ለማስፈረም ሌስተር ሲቲን ማነጋገር መጀመራቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ሰማያዊዎቹ ኬርናን ዴውስቡሪ ሀልን ለማስፈረም እስካሁን ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ለሌስተር ሲቲ አለማቅረባቸው ተነግሯል።

የ 25ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬርናን ዴውስቡሪ ሀል የልጅነት ክለቡ ሌስተር ሲቲን የሚለቅ ከሆነ ቼልሲን ብቻ መቀላቀል እንደሚፈልግ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጆርጂያ ተጨዋቾች የማበረታቻ ሽልማት ሊሰጣቸው ነው !

በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ተሳትፎ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለው የጆርጂያ ብሔራዊ ቡድን ከሀገሪቱ ቱጃር ግለሰብ የማበረታቻ ሽልማት ሊቀርብለት መሆኑ ተገልጿል።

የቀድሞ የጆርጂያ ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የሀገሪቱ ስመ ጥር ቢሊየነር ቢድዚና ኢቫኒችቪሊ ለብሔራዊ ቡድኑ ማበረታቻ 10 ሚልዮን ዶላር ለመስጠት ዝግጅት ላይ እንደሆኑ ተነግሯል።

በተጨማሪም ብሔራዊ ቡድኑ በጥሎ ማለፉ ስፔንን አሸንፎ ሩብ ፍፃሜ የሚደርስ ከሆነ የማበረታቻ ገንዘቡ በእጥፍ እንደሚያድግ ማሳወቁ ተዘግቧል።

ቢልየነሩ ያለው ሀብት 4.9 ቢልዮን ዶላር የሚገመት ሲሆን ይህም የሀገሪቱ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ( GDP ) ሩብ እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፊል ፎደን ብሔራዊ ቡድኑን ለምን ለቀቀ ? የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን የብሔራዊ ቡድኑን ስብስብ በመልቀቅ ወደ እንግሊዝ የተመለሰው ልጁ ሲወለድ ለመገኘት እንደሆነ ተገልጿል። ፊል ፎደን በቀጣይ እሁድ ወደ ጀርመን በመመለስ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ስብስብን እንደሚቀላቀል ተነግሯል። የ 24ዓመቱ የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን በቀጣይ ሶስተኛ ልጁን…
ፊል ፎደን ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ተመልሷል !

በቤተሰብ ጉዳይ ወደ እንግሊዝ ተመልሶ የነበረው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ፊል ፎደን አሁን ላይ የብሔራዊ ቡድኑን ስብስብ ለመቀላቀል ወደ ጀርመን መመለሱ ተገልጿል።

ፊል ፎደን ለአውሮፓ ዋንጫው ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ዝግጅት ላይ የሚገኘው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ነገ በሚያደርገው ልምምድ ላይ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።

እንግሊዝ የአውሮፓ ዋንጫው የጥሎ ማለፍ ጨዋታዋን እሁድ ምሽት 1:00 ሰዓት ከስሎቫኪያ ጋር የምታደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
Forwarded from HEY Online Market
Samsung Galaxy S22 Ultra
256 GB - 67,000 ETB
512 GB - 78,000 ETB

Samsung Galaxy S23 Ultra
256 GB - 92,000 ETB
512 GB - 109,000 ETB

Samsung Galaxy S24 Ultra
256 GB - 109,000 ETB
512 GB - 124,000 ETB

Exchange Available
🏍️ Free Delivery

Contact us :
0925927457 @eBRO4
@Heyonlinemarket
ቤኒ ማካርቲ ከዩናይትድ ጋር ይለያያል !

የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኞች ቡድን አባሉ ቤኒ ማካርቲ በዚህ ወር ኮንትራቱ ሲጠናቀቅ ቀያዮቹ ሴጣኖችን እንደሚለቅ ተገልጿል።

የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ቤኒ ማካርቲ ከሁለት አመት አመት የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን መሾም ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ መቀላቀሉ ይታወሳል።

በአያክስ ፣ ሴልታቪጎ እና ፖርቶ በፊት መስመር አጥቂነት ተጫውቶ ያሳለፈው ቤኒ ማካርቲ ኬፕ ታውን ሲቲ እና አማዙሉን በአሰልጣኝነትም መርቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊዮኔል ሜሲ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞታል ! የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ በትናንቱ ምሽቱ የቺሊ የኮፓ አሜሪካ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል። የጨዋታውን ሙሉ ዘጠና ደቂቃ ተጫውቶ ያጠናቀቀው ሊዮኔል ሜሲ ይሁን እንጂ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ምቾት እንዳልተሰማው ተናግሯል። " በቀኝ እግሬ ላይ ከመጀመሪያው ምቾት እየተሰማኝ አልነበረም ነገርግን ጨዋታውን…
ሊዮኔል ሜሲ በፔሩ ጨዋታ ላይሳተፍ ይችላል !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ላለበት የኮፓ አሜሪካ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ትላንት ባደረገው ልምምድ አለመሳተፉ ተገልጿል።

ሊዮኔል ሜሲ ለሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ዝግጁ እንዲሆን አርጀንቲና ቅዳሜ ሌሊት ከፔሩ ጋር በምታደርገው የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ እረፍት ሊያደርግ እንደሚችል ተነግሯል።

ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀሏን ያረጋገጠችው አርጀንቲና ምድቧን አንደኛ ሆና የምታጠናቅቅ ከሆነ በቀጣይ በሩብ ፍፃሜው ከሜክሲኮ ወይም ኢኳዶር ጋር የምትገናኝ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአሜሪካ ተጨዋች የዘረኝነት ጥቃት ደረሰባቸው !

የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ትላንት ሌሊቲ ከፓናማ ጋር ያደረገውን የኮፓ አሜሪካ ጨዋታ 2ለ1 መሸነፉን ተከትሎ ተጨዋቾቹ የዘረኝነት ጥቃት እንደደረሳቸው ተገልጿል።

ከሽንፈቱ በኋላ ቲሞቲ ዊሀን ጨምሮ ሌሎች የብሔራዊ ቡድኑን ተጨዋቾች ኢላማ ያደረጉ የዘረኝነት ጥቃቶች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ሲሰነዘሩ ተስተውለዋል።

በጨዋታው ከተሰለፉ ስድስት የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጥቁር ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ቲሞቲ ዊሀ 18ኛው ደቂቃ ላይ የተቃራኒን ተጨዋች በመማታቱ ቀይ ካርድ ተመልክቶ ነበር።

የአሜሪካ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባወጣው መግለጫ የተሰነዘሩ የዘረኝነት ጥቃቶች እንዳሳሰቡት ገልፆ " ለዘረኝነት ጥቃቶች ቦታ የለንም እንደ ተቋም ከምንጠቀመው የመከባበር እሴት ተቃራኒ ነው " ብሏል።

በቀጣይም በዘረኝነት ጥቃቱ ምክንያት የስነልቦና ድጋፍ ለሚፈልጉ ተጨዋቾች እና የብሔራዊ ቡድኑ አባላት እንደሚዘጋጅላቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤድመንድ ታፕሶባ በሀገሩ ፋውንዴሽን አቋቁሟል !

የጀርመኑ ክለብ ባየር ሌቨርኩሰኑ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ኤድመንድ ታፕሶባ በትውልድ ሀገሩ ቡርኪናፋሶ የራሱን ፋውንዴሽን ማቋቋሙን ይፋ አድርጓል።

ኤድመንድ ታፕሶባ የመሰረተው ፋውንዴሽን በሀገሩ ቡርኪናፋሶ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ተቸግረው ለሚገኙ ተረጂዎች ዘላቂነት ያለው ድጋፍ ለመስጠት ማለሙ ተገልጿል።

ኤድመንድ ታፕሶባ በሰጠው አስተያየትም " ቡርኪናፋሶ ውስጥ ባለው የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት በርካቶች ሰብዓዊ ጉዳት ደርሶባቸዋል መርዳት የፈለግኩትም ለዚህ ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/06/28 10:34:57
Back to Top
HTML Embed Code: