Telegram Group Search
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
🟢🟡🔴
ሰኔ 17 | #ቅዱስ_አቡነ_ገሪማ (ይስሐቅ) ተሰወሩ፨

አቡነ ገሪማ ወላጆቻቸው እግዚአብሔርን የሚወዱ የሮም ከተማ ንጉሥና ንግሥት ነበሩ። ልጅ በማጣታቸው እመቤታችንን ለመኑና ደግ ፍሬ ሰጠቻቸው። ስሙን ይስሐቅ ብለው አሳደጉት።

በልጅነቱ በመሞቱ ይስሐቅ በዙፋኑ ተተክቶ ነገሠ። ለ7 ዓመታት ሕዝቡን በፍትሕ እያስተዳደረ መጻሕፍትንም እያጠና ኑሯል።

ከግብፅ በርሃ አባ ጰንጠሌዎን መልዕክት ልከው "ምድራዊ ንግሥና ምን ያደርግልሃል? ይልቁኑስ በሰማይ ለዘለዓለም እንድትነግሥ ወደ በርሃ ና" አሉት።

ወደ ፈጣሪው ጸልዮ በለበሳት ልብስ ብቻ ዙፋኑን ጥሎ መነነ። ቅዱስ ገብርኤልም ደርሶ በቀኝ ክንፉ ነጥቆ ግብፅ አባ ጰንጠሌዎን በዓት ላይ አኖረው። በኋላ 9 ሆነው ወደ ኢትዮጵያ መጡ።

በአንዱ ቀን ይስሐቅ በልቶ ቀደሰ ተብለው ቢታሙ፥ ጉዳዩን ለማስረዳት "ሰዎች ብቻ አይደሉም ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል" ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ አንድ ምዕራፍ ተጠራርጎ ሸሸ።

ይህንን የተመለከቱት አባ ጰንጠሌዎን "ወልድየ ይስሐቅ ገረምከኒ (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ) አሏቸው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮም "#አቡነ_ገሪማ" ተብለው ቀሩ፡፡

ጻድቁ ወንጌልን ገዳማትን ከማስፋፋት ባለፈ ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል፦

🍀 ስንዴ ጠዋት ዘርተውት በ9 ሰዓት ደርሶ፣ ጧት የተከሉት ወይን በ9 ሰዓት ደርሶ ቁርባን ይሰዉ ነበር

አንድ ቀን ምራቃቸው ቢወድቅ ጸበል ሆኖ ዛሬም አለ።

🍀 ብዕራቸው ወድቃ አብባ አፍርታለች። ወንጌልን እየጻፉ ሊመሽ ቢሆን ፀሐይን አቁመዋታል።


🍀 በስምህ የዘከረ 12 ትውልድ ይማራል፣ የተራቈተውንም ለሚያለብስ የብልህ እጅ ያልሠራው የብርሃን ግምጃን አለብሰዋለሁ የሚል ቃልኪዳን ተቀብለዋል።

ሞትን አትቀምስም ተብለው ተሰወሩ። መላእክትም በሠረገላ ጭነው እየዘመሩ ብሔረ ሕያዋን አደረሷቸው።

www.tg-me.com/አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ/com.Ewnet1Nat
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመካከለኛው ምሥራቅ አሜሪካ የተከሰተው ጎርፍ!!
🟢🟡🔴
ሰኔ 20 | የመጀመርያዋ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን #በእመቤታችን ስም ታነፀች።

ይኽም በዓል ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው።
ይህችም በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ አገር፥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ ዕንጨት፣ ያለ ጭቃና ውኃ በሦስት ደንጊያዎች በተወደደ ልጅዋ እጅ የታነፀችበት ነው።

አናጺውም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ሐዋርያት በስብከትና በጥምቀት ወደ ክርስትና ያመጧቸው ምእመናን ስለበዙ ለጸሎትና ለቍርባን የሚሆናቸውን ቦታ ሻቱ። ሕንጻንም ሊሠሩ ሱባኤ ገቡ።

ጌታችንም በታላቅ ግርማ መለኮት ተገልጦ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸው። በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ። ጌታችንም ሦስቱን ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው።

ድንጋዮቹም እንደ ሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ። ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው። እነርሱም እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል።

ይህም የሆነው እመቤታችን ካረገች ከ4ኛ ዓመቱ በ52 ዓ.ም ነው።
(ታሪኩ ወደ ሰኔ 21 ይቀጥላል)
🌹

ዳግመኛም ታላቁ ነቢይ #ቅዱስ_ኤልሳዕ ዐረፈ።
ኤልሳዕ ማለት ‹‹እግዚአብሔር ጠባቂ ነው›› ማለት ነው። ታላቁ ነቢይ ኤልያስ በመንገድ ሲሄድ የሳፋጥ ልጅ አልሳዕን በ12 ጥማድ በሬ ሲያርስ አገኘው።

ኤልያስም ሄዶ መጎናጸፊያውን በላዩ ጣለበት፡፡ ኤልሳዕም እርሻውን ትቶ ተከተለው፡፡ ተመልሶም በመምጣት በሬዎቹን አርዶ፣ ሕዝቡን መግቦ፣ በፍጹም ልቡ ኤልያስን ተከተለ። እግዚአብሔርንም በትንቢቱ 50 ዓመት አገልግሎ በሰላም ዐረፈ።

          #_እንኳን_አደረሳችሁ
        ▸ T.me/አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ/com.Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 21 | የመጀመሪያዋ ቤ/ክ
ቅዳሴ ሆነ። እንዲሁም #እመቤታችን በልጇ መቃብር ላይ እያነባች ጸልያ ልዩ ቃልኪዳን ተቀብላለች።
(ሰኔ ጎልጎታን መጸለይ እንዳትረሱ)

ሰኔ 20 ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሐዋርያት ወረደ። ፊልጵስዩስ በምትባል ሃገር በጴጥሮስ እጅ የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን አነጸ ብለን ነበር።

በዚህች ዕለት ደግሞ አእላፍ መላዕክትን፣ ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዟት ወረደ። ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ፦

1. አስቀድሞ ቤተ ክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን አሳየ፣

2. ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ከመካከል አቁሞ "አርሳይሮስ" ሲል ሾመው። ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ጳጳሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው።

በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት "አክዮስ" እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ። አክዮስ ማለት "ይገባዋል ያሥምርለት" እንደ ማለት ነው። ጌታችን ከዚህ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ።

☘️ አማናዊት ማሕደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ

☘️ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ

☘️ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ

☘️ ሐዋርያት ድንግልን ከበው፣ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቁመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ።


በዚያች ቀን በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ። ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው፦

"ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን እነጹ። ይህችን ዕለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ።" ብሏቸው ከድንግል እናቱ ከመላዕክቱ ጋር ዐረገ።

T.me/አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ/com.Ewnet1Nat
 #እንኳን_አደረሳችሁ
【ሰኔ ጎልጎታ】
🌹🍀🌹🍀🌹

"ምሕረትን የምትለምኚ ድንግል እናቱ፤
አንድያው ልጅሽ አያጥፋን በከንቱ!"

"በእንቲአነ በሊዮ ሰአሊተ ምሕረት እሙ፤
ኢታማስን ግብረ እዴከ እንተ ለሐኮ ቀዲሙ!" (አርኬ)

🌹🍀🌹🍀🌹
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
🌹🌹🌹

በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች እመቤታችን ማርያም ሰኔ 21 ቀን ያደረገችው ተአምር ይኽ ነው፨
▰ ▰ ▰

በቂሣርያው ሊቀ ጳጳሳት በባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን በሠራ ጊዜ በውስጡ የእመቤታችን የማርያምን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ሠሌዳ ፈለገ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ዘንድ ስለ አለ አንድ መልካም ሠሌዳ ነገሩት።

ቅዱስ ባስልዮስም ሠሌዳውን እንዲሰጠው ወደ ባለጸጋው ላከ ባለጸጋውም ይህ ሠሌዳ ለልጆቼ ነው አለ እንጂ ፈቃደኛ አልሆነም።

ከዚያም አልፎ በመድፈር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ። ወዲያውኑም በድንገት ወድቆ ሞተ። ልጆቹም ፈሩ። ያንንም ሠሌዳ ከብዙ ወርቅና እንቊ ጋራ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አምጥተው የአባታቸውን በደል ያቃልልለት ዘንድ ለመኑት።

ቅዱስ ባስልዮስም ያንን ሠሌዳ ወስዶ የእመቤታችንን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ለሠዓሊ ሰጠው። እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም በሌሊት ራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጸችለት። ሥዕሏንም በዚያ ሠሌዳ ላይ እንዳይሥል ከለከለችው። ከዐመፀኛ ሰው እጅ ወስዶታልና።

እጅግም ያማረ የእመቤታችን ሥዕሏ የተሣለበት የሁለት ደናግልም ሥዕል ያንዲቱ በቀኝ ያንዲቱ በግራ ሆኖ የተሣለበት ቀይ ሠሌዳ ያለበትን ቦታ ነገረችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ አመለከተችው ወደዚያ ቦታ ሔደ። ያንንም ሠሌዳ አገኘው። ወደዚያች ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ደስታ አመጣው።

ከዚህም በኋላ ዳግመኛ በአንድ ጣዖት ቤት ሁለት ምሰሶዎች እንዳሉ አስረዳችው። እነርሱንም አምጥቶ በመቅደሱ ፊት ለፊት እንዲአቆማቸው በላያቸውም ሥዕሏን እንዲያኖር አዘዘችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እነዚያን ምሰሶዎች ያመጣቸው ዘንድ ሔደ መሠርያኑም ሊከለክሉት ፈለጉ። ጌታችንም ኃይላቸውን ደመሰሰ። እነዚያንም ምሰሶዎች አምጥቶ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው። በላያቸውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏን አስቀመጠ። እግዚአብሔርም ከእነዚያ ምሰሶዎች በታች የውኃ ምንጭ አፈለቀ በውስጧም የሚታጠብ ሁሉ ከአለበት ደዌ ሁሉ የሚድን ሆነ።

እንዲሁም ከእመቤታችን ማርያም ሥዕል በሽተኞችን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት ፈሰሰ። ይህ ሁሉ የሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በሰኔ ወር በሃያ አንድ ቀን ነው።

በዚያችም ቀን እንዲህ ሆነ። አንዲት ሴት መጥታ ታጠበች። ወዲያውኑም ሁለመናዋ በለምጽ ተሸፈነ። ቅዱስ ባስልዮስም ወደርሱ አስቀርቦ በእርሷ ላይ የሆነውን ጠየቃት። እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባችው ነገረችው።

ቅዱስ ባስልዮስም ታላላቅ ሦስት ኃጢአቶችን ሠራሽ ግን ወደ እግዚአብሔር ንስሐ ግቢ ምንአልባት በደልሽን ይቅር ይልሽ እንደ ሆነ አላት። በዚያን ጊዜም ምድር ተሠንጥቃ እንደ ዳታን ዋጠቻት። እርሷ የረከሰች ስትሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባትን ደፍራለችና።

እኛ ሁላችን የክርስቲያን ወገኖች አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም ለመታሰቢያዋ መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል። ስለ እርሷ ለአዳምና ለሁላችን ለልጆቹ ድኅነት ሆኖአልና ይህንንም በዓል ለማድረግ የሚተጋ የተመሰገነ ነው።

                     🌹🌹🌹
                  T.me/አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ/com.Ewnet1Nat
Audio
ድርሳነ ቅዱስ ዑራኤል ዘወርኃ ሰኔ.
◦ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት ◦
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/07/01 12:26:59
Back to Top
HTML Embed Code: