Telegram Group Search
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ተገድላ ተገኘች። ለ91 ቀናት ታግታ የተሰወረችው ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ተገድላ ተገኝታለች። ለወላጆችዋ ዛሬ መርዶ ተነግሯቸዋል። የአስከሬን የአሸኛነት ስነ-ሰርዓት ዛሬ በአቡነ አረጋዊ ቤተክርስትያን ዓድዋ እንደሚፈፀም ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በተማሪ ማህሌት ተኽላይ ግድያ ዙሪያ ፓሊስ የሚሰጠው መረጃ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል። በተማሪ ማህሌት…
ማህሌት ተኽላይ !

መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ  " ዓዲ ማሕለኻ " ከሚባል ስፍራ ነው ታግታ የተሰወረችው።

የታገተችው ቋንቋ ወደምትማርበት ትምህርት ቤት ስትሄድ ነው።

ባጃጅ ይዘው በመጡ ሰዎች ነበር የታገተችው።

ማህሌት ተኽላይ ታግታ ከተወሰደች በኃላ አጋቾች ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ ወላጅ አባቷ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረው ነበር።

የዓድዋ ከተማ ፓሊስም ፥ ከሳምንታት በኃላ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዳሉ ገልጾ ነበር።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ አድዋ ድረስ ተጉዞ የማህሌት ወላጅ አባት ተኽላይ ግርማይን አነጋግሮ በነበረበት ወቅት ቤተሰቦች ምን ያህል የከፋ ሀዘን እና ጭንቀት ላይ እንደወደቁ መመልከት ችሎ ነበር።

አባት ተኽላይና መላ ቤተሰብ ላለፉት ወራት እንቅልፍ ሚባል አላዩም።

የወለደ ሰው የልጅ ፍቅር በወላጅ የሚያሳደረው ነገር ያውቀዋልና 3 ወር ያህል እንቅልፍ ሳያገኙ ነው የቆዩት።

አቶ ተኽላይ ግርማይ እና መላው ቤተሰቦች ከዛሬ ነገ የልጃቸውን በህይወት ቤት መምጣት ሲጠብቁ ዛሬ ጥዋት ግን ልጃቸው በህይወት እንደሌለች መርዶ ተነግሯቸዋል።

#ዓድዋ

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ማህሌት ተኽላይ ! መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ  " ዓዲ ማሕለኻ " ከሚባል ስፍራ ነው ታግታ የተሰወረችው። የታገተችው ቋንቋ ወደምትማርበት ትምህርት ቤት ስትሄድ ነው። ባጃጅ ይዘው በመጡ ሰዎች ነበር የታገተችው። ማህሌት ተኽላይ ታግታ ከተወሰደች በኃላ አጋቾች ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ ወላጅ አባቷ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረው ነበር። የዓድዋ ከተማ ፓሊስም ፥ ከሳምንታት…
#Update #Adwa

ከ3 ወር በላይ ታግታ አድራሻዋ ጠፍቶ ዛሬ በግፍ መገደለዋ የተረጋገጠው ተማሪ ማህሌት ተኽላይ አጋቾችዋ ገድለው እንደቀበሯት ማመናቸውን ፓሊስ አስታወቀ።

የትግራይ ማእከላይ ዞን ፓሊስ የወንጀል ምርመራ ሃላፊ ኮማንደር ፀጋይ ኣስፍሃ ዛሬ ለ104.4 የመቐለ ኤፍኤም በስልክ በሰጡት ቃል ፥ በእገታው እና ግድያው የተጠረጠሩ መያዛቸውን ገልጸዋል።

ግለሰቦቹ ለፓሊስ በሰጡት ቃል ተማሪ ማህሌትን ገድለው በዓድዋ የፓንአፍሪካ ዩኒቨርስቲ ሊገነባበት የመሰረተ ደንጋይ የተጣለበት ቦታ መቅበራቸውን ቦታው ድረስ በመምራት አሳይተዋል ፤ አምነዋል ብለዋል። 

ተጠርጣሪዎቹ  ማህሌትን እንዴት እንዳገቷት ፣ አግተው ወዴት እንደወሰዱዋት ፣ እንዴት ገድለው እንደቀበርዋትና አስከሬንዋ የተቀበረበት ቦታ ጭምር በዝርዝር ለፓሊስ ማሰየታቸውን ኮማንደሩ በሰጡት መረጃ አረጋግጠዋል።

የተማሪ ማህሌት ተኽላይ አስከሬን ከተቀበረበት ጉድጓድ የማውጣት ስነ-ሰርዓት በመከናወን ላይ መሆኑ የገለፁት ኮማንደር ፀጋይ ፤ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ተጨማሪ ምርመራ ይደረግበታል ብለዋል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
@TikvahEthiopiaTigrigna
#DStvEthiopia

ክረምቱን ልጆችዎ በዲኤስቲቪ እየተዝናኑ ይማራሉ፣ ዓለምን እየጎበኙ ይመራመራሉ! 👩🏽‍🚀

በየትኛውም ዕድሜ ላሉ ልጆችዎ እንደ ኒክ ጁኒየር፥ ማይንድሴት፥ ኒኮሎዲየን እና ጂምጃም ያሉ ቻናሎችን በወር ከ350 ብር ጀምሮ በዲኤስቲቪ።

ክረምቱን ልጆችዎ በዲኤስቲቪ እየተዝናኑ ይማሩ!

የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/3yBcOHc

#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው
#Amahra

በአማራ ክልል ፤ በምዕራብ ጎንደር ዞን ' ታጣቂዎች ' ባደረሱት ጥቃት አንዲት ሱዳናዊ ስደተኛን ጨምሮ 3 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።

በጥቃቱ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የጥቃቱ ባለፈው እሁድ ሰኔ 9/2016 መፈጸሙን አረጋግጧል።

ጥቃት የተፈጸመው ከገንደ ዉሃ ወደ ነጋዴ ባህር ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ " ደረቅ አባይ " በተባለ ስፍራ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የዞኑ ኮሚኒኬሽን ጥቃቱ ከቀኑ 10 ሰዓት መድረሱን አሳውቋል።

የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ፥ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ታጣቂዎች ተኩስ ከከፈቱ በኃላ አንድ ውስጥ የነበረ የመንግስት የጸጥታ አባል ወርዶ የታጣቂዎቹ ጥቃት ለመከላከል ባደረገው የተኩስ ልውውጥ ከመኪናው ውስጥ የነበረች አንዲት ሱዳናዊ ስደተኛና ሌሎች ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን አስረድቷል።

" የጥቃቱን መድረስ ተከትሎ የመንግስት ጸጥታ ኃይል በአፋጣኝ ባይደርሱ ኖሩ ከአሁኑ የበለጠ የከፋ ጉዳት ሊከሰት ይችል ነበር " ሲልም ገልጿል።

የተፈጸመው ጥቃት በዘፈቀደ እንጂ በስደተኛዋ ላይ ያነጣጠረ እንዳልነበር አክሏል።

ስደተኛዋ በወቅቱ ፤ መድሃኒት ገዝታ ወደ መጠለያዋ እየተመለሰች ነበር ተብሏል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያቸው እንዳይወጡ በተደጋጋሚ ቢነገራቸውም አንዳንዶቹ ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻላቸው  ለአደጋ እየተጋለጡ ሲል ገልጿል።

የመረጃው የዶቼቨለ ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
Final Exit Exam Schedule.xls
196.5 KB
#ExitExam

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከአርብ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል።

በኦንላይን ለሦስተኛ ጊዜ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናው፤ በድጋሜ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞችም ይሰጣል፡፡

Via @tikvahuniversity
" የሞባይል ስልክ እና ላፕቶፕ ጠፍቶብኛል የሚል ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ ይችላል " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል ግምቱ 150 ሺህ ብር የሚያወጣን ሞባይል ስልክን ከሌባ ላይ የገዛችን ግለሰብን በቁጥጥር ስር አውሎ ንብረቱን ማስመለሱን አስታወቀ፡፡

ግለሰቧ ከወንጀለኞች በተለያየ ጊዜ የገዛቻቸው ልዩ ልዩ ሞባይል ስልኮችን ፣ ላፕቶፖችንና ታብሌት ይዞ ምርመራው መቀጠሉን አዲስ አበባ ፖሊስ ገልፆል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው ...
    
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው " አለምነሽ ፕላዛ " አካባቢ አንድ ግለሰብ  ግምቱ 150 ሺህ ብር የሚያወጣ አይነቱ አይፎን ፕሮ ማክስ ሞባይል ስልክ ይቀማሉ።

ይህን ተከትሎ አደይ አበባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታሉ።

የግለሰቡን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ፖሊስ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመቀናጀት በቴክኖሎጂ በመደገፍ ባደረገው ክትትል የተሰረቀው ስልክ አራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ከሚገኝ አንድ የሞባይል መሸጫ ሱቅ መኖሩ ይረጋገጣል፡፡

ፖሊስ የህግ አግባብን በመከተል ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትእዛዝ በማውጣት ባደረገው ብርበራ ከግለሰቡ ላይ የተቀማውን ስልክ ጨምሮ በልዩ ልዩ ጊዜያት ከተለያዩ ቦታዎች የተሰረቁ ፦

➡️ 85 ስማርት ሞባይል ስልኮችን  ፣

➡️ 4 ለፕቶፖችን ፣

➡️ 1 ታብሌትና የላፕቶፕ ቦርሳዎችን በኤግዚቢትነት ይዟል።

የቅሚያ ወንጀል የፈፀመውን ተጠርጣሪ ለመያዝ ክትትሉ መቀጠሉን ፖሊስ አመልክቷል።

የሞባይል ስልክ እና ላፕቶፕ ጠፍቶብኛል የሚል ማንኛውም ግለሰብ አደይ አበባ ስቴዲዮም አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ሞባይል ስልኩን በመለየትና  ትክክለኛ ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ  እንደሚችል አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

#AddisAbabapolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የተማሪ ማህሌት ተኽላይ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ።

የማህሌት አስክሬን አጋቾች ከቀበሩበት ወጥቶ የአስከሬን ምርመራ ተጠናቅቆ ዛሬ ከቀኑ 9:00 ሰዓት በዓድዋ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስትያን የቀብር ስነ-ሰርዓት ተፈጽሟል።

የቀብር ስነ-ስርዓቱ የክልል ፣ የዞን እና የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም በርካታ የዓድዋ ነዋሪዎች ተገኝተው ነበር።

ተማሪ ማህሌት ተኽላይ በዓድዋ  ከተማ " ዓዲ ማሐለኻ " የሚባል ቦታ ታግታ ከተወሰደች በኃላ አጋቾች ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር ቤተሰቦቿን ጠይቀው ነበር።

የት እንደ ደረሰች ላለፉት 91 ቀናት ሳይታወቅ ቆይቶ ማህሌት ተገድላ ፤ ተቀብራ አስክሬኗ ዛሬ ተገኝቷል።

ከእገታው እና ግድያው ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ገድለው የቀበሩበትን ቦታ ለፖሊስ መርተው በማሳያት አስክሬኗ እንዲወጣ እና ምርመራ እንዲደረግ ተደርጓል።

የትግራይ ማዕከላይ ዞን ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ፀጋይ ኣስፍሃ ፥ አጋቾቹ የጠየቁትን ብር ቤተሰቦቿ አቅም ስለሌላቸው መክፈል ባለመቻላቸው ማህሌትን ገድለው እንደቀበሯት ገልጸዋል።

#Adwa #Tigray

@tikvahethiopia
2024/06/20 01:14:56
Back to Top
HTML Embed Code: