Telegram Group Search
🌪  የቻይና ሁለት ግዛቶች በታይፎን ያጊ አርብ አመሻሽ ላይ ይመታሉ ተብሎ የተተነበየ ሲሆን በሃይናን እና ጓንግዶንግ ሪዞርቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል።

በሃይናን ደሴት ወደ 420,000 የሚጠጉ ሰዎች አካባቢው እንዲለቁ የተደረገ ሲሆን፤ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፤ በተጨማሪም የአየር በረራ እንዲቋረጥ ተደርጓል።
Audio
መልክአ ቅዱስ ራጉኤል
Audio
መልክአ ቅዱስ ዮሐንስ
. ጳጕሜን 3
   🌈 ርኅወተ ሰማይ
🌈
💚💛❤️

ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት፣ አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት፣ ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ – ሰማይ የሚከፈትባት ቀን" ትባላለች።

[አሁን] በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም። የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት ያለ ከልካይ የሚያሳርጉበት፣

[አንድም] ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንዲህ ተባለ እንጂ።

እመቤታችን ድንግል ማርያም ለዓፄ ናዖድ እንደ ነገረቻቸው፥ በዚህች ዕለት ሁሉም ቅዱሳን ስለሚታሰቡ የእግዚአብሔር የምሕረት መዝገቡ ስለሚከፈት ዕለቷን ክብርት ያሰኛታል።

#በቅዱስ_ሩፋኤል አበጋዝነት (መሪነት) በዚህች ዕለት ለዓመት የሚበቃ ምሕረት ይገኛል።

ስለዚህም አባቶቻችን በዚህች ሌሊት፥ ሦስት መቶ ስልሳ አምስት አቡነ ዘበሰማያትን ሲጸልዩ ያድራሉ። በሌላ ወገን ደግሞ የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መታሰቢያ እንደ መሆኗ ትልቅ ትኩረትም ይሰጣታል።

«☘️ ቸሩ ጌታችን ከተከፈተች ገነት ከተነጠፈች ዕረፍት ሁላችንንም ያድርሰን ☘️»

💚 www.tg-me.com/christian930
💛
www.tg-me.com/AlphaOmega930
❤️
www.tg-me.com/አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ/com.Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ጳጒሜን 3 |
የመላእክት አለቃ የከበረ
#ቅዱስ_ሩፋኤል በዓሉ ነው።

እርሱም ከመላእክት አለቆች ሦስተኛ የሆነ ነው።
ደግሞም ከእስክንድርያ ውጭ በደሴት የታነፀች ቤተ ክርስቲያኑ በከበረ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጸባት የከበረችበት ነው።

ያቺ ደሴት በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የቆመች ናትና የሰዎች ብዛትም በከበደው ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አነሣሣው። ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔርም በከበረ መልአክ ሩፋኤል ስም ጮኹ።

ያን ጊዜ ይህ የከበረ ሩፋኤል ያንን አንበሪ በጦሩ ወግቶ እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር አዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጽ ጸጥ ብለህ ቁም። አንበሪውም ጸጥ ብሎ ቆመ አልታወከም። በውስጧም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለሕሙማንም ፈውስ ሆነ።

🍀 ለእግዚአብሔር ልጅ ምሳሌው የሆነ #የመልከጼዴቅ መታሰቢያው ነው።

አብርሃምም ከጦርነት ነገሥታትን ድል አድርጎ በተመለሰ ጊዜ ኅብስትንና ወይንን አቀረበለት። አብርሃምም ከገንዘቡ ሁሉ ከዐሥር አንድ ሰጠው እርሱ ካህንም ንጉሥም ሁኖ ተሹሟልና።

🍀 መልካም ስም አጠራር ያላቸው #ዓፄ_ዘርዐ_ያዕቆብ ዐረፉ።

ተአምረ ማርያምን ጨምሮ ከ11 ያላነሱ መጻሕፍትን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ደርሰዋል። ብዙ መጻሕፍትን ከውጪ አስመጥተው አስተርጉመዋል፡፡ ሰው ሁሉ ለእመ ብርሃንና ለቅዱስ መስቀሉ ፍቅር እንዲገዛ ጥረት አድርገዋል፡፡

እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ከመውደዳቸው የተነሣ ዛሬም ድረስ በሃገራችን ድንግል ማርያም "የዘርዓ ያዕቆብ እመቤት" እየተባለች ትጠራለች፡፡

🍀 #ቅዱስ_ሰራጵዮን ዐረፈ።
ይህም ቅዱስ ራሱን ባርያ አድርጎ እየሸጠ አሕዛብን ወደ ክርስቶስ የሚመልስ ነው።


🍀 ባለ ስድስት ክንፉ፣ በቃልኪዳናቸው መልአከ ሞትን የማያሳዩት #አቡነ_ቀፀላ_ጊዮርጊስ ዐረፉ።

T.me/አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ/com.Ewnet1Nat
Audio
መልክአ ቅዱስ ሩፋኤል
Audio
የቅዱስ ሩፋኤል ክብር እና ሥልጣን
በመሬት መንሸራተት የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ትናንት ጷጉሜ 2/2016 ዓ.ም በቄለም ወለጋ ዞን ጅማ ሆሮ ወረዳ በሶስት ቀበሌዎች ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት በንብረት ላይ እና የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል። ተጨማሪ በ10 የአርሶ አደር ቤቶች ላይ አደጋው ጉዳት ሲያደርስ፣ በ15 ቤተሰብ እና 150 ሰዎች ተፈናቅሏል።
🟢🟡🔴
ጳጕሜን 4 | #ቅዱስ_አባ_ባይሞን ዕረፍቱ ነው።

ይህም አባት ባይሞን በአስቄጥስ ገዳም ለሽማግሌዎችም ለጎልማሶችም አረጋጊ ወደብ የሆነ ነው። ከጠላት ሰይጣን ፈተና የሃይማኖት ጥርጥር ወይም ደዌ ያገኘው ሁሉ ወደርሱ ይመጣል ወዲያውኑ ያረጋጋዋል፤ ከደዌውም ይፈውሰዋል።

ከአፉ በሚወጡ ጥዑም ምክሮቹ የታወቀ ነው። ጥቂቶቹ፦

፩. "ባልንጀራህ በወደቀ ጊዜ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥበት። ይልቅስ አንቃው፣ አበረታታው፣ ሸክሙንም አቅልለት እንጂ"

፪. "ለጥሩ ባልንጀራህ የምታደርገውን ደግነት ለክፉው በእጥፍ አድርግለት። መድኃኒትን የሚሻ የታመመ ነውና። አልያ ግን ለበጎው ያደረከው ከንቱ ነው።"

፫. "ባልንጀራህ በበደለ ጊዜ አትናቀው። ያንተ ተራ በደረሰ ጊዜ ጌታህ ይንቅሃልና።"

፬. "የማንንም ኃጢአት አትግለጥ (አታውራ)። ካላረፍክ ጌታ ያንተኑ ይገልጥብሃልና።"

፭. "አንደበትህ የተናገረውን ሁሉ ለመሥራት ታገል። አልያ ውሸታም ትሆናለህ።"

🍀
T.me/አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ/com.Ewnet1Nat
2024/09/09 00:20:21
Back to Top
HTML Embed Code: